TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፦

" ከዓለም ህዝብ ሩብ ያህሉ (2 ቢሊዮን ህዝብ) በጦርነት ቀጠና ውስጥ እየኖረ ነው።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሁከትን የፈጠሩ ከፍተኛ ግጭቶች አሁን ላይ ተስተውለዋል።

በየመን፣ በሶሪያ፣ በሚያንማር፣ በሱዳን፣ ሄይቲና ሳህል ቀጠና ያሉ ጦርነቶች እንዲሁም የቅርብ ጊዜው የዩክሬኑ ጦርነት ዓለም የተገነባበትን ስርዓት የሚሸረሽሩ ናቸው።

እነዚህ ጦርነቶች #በምግብ#በነዳጅ እና #በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲኖር ምክንያት ሆነዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 84 ሚሊየን ሰዎች ጦርነት በፈጠረው ሁከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተደረገው ጦርነትም 4 ሚሊዮን ዜጎችን ከዩክሬን ሲያስወጣ በሀገሪቱ ውስጥ ደግሞ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

በዚህ ዓመት ብቻ 274 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ጨምሯል "

#AlAIN

@tikvahethiopia
#UN

" ሚሊዮኖች በምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ንረት እየተሰቃዩ ነው " - ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በዩክሬን ጦርነቱ በመባባሱ ምክንያት ሚሊየኖች #በምግብ እና #በነዳጅ ዋጋ ንረት ምክንያት እየተሰቃዩ ነው አለ።

- በፋይናንስ፣
- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ
- በአየር ንብረት ለውጥ እየተባባሰ በመጣው ቀውስ ላይ ጦርነቱ ሲጨመርበት በዓለም የኑሮ ውድነት መባባሱን ተመድ ገልጿል።

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ያስከተለውን ጫና እንዲያጠና በተመድ የተሰየመው ቡድን ይፋ ባደረገው መረጃ ጦርነቱ ፦
- የምግብ ዋስትና፣
- የኃይል አቅርቦት እና
- በፋይናንስ ላይ ከባድ እና ፈጣን ተጽዕኖው እየታየ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ጀርመን እና ፖላንድ የምግብ አቅርቦትን ለመደገፍ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችቷል የተባለን እህል ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የሚደረገውን ጥረት ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለዋል።

ከዩክሬን እህል ማውጣት እንዲቻል ለማደራደር ቱርክ ከፍተኛ ሚና እንድትጫወት ይጠበቃል። ሆኖም ቱርክ በጥቁር ባሕር ላይ እህል እንድታጓጉዝ ስምምነት ተደርሷል የሚባለውን ሩሲያ የተሳሳተ መረጃ ነው ብላለች።

ሞስኮ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችቷል የሚባለው እህል መጓጓዝ እንዲችል የበኩሏን ኃላፊነት እንድትወጣ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች።

ሌሎች ሃገራት በነዳጅ እና የምግብ እህል እጥረት እንዲቸገሩ ምክንያት ሆናለች በሚል የሚቀርቡ ክሶችንም ውድቅ ማድረጓን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia