TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከባቲ- ከሚሴ በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወር የነበረ 880 የክላሽ ጥይት ኮምቦልቻ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ያለለት ዘገዬ ለአብመድ እንደተናሩት ዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ረፋድ ላይ 880 የክላሽ ጥይቶችንና 400 ሺህ ብር የያዘ የባንክ ደብተር ይዞ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ መናኸሪያ ባሉ ተራ አስከባሪዎች እና የትራንስፖርት ባለሙያዎች ተይዞ ለፖሊስ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ደግሞ ግለሰቡ 8 ሺ 150 ብር በካሽ፣ የሞባይል ካርድና ፓስፖርት ይዞ መገኘቱን ተናግረዋል::

በአካባቢው ሰላም የሚያውኩ ድርጊቶች እንዳይፈጠሩ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፀረ ሽምቅ፣ ሚሊሻ እና የአካባቢው ፖሊስ ተሰማርቶ እየጠበቀ እንደሆነም ኮማንደር ያለለት ተናግረዋል፡፡ ወደ አካባቢው የሀገር መካለከያ ሠራዊት እንደገባም ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

አካባቢው #ትልልቅ ድርጅቶች የሚገኙበት በመሆኑም ጥቃት እንዳይደርስባቸው ከወጣቱ እና ከአካባቢው ማኅረሰብ ጋር በመተባበር ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሆነ ነግረውናል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ኮማንደሩ አስታውቀዋል፤ ኮምቦልቻ እና አካባቢዋ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ባይኖርም #ስጋት ለመቅረፍ #መከላከያ በአካባቢው መኖሩን ኮማንደሩ አመልክተዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia