TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" በሰው ላይ ጨዋታ ነው እንዴ የያዙት ? " - ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ' ጨፌ ሜዳ ' ነዋሪዎች በመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ጠፍቶ እስከወዲያኛው መቅረት እጅግ በጣም ተማረዋል።

በተደጋጋሚ ቅሬታ ቢያቀርቡም መፍትሄ አላገኙም።

ነዋሪዎች ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

➡️ ከአምትና ከሁለት ዓመት በፊት እንዲሁ ይጠፋል ይቃጠላል መጥተው ይቀይራሉ ፤ የሚቀይሩት ኃይሉ የተመጣጠነ አይደለም ወዲያ ይጠፋል።

➡️ ሰው ላይ ጨዋታ ነው እንዴ የያዙት ? ለምንድነው እንዲህ የሚደረገው ? ሰራን ብለው እንደሄዱ ወዲያው ይጠፋል። እነሱ ደመወዛቸውን እየበሉ ነው ፤ እንጀራ ጋግሮ መብያ ይጠፋል እንዴ ?

➡️ ከ30 እና 40 ዓመት በፊት ስንገለገልበት በነበረበት መጠን እንድንገለገል እየተደረገ ሰው ጭለማ ውስጥ ነው ያለው።

➡️ ፍሪጅ ተበላሽቷል አይሰራም ፤ ቴሌቪዥን ተበላሽቷል ለሰራተኛ ብር እየሰጠን ነው የምናሰራው። ለፍተን ደክመን አጠራቅመን በእርጅና ጾም እንፈታበታለን ያለው ነገር ሁላ እየተበላሸብን ነው። ባለፈው ብዙ ነገር ተበላሽቶ ጥለናል።

➡️ ፍሪጅ የሚፈልግ መድሃኒት አለ ያ ሁሉ ከንቱ ቀረ ሰው ይሙት እያሉ ነው ?

➡️ ህጻናት ፣ ልጆች ፣ አቅመ ደካማ አለ ስንት ጣጣ ነው ያለው። ቤት ውስጥ ብዙ ነገር ነው ያለው። ቢደወልላቸው አይመጡ ፤ መጣን መጣን እያሉ ያሾፋሉ። ሲመጡ ደግሞ ምኑን ነክተውት እንደሚሄዱ አይታወቅም ኬላ እንኳን ሳያልፉ ወዲያው ይጠፋል።

➡️ የተቦካ እህል እየተበላሸ ነው የት ይጋገር ?

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ኃላፊ ዳይሬክተር ይሄይስ ስዩም ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ፤ ቅሬታው እውነትነት እንዳለው ገልጸዋል።

" ለፈጠርንባቸው ችግር ደንበኞቻችንን ይቅርታ ጠይቃለሁ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለት ሳምንት ሳይሞላ ወይም ከዛም ባነሰ ጊዜ መፍትሄ እንሰጣቸዋለን " ብለዋል።

#ፈረንሳይለጋሲዮን #ጨፌሜዳ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM