TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ በሕገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ለማስተላለፍ ታስቧል፡፡

በመዲናዋ የመሬት፣ የቀበሌ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ሕንፃዎችን የኦዲት ስራም ተጀምሯል፡፡

ምክትል ክንቲባ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የቆጠራ ስራውን #ለማወክ ጥረት የሚያደርጉ መኖራቸውን አስታውሰው ሕብረተሰቡ በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሬትና ቤቶችን ጥቆማ ካለው ለአስተዳደሩ ያድርስ ብለዋል፡፡

የመዲናዋን ሰላም #ለማደፍረስ ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን ምልክቶች መታየታቸውንና ህብረተሰቡ በንቃት ከአስተዳደሩ ጋር እንዲቆም
ጥሪ አቅርበዋል፡፡

©ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ‼️

በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳሰበ፡፡

በድሬድዋ ከተማ ግጭት የተፈጠረው ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የጥምቀት ማግስት የቃና-ዘገሊላ በዓልን በሚያከብሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች በፈጠሩት ረብሻ ሳቢያ ነው፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን በስልክ ለአብመድ እንደተናገሩት በዕለቱ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ችግር በሁለት እና ሦስት ቀናት ወደ ተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ተስፋፍቷል፡፡

‹‹ሃይማኖታዊ በዓሉን በመረበሽ የድሬዳዋ ከተማን አንድነት መሸርሸር እና አገራዊ ሰላምን ለማደፍረስ ታስቦ የተሠራ ነው›› ብለዋል ከንቲባው፡፡ ግጭቱን ሃይማኖታዊ መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ፀብ የማጫር ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ አካላት መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡ ከክብረ በዓሉ ቀደም ብለው ጭምር ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበርም ነው አቶ ኢብራሂም የጠቆሙት፡፡

ቀደም ብሎ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግም ሌላ የግጭት አጀንዳ እንደተነደፈ አስታውቀዋል፡፡ እንደ ከንቲባው ገለጻ ችግሩን የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የጎሳ እና የፖለቲካ መልክ ለማስያዝ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡

ሰላም በመደፍረሱ ምክንያት የዝርፊያ ወንጀሎች እየተባባሱ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

በተለይ ወደ ባንኮች ተደራጂቶ የመሄድ አዝማሚያ መኖሩን፣ መንገድ የመዝጋት፣ የግለሰቦች ቤትና ንብረት የማውደም እና የተወሰኑ የመንግሥት ተቋማት ላይ ጉዳት የማድረስ ሁኔታዎች በከተማዋ መስተዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡

የከተማዋን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ‹‹ለዚህም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ ነው፡፡ ከግጭቱ ጀርባ ስውር አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ከ80 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ለሕግ የማቅረብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ነው ያሉት ከንቲባው፡፡

‹‹ችግሩ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ #የመከላከያ_ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊሶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል›› ያሉት ከንቲባው ዛሬ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አስታውቀዋል፡፡

‹‹አንድ ስፍራ ብቻ አሁንም ችግሩ አለ፤ የፀጥታ ኃይሎች ሰላም ለማስከበር ወደ ስፍራው አቅንተው ሰላም የማስከበር ሥራ እየሠሩ ነው›› ብለዋል አቶ ኢብራሂም፡፡

ድርጊቱ የድሬዳዋን ሕዝብ የዘመናት አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡

በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው #የሀሰት_ወሬ የድሬድዋን ከተማ ብቻም ሳይሆን የሀገሪቱን ሰላም #ለማደፍረስ እንደ ቤንዚን የሚጠቀሙ ስውር የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው አካላት በመኖራቸው መጠንቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia