TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የሹፌሮችድምጽ

" የታገቱትን ሊፈልግ የሚወጣ የጸጥታ ሃይል የለም ሄዱበት በተባለው መንገድ የሚገባ የለም " - ጣና የከባድ መኪና ሹፌሮች ማህበር

በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የከተማ አቋራጭ እና ሃገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች ለእገታ እና ግድያ እየተጋለጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል።

የጣና የከባድ መኪና ሹፌሮች ማህበር በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ከ200 የሚበልጡ አሽከርካሪዎች ቢገደሉም ችግሩን ለመቅረፍ ግን ምንም እንቅስቃሴ እየተደረገ አለመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ  ገልጿል።

" ሰው ታፈነ ሲባል ሰውን ያህል ነገር ታፍኖ የአካባቢው የጸጥታ ሃይል የት፣እንዴት ታፈነ የሚለውን ጠይቆ እና አነፍንፎ የሚንቀሳቀስ መንግስት አጥተናል" ሲሉ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አክለውም " መታገትህን ትናገራለህ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ይባላል የታገቱትን ሊፈልግ የሚወጣ ሃይል የለም ሄዱበት በተባለው መንገድ የሚገባ የለም " ነው ያሉት።

አጋቾች የሚደራደሩት በስልክ ነው ገንዘብም የሚገባው በባንክ ነው ያሉ ሲሆን እገታን እዚህ ደረጃ ያደረሰው መንግስት ለሚታገቱ እና ለሚገደሉ ሰዎች የሰጠው ትኩረት በማነሱ ምክንያት ነው ብለዋል።

እንደ ማህበሩ አመራር ገለጻ ህዳር አንድ ላይ አራት አሽከርካሪዎች መተሃራ እና አዋሽ ሰባት መሃል ታፍነው በታጣቂዎች ተወስደዋል።

በተደጋጋሚ የሹፌሮች መታገት እና መገደል የነበረባቸው አንደ ታች አርማጭሆ ያሉ አካባቢዎች ሚሊሻዎችን በየመንገዱ የማሰማራት እና መንገዱን የመጠበቅ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን የጠቀሱ ሲሆን በተጠቀሰው አካባቢ መሻሻል አለ ብለዋል።

" ከአይከል -ጭልጋ- ገንዳውሃ " ያለው መንገድ ግን አሁንም ለሹፌሮች እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ከመንግሥት ውጪ የሆነ እና በየመንገዱ የሚሰበሰብ እስከ 20 ሺ ብር የሚደርስ ህገወጥ ቀረጥ ሹፌሮችን እያማረረ ነው ብለውናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የሹፌሮችድምጽ

" ከታህሳስ 2 እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ 6 ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል " - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር

🚨 " ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው !! "

የከባድ መኪና ሹፌሮች በሃገር አቋራጭ እና ከተማ አቋራጭ ጉዞዎቻቸው ወቅት በታጣቂዎች የሚደርስባቸው እገታ እና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ባለፉት 5 አመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገደሉ ሹፌሮች ቁጥርም 230 መሻገሩን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከታህሳስ 2 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ ስድስት ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል ብለዋል።

አራቱ ሹፌሬች የተገደሉት በመተማ ጎንደር መንገድ ጭልጋ አካባቢ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ከጎንደር ሳንጃ መንገድ ፈረስ መግሪያ አካባቢ ነው።

ፈረስ መግሪያ አካባቢ የተገደሉት ሹፌርና ረዳት ሲሆኑ ከታህሳስ 2 ጀምሮ አግተው ገንዘብ እንዲሰጣቸው ሲደራደሩ ቆይተው ታህሳስ 5/2017 ዓ/ም 120 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ገድለው እንደጧላቸው ሃላፊው አስረድተዋል።

የችግሩን ክብደት ሲያስረዱም " አንዳንድ ቦታዎች ላይ መኪና ሲበላሽ የመጀመሪያ ስራ ወርዶ ዝቅ ብሎ ማየት አልሆነም የመጀመሪያ ስራ ወርዶ መሮጥ ነው ምክንያቱም እንደቆምክ አንድ ታጣቂ መጥቶ ሊያግትህ ወይም ሊገድልህ ይችላል ምን ተበላሸ ብለህ የምታየው አንድ ሚሊሻ ይዘህ ተመልሰህ መጥተህ ነው " ብለዋክ።

ማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ከሶረቃ እስከ ሳንጃ፣ ፈረስ መግሪያ ፣ ' ኢትዮጵያ ካርታ ' የሚባለው አካባቢ ድረስ ለሹፌሮች አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ሳንጃ እና አሽሬ ባለው የመንገድ ክፍል ከህዳር 25 እስከ አሁን ድረስ 5 ሹፌሬች እንደታገቱ ተናግረዋል።

ሃላፊው ፤  " ሰው የሹፌሮችን እገታ እና ግድያ አሁን በክልሉ ከሚታየው የጸጥታ ችግር ጋር ያያይዘዋል ነገር ግን እገታ በጠቀስናቸው አካባቢዎች 7 እና 8 ዓመት አልፎታል ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው " ሲሉ አማረዋል።

" በብዛት የሹፌሮች እገታ ያለበት አካባቢ ግጭት ያለበት አካባቢ አይደለም " ያሉት አመራሩ " ታገትን ተገደልን ብለን ስንናገር : ግጭት ወዳለበት አካባቢ እያሽከረከራቹ በመሆኑ ነው ' እየተባለ ይደበሰበሳል እንባላለንም ነገር ግን ይህ ለወንበዴ ሽፋን መስጠት ነው " ብለዋል።

በመተማ እና ጎንደር መሃል ቦና ፣ መቃ እና ግንታ አካባቢ አንድ ሹፌር እስከ 40 እና 50 ሺ ብር እንዲከፍል እንደሚገደድ አንስተው በ05/04/17 ሳይከፍሉ ያለፉ ሹፌር እና ረዳት በዚሁ አካባቢ መገደላቸውን አስታውሰዋል።

ለምንድነው የምትሰበስቡት ? ስንልም " ከምናግታቹ ብለን ነው " የሚል መልስ ይሰጠናል ብለዋል።

እገታ የሚፈጸምባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ኃይል ካምፕ ያለበት ቢሆንም ለሹፌር ጥበቃ የሚያደርግ ሆነ ወንበዴዎችን የሚያጸዳ ሃይል እንደሌለ ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት በሳንጃ ሶረቃ መንገድ 2 ሺህ ብር በመክፈል በአጃቢ ሚሊሻ ለመንቀሳቀስ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአካባቢውን የጸጥታ አመራሮች ምላሽ እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM