TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቲክቶክ

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት " ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጸደቀ።

አዋጁ የቻይናው #ባይትዳንስ_ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " በስድስት (6) ወራት ውስጥ አክሲዮኖችን #ለአሜሪካውያን ካልሸጠ በመላው አሜሪካ ይታገዳል ብሏል።

ይህ አዋጅ በሴኔቱ ጸድቆ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ካልተፈረመበት ህግ ሆኖ ተፈጻሚ አይሆንም ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ባይደን ግን የህግ መወሰኛ ምክርቤቱ (ሴኔቱ) አዋጁን ካጸደቀው ሳይውሉ ሳያድሩ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩበት ከዚህ ቀደም መግለፃቸው ተነግሯል።

ባይትዳንስ በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጸደቀውን አዋጅ ተፈጻሚ ለማድረግ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ይሁንታ ማግኘት አለበት።

በዓለማቀፍ ደረጃ በወር ውስጥ ከ1 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራው " ቲክቶክ " በአሜሪካም ከ150 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።

መተግበሪያው የግለሰቦችን ምስጢር ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል በሚል በአሜሪካ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል ታግዷል።

በአንዳንድ ግዛቶች ትምህርት ተቋማት እንዲሁ ወጣቶችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እየመራ ነው በሚልም ታግዷል።

አሁን ደግሞ በመላው ሀገሪቲ ቲክቶክ ሊታገድ ይችላል በሚል በቲክቶክ ገንዘብ የሚሰሩ በርካታ አሜሪካውያን የአዋጁን መጽደቅ ተቃውመው አደባባይ መውጣታቸውን አል አይን ኒውስ ሮይተርስ እና ቢቢሲን ዋቢ በማደርግ አስነብቧል።

" ቲክቶክ " ምንም እንኳን አሜሪካ ውስጥ ከቻይና ጋር ተገናኝቶ በይበልጥ ከደህንነት ጋር በተያያዘ እንዲታገድ ግፊት ቢደረግም እንደ ኔፓል፣ ኪርጊስታን በመሳሰሉ ሀገራት ፦
- " የማህበራዊ ህይወትን እያወከ ነው "
- " ለወጣቶች እና ለልጆች አእምሮ ጠንቅ ነው "
- " ጎጂ የሆኑን ከሀገር ባህል እና እምነት ያፈነገጡ ተግባራት ይሰራጩበታል "
- " ሱስ በሚያሲዝ ይዘቱ ወጣቱ ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያደረሰ ነው " በሚሉና በሌሎች ምክንያቶች ታግዷል።

በተቃራኒው የ" ቲክቶክ " መተግበሪያ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ ድርጅት በመረጃና ደህንነር ጉዳይ ከቻይና ጋር ምንም የሚያያዘው ነገር እንደሌለ በተደጋጋሚ የገለጸ ሲሆን እገዳውን የሚቃወሙ በርካታቾች ደግሞ ለወጣቶች እየስራ እድል እየፈጠረ ነው ፤ ብዙ ሰዎች ያለ ብዙ ድካም ተደራሽ እንዲሆኑ እያደረገ ነው ፣ የሰዎችን ህይወት እየለወጠ ነው በሚል እገዳውን ይቃወሙታል።

@tikvahethiopia