TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል። አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦ - ሰርገኛ…
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ የታየው ቅናሽ (በቀዳማይ ወያነ ገበያ) ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11,000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6,000 እስከ 6,500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

- የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

- ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል።

- ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ቀንሷል። 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

- ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደ የጥራቱ)።

- ስኳር አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል።

- 25 ኪሎግራም መኮሮኒ 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 1,800 ብር እየተሸጠ ነው።

- አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል።

- አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል።

(ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።)

@tikvahethiopia
#Tigray

ህወሓት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን #ሁሉን_አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት #ኃላፊነቱን_እንዲወጣ ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይና በህዝቡ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም እንዲያደርግ ፤ ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድዱ ፤ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል #ተጠያቂ እንዲሆን እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ህወሓት " በዛሬው መግለጫው ያነሳቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- በተፈረመው #የሰላም_ስምምነት መሰረት ጦርነት እንዲቆም ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እንዲከበር፣ የኤርትራና ሌሎችም ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ህወሓት ፤ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በሰላም ስምምነቱ #እንዳልተደሰቱ ገልጾ ፤ " ወታደሮቹን ያስወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተጨማሪ ክፍሎችን (ኃይሎቹ) ወደ ትግራይ እያመጣ ነው " ብሏል። ይኸው ጦር በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል ሲል ገልጿል።

- የኤርትራ ጦር በሴቶቻችን ላይ ጾታን መሰረት ያደረገ እጅግ አረመኔያዊ ጥቃት እየፈፀመ ፤ ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ፣ የህዝብና የግል ንብረት እየዘረፈ ወደ ኤርትራ እያጓጓዘ ፤ የተረፈውን ደግሞ #እያጠፋ እና እያቃጠለ ነው ፤ የትግራይ ቅርሶችም በከፍተኛ ደረጃ እየወደሙና እየተዘረፉ ነው ፤ በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ) የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

- ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ እና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል #በአስቸኳይ_እንዲያስቆም ፤ ከትግራይ እንዲወጣም እንዲያስገድደው እንዲሁም በትግራይ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን ማደረግ አለበት ብሏል።

- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢሳያስ አፈወርቂ " አምባገነን " ስርዓት ላይ ትክክለኛ ማዕቀብ እንዲጥልና ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን የህወሓት ክስ በተመለከተ ከ "ኤርትራ" በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ጦርነት እንዲያበቃ ፤ ያሉት ችግሮችም #በሰላም እንዲፈቱ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ለተቸገሩት ዜጎች ሁሉ እንዲደርስ ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ በደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ (የስምምነቱ ማስፈፀሚያ ላይ) ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

በናይሮቢ ስምምነት በትግራይ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት የውጭ ኃይሎችን እና ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ኃይሎችን ሁሉ ከክልሉ (ከትግራይ ክልል) ከማስወጣት ጋር #አብሮ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሰብሰባውን ያደረገ ሲሆን ስብሰባውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ባለ 10 ነጥብ ስምምነት ቤተክርስቲያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በመግለጫ አረጋግጣና በሮቿን ክፍት አድርጋ ለሰላም ከፍተኛ ጥረት በምታደርግበት ወቅት ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው…
#የሰላም_ጥሪ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ተከታዩን የሰላም ጥሪ አቅርቧል  ፦

1. ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣

2. ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያኗ ለሀገሪቱ ሰላም ካላት የጸና አቋም አንጻር አሁንም በድጋሚ ለመጨረሻ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት በተደረሱት 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ከዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በጽሑፍ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉና በቤተ ክርስቲያ ቀኖና መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀኖናቸውን ተቀብለው እንዲፈጽሙ፣

3. የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለሰላም ስምምነቱ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቤተ ክርስቲያኗ ምስጋናዋን ያቀረበች ሲሆን በቀጣይ በተደረሰው 10 የስምምነት ነጥቦች መሠረት ሕገ-ወጦቹ ግለሰቦች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ የበኩላቸውን መንግሥታዊ ሚና እንዲወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን በድጋሚ አስተላልፋለች።

4. በተደረሰው ስምምነት መሠረት በሕገ-ወጥ መንገድ አህጉረ ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሰብረው የያዙ ግለሰቦችን በተመለከተ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ተገቢውን የሕግ ማስከበር ሥራ በመሥራት ከቤተ ክርስቲያን ይዞታ በማስወጣት ለቤተ ክርስቲያናኗ ሕጋዊ የሥራ ኃላፊዎች በማስረከብ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእለት ከእለት ተግባርና ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለምንም የጸጥታ ሥጋት እንዲከናወን እንዲሁም በተደረሰው ስምምነት መሠረት እስከአሁን መፈታት ሲገባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎችና ምእመናን እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን አስተላልፋለች።

5. ሃያ አምስቱን ግለሰቦች በሚመለከት ከኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይት ርእሰ መስተዳድሩ በተደረሰው 10ሩ ስምምነት ነጥቦች መሠረት " ሃያ አምስቱንም ግለሰቦች አጠቃልዬ ወደ አዲስ አበባ አመጣቸዋለሁ " በማለት በገቡት ቃል መሠረት በአሁኑ ሰዓት ግለሰቦቹ በክልሉ መንግሥት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ስለተሰማ የክልሉ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት ለፈጸመው አድራጐት ቤተ ክርስቲያኗ ያመሰገናች ሲሆን ያልገቡትን ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተገባው ቃል መሠረት እንዲገቡ እንዲደረግ ቤተክርስቲያኗ ጥሪ አስተላልፋለች።

6. ውግዘቱን በሚመለከት ውግዘቱን የማንሳት ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለመጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጠቃለው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል።

ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77044?single

@tikvahethiopia
#ረመዷን

በመላው ዓለም ላይ የሚታወቁት የዝምባብዌ ዜግነት ያላቸው የእስልምና መሁር ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ስለ ቅዱሱ የረመዷን ወር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በፕሪቶሪያ የተፈረመው #የሰላም_ስምምነት ለዘላቂ ሰላም አስተዋፅኦ ያደርጋል ? ወይስ አያደርግም ? በሚሉት ነጥቦች ክርክር እና ውይይት እንዲደረግ ከ #USAID በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ " ሀበጋር " (የደበበ ኃ/ገብርኤል የህግ ክርክር ፕሮግራም) ባለፈው ቅዳሜ አንድ የውይይት እና ክርክር መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር።

በመድረኩ ላይ የተጋበዙ ምሁራን ፣ የሕግና የፖለቲካ ባለሙያዎች ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች በየፊናቸው ሀሳብ ሲሰጡ ፤ የተለያዩ ጥያቄዎችንም ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል።

የታሪክ ምሁር እና የቀድም #የአብን ብሔራዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም (ዶ/ር) የፕሪቶሪያው ስምምነት " #ዘላቂ ሰላምን አያመጣም " በማለት፣ እንዲሁም የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አበበ ገ/ህይወት " ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም ያመጣል " በማለት ክርክር አድርገዋል።

በአንድ ወገን ያሉት ተሳታፊዎች ስምምነቱ ከነችግሩም ቢሆን ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ስምምነቱ አሳታፊና ግልፅኝት፣ ተጠያቂነት መርሆችን ካላሟላ ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊመያመጣ አይችልም ፣ ቀድሞውንም አሳታፊነት እና ግልጸኝነት የጎደለው ነው በማለት ሀሳባቸውን አቅርበዋል።

በመድረኩ ፦

- የፕሪቶሪያው ስምምነት ዘላቂ ሰላም ያመጣል ? አያመጣም ?
- የተፈናቃዮች ጉዳይ
- የራያ እና ወልቃይት ጉዳይ ተነስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ክርክርና ውይይት መድረኩ የተሳተፉ አካላትም አነጋግሯል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-19
#መልዕክት

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዜዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ፦

" . . . በዓለማችን #የሰላም ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብር እግዚአብሔር በራሱና በሰው ልጆች መካከል፤ እንዲሁም በሰው ልጆች መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶ ሰላምን ለማውረድ ያደረገውን ማሰብ ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ምሳሌነት ለመከተል መወሰንን ይጨምራል፡፡

በተለይም በአሁኑ ጊዜ  በአገራችን የሚታዩት ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ተወግደው ሰላም እንዲሰፍንና አገራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ መላው የአገራችን ሕዝቦችና ሕዝበ ምዕመኑ እንደወትሮው የእግዚአብሔር አምላካችንን ጣልቃ ገብነት ተግተው መለመንና አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች ለሚነሱ  አዳዲስ ግጭቶችም ሆነ ለሰነበቱት አለመግባባቶች ዋነኛ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው #በሰላማዊ_መንገድ  ተቀራርቦ መመካከርና መነጋገር ብቻ እንደሆነና የትጥቅ ፍልሚያ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችል ታምናለች፡፡

የሰው ልጆች አብረው በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ የሰላም ወንጌልን ትሰብካለች፡፡ ከሰላም እጦት የተነሳ የሚፈጠረውን ሞትና እንግልት ትቃወማለች፤ በበኩልዋም ችግሮች ሲፈጠሩ ለእርቅና ለሰላም ጥረቶች የምትጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆንዋንም በየጊዜው ስትገልጽ  ቆይታለች፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱም ራስዋ በየጊዜው በተለያዩ ታጣቂ ኃይላት መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ቀጥታ ተጠቂ የሆነችባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡

ለዚህም በቅርብ ጊዜ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጸሎት ላይ በነበሩ ንጹሐን ምዕመናኖቻችን ላይ  የደረሰው የጅምላ ግድያ በማሳያነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ በጊዜው ድርጊቱን ከመቃወምና ከማውገዝ ባሻገር ሁኔታውን አስመልክቶ ክትትል እንዲደረግና ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ጥሪ ማድረግዋ የሚታወስ ነው፡፡

አያይዛም እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ የትጥቅ ፊልሚያዎችን አቁሞ ለሰላማዊ ምክክር ዕድል መስጠት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነም አስታውሳለች፡፡

አሁንም ይህንኑ ጥሪ ደግማ ደጋግማ ማሰማትዋን ትቀጥላለች፤ ምዕመናንዋንም በዚሁ መስመር በጸሎት በማትጋት ላይ ትገኛለች፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም፤ እርሱ የምህረት ፊቱን ይመልስልናል፤ ሰላሙንም በእርግጥ ይሰጠናል፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረመዷን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፦ " ታላቁ የረመዳን ወር የእዝነት፣ የመተሳሰብ፣ የምህረት ወር በመኾኑ ደካሞችን፣ ችግረኞችን፣ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ወላጅ አልባ ሕጻናትን በመርዳትና ማዕዳችንን በማካፈል በመተሳሰብና አላህን በመለመን ልናሳልፈው ይገባል። የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት…
#ረመዷን

ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል።

@tikvahethiopia
" ከእንግዲህ በሽፍትነት / rebel በመሆን መንግሥትን መጣል አይደለም ፤ መነቅነቅ አይቻልም " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ከእንግዲህ በኃላ በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር መንግስትን መጣል አይደለም መነቅነቅ እንኳን አይቻልም " አሉ።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ይህን ያሉት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ እና ታማኝ ግብር ከፋይ ባለሀብቶችን ሰብሰበው በመከሩበት ወቅት ነው።

ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ለጠ/ ሚኒስትሩ በዛ ያሉ ጥያቄዎችን ያቀረቡላቸው ሲሆን በየአካባቢው ከሚታየው ሁኔታ አንፃር #የሰላም ጉዳይ ከጥያቄዎቹ አንዱ ነበር።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው " ብለዋል።

ሰላምን በተመለከተ ያነሷቸው ሃሳቦች ሁሉ ጥሩ እንደሆነ ገልጸው " ሽማግሌ ነን እድሜያችን ልምዳችን ያላችሁ #ሸምግሉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" እኔ የማረጋግጥላችሁ ግን በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር ከእንግዲህ በኃላ የኢትዮጵያን መንግስት መጣል ሳይሆን መነቅነቅ አይቻልም። በጣም የተለያየን ነን ብቃታችን አይደለም የሚለያየው ያለን conviction ይለያያል እሱ ብር ነው የሚሰበስበው እኛ ስራ ነው የምንሰራውን እናውቃለን እያደረግን ያለነውን በቀላሉ የሚሆን አይመስለኝም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እነሱ ሰዎች ልብ ገዝተው ከመጡ በጣም በጣም በደስታ ነው የምንቀበለው ፤ እናተም ሞክሩ በሁሉም በምትችሉት መንገድ ሞክሩ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ #የሰላም#የአንድነት#የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

መልካም በዓል !

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦትስዋና

" የሀገራችንን የሰላም እሴቶች እናስቀጥል ፤ ... እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋግጥላችኋለሁ " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

ዱማ ቦኮ የቦትስዋና ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ።

ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫው ተሸንፈዋል።

ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል። ፓርቲውን ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ሸንፈትን ተከናብቧል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ በከፍተኛ ብልጫ አሸንፏል።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ፤ ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ቢፈልጉም በሰላማዊ ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለዋል።

በሀገራቸው የዲሞክራሲ ሂደት ግን እጅግ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ገለል ብለው በሽግግሩ ላይ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።

ለተመራጩ ፕሬዜዳንትም ስልክ ደውለውላቸው በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው " እንኳን ደስ አለህ " ብለውታል።

መላው ህዝብም በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም በጋራ የሀገሪቱን #የሰላም እሴቶች እንዲያስቀጥል ፤ እንዲያስከብር ጥሪ አቅበዋል።

እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አረጋግጠዋል።

ሀገሪቱን ለማገልገል ለተሰጣቸው እድልም ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት አመስግነዋል።

ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia