TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Adama ሰላም ሚኒስቴር " የአገር ግንባታ መሠረታዊያን በሚል ርዕስ ለሚዲያ አካላት ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር " ትላንት በአዳማ ከተማ የአንድ ቀን የምክክር መድረክ አካሂዶ ነበር። በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደኣ፣ መሰል የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ለሚስተዋለው ግጭትና አለመግባባት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል…
#ETHIOPIA

" ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ ? " - አቶ ወንድሙ ኢብሳ

" መከላከያ ወንድሞቹን መግደል የለበትም፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም " - አቶ ታዬ ደንደአ


ሰላም ሚኒስቴር ረቡዕ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዳማ ከተማ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ የተጋበዙት ጠበቃና የሕግ አማካሪ አቶ ወንድሙ ኢብሳ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎችም ጋዜጠኞች ፦
° ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ለማምጣት እየሄደበት ያለው ሁኔታ ፣
° ሁለት ጊዜ የከሸፈው የመንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / " ኦነግ ሸኔ " ድርድርን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ሊመጣ የሚችለው ምን ቢደረግ እንደሆነ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተከታዮቹን ምላሾች እንካችሁ ብለዋል።

አቶ ወንድሙ ኢብሳ ስለሰላም ሚኒስቴር ምን አሉ?

* የሰላም ሚኒስቴር ላይ ጥያቄ አለኝ። ለመሆኑ እራሱ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ ? ሰላም ሚኒስቴር በራሱ ጊዜ ሰላምን መስበክ አለበት በስውርም በአደባባይም ፡ አሁን ላይ ሰላም ሚኒስቴር ውስጥ የማያቸው ሰዎች በስውር አማፂያንን ሲደግፉ አያለሁ።

* ለምሳሌ የሁለተኛው የ " ሸኔ " እና የመንግሥት ድርድር ሲደረግ ከሰላም ሚኒስቴር ውስጥ የሆኑ ሰዎች (ስማቸው ከተፃፈ አላውቅም) ከሕውሓት ጋር የተደራደርክ፣ ሰላም የፈጠርክ " ሸኔ " ኦሮሞዎችን ለምንድን ነው እነርሱ የጠየቁትን ጥያቄ በሙሉ መልስ እሺ ያላልከው ? ያሉ አሉ።

* ጥያቄያቸው ደግሞ (የሸኔ) " የሽመልስ አብዲሳ ቦታ ለእኛ ይሰጠን፣ የኦሮሚያ መንግሥት አሁን ያለው ይፍረስና አዲስ ምርጫ ይካሄድ የሚል ነበር። ሰላም ሚኒስቴስ ውስጥ ሆኖ ይህን የሚጠይቅ ሰው ስላለ ሰላም ሚኒስቴር ጤናማ አይመስለኝም።

* አንድ ኢንጅነር ቢመረቅና ሥራ ቢያገኝ ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል። ፖለቲከኛ ግን 'ስንት ሰው ልግደል' ነው የሚለው። በእኔ ምክንያት አንድ። ሰው መሞት የለበትም የሚል ፓርቲ ያስፈልጋል። በፖርቲ ሥም የሚፈጠር ሞትን የኢትዮጵያ ሕዝብ #ማውገዝ አለበት።

የመንግሥትና የሸኔ (ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) ድርድር ዘላቂ መፍትሄው ምንድን ነው ? ለሚለው ጥያቄም፣ መንግሥትና የ " ሸኔ " ድርድር አሁንም መቀጠል አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ተሳታፊ ጋዜጠኞችና ሌሎች ምሁራን በበኩላቸው ፦

° ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሄደበት ባለው ተደጋጋሚ መንገድ ለሰላም ለውጥ ማምጣት ይችላል ወይ ?

° በግጭት ምክንያት
#የሚፈናቀሉ ሰዎችን አሁንም ማስቆም አልቻለም በዚህ ሁኔታ እንዴት ሰላምን መፍጠር ይቻላል ?

° መስሪያ ቤቱ ሰላምን ልማስረፅ ምን እየሰራ ነው ?

° የሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሑፎች ለችግሮችን ይመጥናሉ ወይ ?

° በተጨባጭ መሬት ላይ ያለው ችግር እንዴት ይታያል ?

° በአማራና በኦሮሚያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመፍታት ለምን መግባባት ላይ ማድረስ አልተቻለም ?.... የሚሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል።


የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንድአ ምን ምላሽ ሰጡ ?

- ብዙ ሥራ እየሰራን መጥተናል ገና ብዙ ይቀረናል። ነገር ግን የሚገባንን ሁሉ #ሥልጣን ተሰጥቶናል ብለን አናምንም እንደ ሰላም ሚኒስቴር። አዎንታዊ ሰላም ከማስረፅ አኳያ ትልቅ ስልጣን አለን እየሰራን ነው። የሰላም ችግር ሲፈጠር፣ #ሰው ሲፈናቀል ያንን የማስቆም ስልጣን ግን ለእኛ አልተሰጠንም። ይሄ #የአወቃቀር ችግር ነው።

- የአደጋ ሥጋት እንኳ #ለእኛ አይደለም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ነው። #ፓሊስ ለእኛ ተጠሪ አይደለም። መሆን የነበረበት እዚህ ነው። #የግጭት ሥጋት ሲኖር የምናዘው አንድም #ሚሊሻ የለንም። ስለዚህም ለሚፈጠሩ ግጭቶች የሰላም ሚኒስቴር #ሊወቀስ_አይገባም

- ትክክል ነው በተመሳሳይ አይነት ሥራ የተለየ ውጤት አይፈጠርም። በእኛ በኩል ግን ተመሳሳይ ሥራ እየሰራን ነው ብለን አናምንም። 

- ጥናታዊ ፅሑፎች እና በመሬት ላይ ያለውን ችግር በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ፣ የስልጣን፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትህ ችግሮች አሉብን። ሥልጣን ካልተገደበ፣ ተጠያቂነት ካልተረጋገጠ፣ ኢኮኖሚው በፍትሃዊነት ካልተሰራጨ፣ ሌቦች ከተቆጣጠሩት…ሰላም ሊመጣ አይችልም።

- የተሰጠን ስልጣን ወቅታዊ ችግር መፍታት ሳይሆን ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ነው። 

- ተጠያቂነትን መስፈን አለበት። ከተጠያቂነት አኳያ ደግሞ ሥልጣን የተሰጣቸው አሉ። ለምሳሌ የፍትህ ሚኒስቴሩ ሥራው ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ መሆን ነበረበት #ድርድር ከመሄድ ይልቅ።

- ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ አዎ ሰላም ነው። ሰላም የማንሆንበት ምክንያት የለንም። እኛ እያደረግን ያለነው የአገር አንድነት እንዲጠናከር፣ ሰላም እንዲሰፍን ተባብረን እየሰራን ነው።

- በኦሮሚያ ክልል ለ5 ዓመታት ጦርነት እየተካሄደ በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው ችግር አለ። የትግራይ ክልሉም በጣም ይጸጽተናል። ግን ይህንን የሚያደርገው ከጀርባ ያለው ማነው? እሱን ነው ማወቅ የሚያስፈልገው።

- መከላከያ ሰራዊት ወንድሞቹን መግደል የለበትም፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም። ከብሔርተኝነት አኳያ ኦሮሞም ፣ አማራም ፣ ትግራይም በጣም አስቸጋሪ ችግር ነው ያለው። ለአማራ ችግር ኮዙ ኦሮሞ ነው፣ ለትግራይ አማራ ነው ተብሎ ይወሰዳል። ግን ችግሩ በእውነት ምንድን ነው ? ከዚያ ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው? ይህንን ሚዲያዎች ለሕዝብ ማስገንዘብ አለባቸው ብለዋል።

ጥንቅሩ በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia