TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ያለመከሰስ_መብት?⬇️

«ያለመከሰስ መብት»ን በተመለከተ በበርካታ የህግ መዝገበ ቃላት ላይ የሚደጋገመው ትርጓሜ «አንድ ግለሰብ ወይንም አካል የህግ ጥሰት የፈፀመ መሆኑ እየታወቀ ለወንጀሉ ተጠያቂ እንዳይሆን የሚደረግለት ህጋዊ ከለላ» ከሚለው ጋር የሚስተካከል ነው።

የዚህ «ልዩ ከለላ» ተጠቃሚዎች ከሆኑት መካከል የህዝብ #እንደራሴዎች#የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና #የዳኝነት አካላት ይገኙበታል።

የመብቱ የጀርባ አመክንዮ ግለሰቦቹን እና አካላቱን በመክሰስ ወይንም ለፍርድ በማቅረብ ከሚገኘው ጠቀሜታ ይልቅ ካለ ክስ እና #ተጠያቂነት በማለፍ የሚሳካው ማህበረሰባዊ ግብ የላቀ ነው ከሚል ዕምነት ጋር ይያዛል።

ሆኖም ይሄ የከለላ መብት #ተነስቶ ግለሰቡ ወይንም አካሉ ላይ ክስ የሚከፈትባቸው አግባቦች ፈፅሞ የሉም ማለት አይደለም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ ህገ- መንግስት እና የክልል ህገ-መንግስታት ይሄንን መብት ከሰጣቸው ወገኖች መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተጠቃሽ ናቸው።

ለአብነት የህዝብ ተወካዮችን በሚመለከተው የአፌዲሪ ህገመንግስት #አንቀፅ 55 (6) ላይ የአለመከሰስ መብትን እና መብቱ የሚነሳበትን
አግባብ እንደሚከተለው ደንግጓል።

«ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈፅም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፣ በወንጀልም አይከሰስም።»

ይሄን መሰረት አድርጎ #ያለመከሰስ መብታቸውን ከተነጠቁት የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና የቀድሞው የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ዓለማየሁ ጉጆ ይጠቀሳሉ።

ከሰሞኑ ደግሞ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና ስድስት የክልሉ ምክር ቤት አባላት በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ውሳኔ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

እንደ ኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ሁሉ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ህገ -መንግስት አንቀፅ 48 (6) ላይ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ
መብት የሚነጠቅበት አግባብ መቀመጡን ልብ ይሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR (1).pdf
#ይነበብ🚨

" በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል።

በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ '  ሰፍሯል።

ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ?

- በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት #የዳኝነት_አካላት ለተወሰነ ጊዜ፦

በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ #ክትትል_ለማድረግ

የኮምፒዉተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችንና ሰርቨሮችን ለመለየት፣

መገናኛዎችን #በክትትል ሥር ለማዋል ወይም #ለመጥለፍ

ድርጊቶችን፣ ባህሪዎችንና ንግግሮችን በድምፅ እና በምስል #ለመቅረፅ እና #ፎቶግራፍ_ለማንሳት

የደብዳቤ ልዉዉጦችን #ለመጥለፍ እና #ለመያዝ

በሽፋን ሥር ስለሚደረግ ምርመራና በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍ ለመጠቀም፣

የሚያስችል ትዕዛዝ #ለወንጀል_መርማሪ_አካላት መስጠት ይችላሉ።

- የመርማሪ አካል የተደነገጉትን የማስረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚችለዉ ፍርድ ቤት አስተማማኝ ምክንያት መኖሩን በማረጋገጥ #ሲፈቅድ_ብቻ ነዉ።

- መርማሪው አካል #አስቸኳይ_ሁኔታ_ካጋጠመው በአካባቢው ያለውንና የሚመለከተውን የዓቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስረጃዎችን ሊሰበስብ ይችላል፡፡

- መርማሪ አካል #ያለፍርድ_ቤት_ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስረጃ ለመሰብሰብ በጀመረ በ፵፰ ሰዓት ውስጥ ምክንያቶቹንና በዓቃቤ ሕግ የተሰጠውን ጊዜያዊ ፈቃድ ጨምሮ ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል። ፍርድ ቤቱ የጥያቄውን አግባብነት መርምሮ ለመቀበል ወይም ደግሞ ውድቅ ለማድረግ ይችላል፡፡

- ፍርድ ቤት የምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበስብ ለመርማሪ አካል ፈቃድ ሲሰጥ፡-
ሀ. ማስረጃ ስለሚሰበሰብበት ዘዴ እና ስለሚከናወንበት አግባብ፤
ለ. የሚከናወንበት ጊዜ በተመለከተ ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡

- የማስረጃ ማሰባሰቢያው ዘዴ ጠለፋ ወይም ክትትል እንደሆነ #ጠለፋዉ ወይም #ክትትሉ የሚደረግበትን የስልክ ፣ የፋክስ ፣ የሬዲዮ ፣ የኢንተርኔት ፣ የኤሌክትሮኒክስ ፣ የፓስታና የመሳሰሉትን የግንኙነት መስመሮች አድራሻ ወይም መለያ መጥቀስ አለበት፡፡

- ማንኛውም የመገናኛ አገልግሎት አቅራቢ በመርማሪ አካል ጠለፋውን ለማካሄድ ሲጠየቅ ጠለፋው በፍ/ቤት ወይም በአቃቤ ሕግ የበላይ ሃላፊ የተፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ አለበት፡፡

- በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሕግ አስከባሪ አካላት በጠለፋ የተገኘ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ #በጠለፋ_በተገኘበት_መልክ_በቀጥታ ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም፡፡

ሙሉ ረቂቅ አዋጁን በዚህ ያንብቡ 👇 https://t.iss.one/tikvahethiopia/88222

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia