TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በርከት ያሉ ዝርፊያ የፈፀሙ ግለሰቦች በሌሉበት #ከሞት ፍርድ እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው ፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

ግለሰቦቹ ከ1 ሚሊዮን 375 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶችን እንደሰረቁ ነው የተነገረው።

ግለሰቦቹ ፦
1ኛ አቤል ኢሳስ ተስፋዬ ዜግነቱ ኤርትራዊ፣
2ኛ አቤል አዋየው አሊ፣
3ኛ አቤል ግደይ በረኸ፣
4ኛ ሀብታሙ ወንድሙ ገብረየስ፣
5ኛ ዳንኤል ጎይቶም ተስፋዬ ዜግነቱ ኤርትራዊ፣
6ኛ ናትናኤል ግደይ በረኸ፣
7ኛ ዳንኤል ዮሐንስ ገ/መድን፣
8ኛ ዮናስ ፍፁም ከበደ፣
9ኛ ናትናኤል ረዳኢ ኪሮስ የተባሉ ዘጠኝ ተከሳሾች በሁለት ክሶች ተከሰዋል።

በ1ኛ ክሳቸው ተከሳሾች ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 9፡30 ሰዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 መሪ 20 ሜትር ጎላጉል አጠና ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ካልተያዙ ግብረ-አበሮቻቸው ጋር በመሆን ፦
* ሽጉጥ፣
* ጩቤ፣
* ገጀራ ይዘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ግቢ በር ገንጥለው በመግባት ተበዳዮችን በማስፈራራት አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 365 ሺ ብር የሚያወጣ የተለያዩ ንብረቶችን ዘርፈዋል የሚል ነው።

ሁለኛው ክሳቸው ከላይ በአንደኛ ክስ በተገለፀው ቀንና ቦታ ከሌላኛው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ የግቢውን የአጥር ሽቦ በከተር ቆርጠው ዘለው በመግባት በማስፈራራት አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው 1 ሚሊዮን 13 ሺ 200 ብር የሚያወጣ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን በመውሰድ ተከሰል።

ግለሰቦቹ ዝርፊያውን ከፈፀሙ በኃላ ከአካባቢው ተሰውረው ፖሊስ ባደረገው ክትትል የተያዙ ሲሆን በፍትህ ሚኒስቴርም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የከባድ ውንብድና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

የክርክር ሂደቱ የታየውም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ነበር።

ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው እንዲያሰሙ ቀጠሮ ቢሰጣቸውም የመከላከያ ምስክር ባለማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ የመከላከል መብታቸው ታልፎ በተከሳሾች ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦
- 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች በሌሉበት #በሞት እንዲቀጡ፣
- 2ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በሌሉበት በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣
- 9ኛ ተከሳሽ በሌለበት በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣
- 3ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች በሌሉበት በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሁም 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች ቀርበው በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

ይህ መረጃ በፍትህ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገፅ ላይ የተመለከቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፦
° አብዛኞቹ ፍርደኞች #አለመያዛቸው ግር እንዳሰኛቸው
° ፍርዱ እስከሞት የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ በዝርዝር እንዳልተብራራላቸው
° በገዘንብ የማይተመን የሰው ነፍስ በአሰቃቂ መንገድ ያጠፉ ፣ ህፃናትን የደፈሩ የተወሰነ አመት ሲፈረድባቸው እዚህ ጋር የተገለፀው ፍርድ እስከ ሞት መሆኑ ደግሞ ለመረዳት እንዳስቸገራቸው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia