TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህጻናት እና የአእምሮ ህሙሟን ጨምሮ በርካቶች በግዳጅ ተይዘው እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል። ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎችን ከሕግ ውጪ የያዙ እና ገንዘብ እንዲከፍሉ ያስገደዱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ላይ የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳውቋል።   በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ…
🔈 በሻሸመኔ ከተማ ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል እና ምርመራ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የገለጹ ሕፃናት " ወታደራዊ ስልጠና ትገባላችሁ " በሚል ወደ ማቆያ አዳራሾች እንዲገቡ መደረጋቸውን አረጋግጧል።

በሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በማቆያ አዳራሽ ከነበሩ እና ኢሰመኮ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን የገለጹ ሲሆን አንድ ሕፃን ደግሞ ዕድሜው 11 ዓመት መሆኑን ገልጿል።

ከት/ቤት ሲወጡ #ከነዩኒፎርማቸው ፤ ሀሌሉ ወረዳ ወደ ሚገኘው ማቆያ አዳራሽ እንዲገቡ የተደረጉ የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ ሁለት የ15 ዓመት ሕፃናት ወደ አዳራሽ ከገቡ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው ገልጸው የገቡበትን ሁኔታም አስረድተዋል።

ሕፃናቱ ፤ “ ከትምህርት ቤት ስንመለስ መከላከያ ለሚገቡ 25,000 ብር ይሰጣል ብሎ አንድ ግለሰብ በባጃጅ አሳፈረን፤ ከዚያ 010 ቀበሌ (ሀሌሉ ወረዳ) ወደ ሚገኘው አዳራሽ ገባን፤ ነገር ግን ከገባን በኋላ መውጣት አልቻልንም  ” ሲሉ ነው የገለጹት።

በጅማ ከተማ ኢሰመኮ ያነጋገረው የ14 ዓመት ሕፃን ስለተያዘበት ሁኔታ ሲያስረዳ፦

“ ኅዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ ቤት እየሄድኩ እያለሁ መንገድ ላይ ቆመው የነበሩ ሚሊሻዎች ባትሪ አብርተውብኝ አስቆሙኝ፤ መታወቂያ ሲጠይቁኝ ዕድሜዬ ገና 14 ዓመት ነው፤ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ መታወቂያ የለኝም ብዬ ስመልስ፣ ቀበሌ ሄደህ ጉዳይህ ይጣራል በማለት ወደ ቀበሌ ወስደው ብዛታቸው ከ20 በላይ ከሚሆኑ ወጣቶች መካከል ቀላቅለውኝ ሄዱ። ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት መያዜንም ወጣቶቹ ናቸው የነገሩኝ። በማግስቱ በድብቅ ለቤተሰቦቼ ደውዬ ካሳወቅኩ በኋላ ለመውጣት ችያለሁ ” ብሏል።

#EHRC #OROMIA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM