TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ኦሮሚያ‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ #አድማሱ_ዳምጠው በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ
ሰጥተዋል።

አቶ አድማሱ በመግለጫቸውም፥ የክልሉ መንግስት ህዝቡን መሰረት አድርጎ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እየሰራ ያለው ስራ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ነው ያሉት።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በተወሰኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ #አሳሳቢ መሆኑን እና በአፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ያለበት መሆኑን የክልሉ መንግስት ይገነዘባል ያሉት አቶ አድማሱ፥ በዚህ ላይም እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ አድማሱ አክለውም፥ የክልሉ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል አቋም እንደሌለው እና ማንኛውንም አካል በመማረክ የማስተዳደር ፍላጎት እንደሌለውም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግስት በኦሮሞ ስም ተደራጅተው ከሚንሰቃቀሱ አካላት ጋር ሰለማዊ በሆነ መንገድ በመወያየት እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አድማሱ፥ ወደ ፊትም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት፣ በመደማመጥና በመከባበር የሚፈታ መሆኑን በመግለጽ፥ የክልሉ መንግስትም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በመመለስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚወያይ መሆኑንም አስታውቀዋል።

አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አሁን እየመጣ ያለውን ለውጥ ጠብቀው በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡም አቶ አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን እጣ ያወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተገነቡ ሆኖ ሳለ በእጣ መተላለፋቸውን እንቃወማለን ያሉ የክልሉ ነዋሪዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሂደዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይም የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል።

የቢሮው ሀላፊው አቶ #አድማሱ_ዳምጠው በሁሉም አካባቢዎች የተካሄዱት ሰልፎች ሰላማዊና የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥባቸው እጣ መውጣቱን የተቃወሙበት ነው ብለዋል።

ይህም የዴሞክራሲ ባህል እየተሻሻለ መምጣቱ ማሳያም ነው ብለዋል። ሰልፎቹ በክልሉ እየተካሄዱ ያሉ የለውጥ ስራዎችን በመቃወም ሳይሆን ከዚህ ቀደም ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የጠየቁ መሆናቸውንም ነው ያመለከቱት።

የክልሉ መንግስትም በኦሮሞ ህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ እንዲሰጣቸው ይሰራል ብለዋል።

 ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ኦሮሚያ እንዲሁም ከኦሮሚያ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ #አድማሱ_ዳምጠው ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉት “የፖለቲካ ጥቅም  በሚሰሩ ጥቂት አሻጥረኞች” በተቀነባበረ  ሴራ ነው። “በምንም ምክንያት ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ማየት አሳዛኝ ነው” ያሉት ሃላፊው የኦሮሚያ ክልል የመኸር እርሻ ከመጀመሩ በፊት ተፈናቃዮቸን ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ለመመለስ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል ብለዋል።
በመሆኑም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ኦሮሚያ ፣ ከጉጂ ዞንወደ ደቡብ ክልል እንዲሁም  ከጌዴኦ ወደ ጉጂ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ይከናወናል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ከፌዴራል እና ከአጎራባች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስታት ጋር ዜጎችን መመለስን በተመለከተ ሰፊ ውይይት አድርጎ መግባት ላይ ተደርሷልም ነው ያሉት።

በክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ  አብዲሳ የሚመራ ልኡክ ከጉጂ ኦሮሚያ የተፈናቀሉ ዜጎችን በሚመከት ከደቡብ ክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑንም አውስተዋል።
ከያዝነው ሳምንት ጀምሮም ተፈናቃዮቹን ወደ ኦሮሚያ የመመለሱ ስራ ይጀመራል ብለዋል።
ክልሉ ተፈናቃዮቹ እስኪቋቋሙ ድረስም የዘር አቅርቦትን ጨምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አረጋግጠዋል።

ዜጎች በሚመለሱበት ጊዜ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንዳይፈጠርባቸው በጸጥታ በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።

በቀጣይም መሰል ችግር እንዳይፈጠር የኢፌዴሪ መንግስት በትኩረት ክትትል እንደሚያደርግ ቃል እንደገባላቸው አውስተዋል።

የኦሮሚያ ክልል  ከሌሎች ክልሎች በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች በጋራ የሚለሙባቸው መሰረተ ልማቶችን  በመገንባት ለዜጎች አብሮነት የበኩሉን እንደሚወጣም አውስተዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia