TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመከላከያ_ሠራዊት_ቀን

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከለካያ ሚኒስቴር ከዚህ ዓመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በየዓመቱ " ጥቅምት 15 " ቀን እንዲከበር ወስኗል። ቀኑ " የሠራዊት ቀን " ተብሎ እንዲሰየም ሚኒስቴሩ የተለያዩ ታሪካዊ ኩነቶችን መቃኘቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ የሠራዊት ቀን ሲከበር የመጀመሪያው ነውን ?

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ1950 ዓ.ም ግንቦት 20 የተካሄደው የስፖርት ውድድር በሠራዊታቸው ውስጥ የፈጠረው መነቃቃት አስደስቷቸው ዕለቱ የጦር ኃይሎች ቀን ሆኖ በየ 3 ዓመቱ እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፈዋል።

ከ1966 ዓ/ም በኋላ የጦር ኃይሎች ቀን አንዴ ሲከበር አንዴ ሲቋረጥ ቆይቷል።

ከ1987 ዓ/ም ጀምሮም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት በአዋጅ የተቋቋመበትን ቀን ለማሰብ የካቲት 7 ቀን የሠራዊት ቀን ሆኖ ሲከበር ቆይቷል።

ጥቅምት 15 ለምን ተመረጠ ?

ይኽ ቀን " የሠራዊት ቀን " ሆኖ ሲመረጥ የተለያዩ ታሪካዊ ኩነቶች ከግምት ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደ አንድ የሀገሪቱ ተቋም ሆኖ በሚኒስቴር መስሪያ ቤትነት ደረጃ የተቋቋመበት ጥቅምት 15 ቀን 1900 የሠራዊት ቀን እንዲሆን ውሰኔ ላይ ተደርሷል።

አጼ ምኒሊክ 1900 ካቋቋሟቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አንዱ የጦር ሚኒስቴር ሲሆን ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ በሚኒስትርነት ተሾመውም ነበር።

ንጉሱም ይህንን ዜና በይፋ ለዓለም ሀገራት ማሳወቃቸውን ተከትሎ በአሜሪካና በእንግሊዝ ጋዜጦች ጭምር ታትሞ ወጥቷል።

ዘንድሮ ቀኑ በፖናል ውይይት እንዲሁም በመጽሐፍ ምረቃ ብቻ የሚከበር ሲሆን በቀጣይ "ለማይታወቁ ጀግኖች" እንዲሁም ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት የቀብር ሥፍራ ለማዘጋጀት ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia