TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

አሜሪካ #እንዲያዙ_ለጠቆመ 10,000,000 (አስር ሚሊዮን) ዶላር ወሮታ ሰጣለሁ ያለቻቸው የአልሻባብ የሽብር ቡድን አመራሮች እነማን ናቸው ?

የአሜሪካ መንግሥት ሶስቱን (በፎቶ ያሚታዩትን) የአልሸባብ ቡድን መሪዎች ለመያዝ የሚያግዝ መረጃ ለሚሰጡ ሰዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ወሮታ እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ማሳደጉን አስታውቋል።

የአሜሪካ ዜግነት ያለውን ግለሰብ እና ለላፉት 14 ዓመታት የቡድኑ ከፍተኛ መሪዎች የሆኑትን ሁለቱን ግለሰቦች ጨምሮ አህመድ ድሪዬ፣ ማሃድ ካራቴና ጂሃድ ሙስጠፋ የተባሉትን ሶስቱን ሰዎች ፍለጋ የሶማልያ ዜጎችና በአካባቢው የሚገኙ ሀገሮች እንዲተባበሩ የአሜሪካ መንግሥት ጠይቋል፡፡

ሶስቱ ግለሰቦች በ #ሶማልያ እና #ኬንያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለሞቱባቸው ጥቃቶች በተጠያቂነት የተከሰሱ መሆናቸው ተገልጿል።

በሶማልያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ላሪ አንድሬ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የ10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ከዚህ በፊት ከነበረው ወሮታ #በእጥፍ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ ፤ የሶማልያ መንግሥት ከአልቃይዳጋር ግንኙነት ያለውን አልሻባብን ድል በመንሳት እያደረገ ያለውን ጥረት ማድነቃቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia