TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Bitcoin

" በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " - ትራምፕ (በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት)

የዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆኖ መመረጥ ለክሪፕቶ ማህበረሰቡ ትልቅ ብስራት ነው የሆነው።

ትራምፕ መመረጣቸው ከተሰማ በኃላ ቢትኮይን ታይቶ ባይታወቅ እና በማይታመን ሁኔታ ጨምሯል።

ዛሬ ላይ አንድ ቢትኮይን ከ91,000 ዶላር በላይ ገብቷል።

ልክ ትራምፕ ሲመረጡ በክሪፕቶ ማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ደስታ የተፈጠረ ሲሆን " የመጀመሪያው የክሪፕቶ ፕሬዝዳንት ተመረጠ " ነው የተባለው።

ትራምፕ የመጀመሪያው በይፋ ቢትኮይን እና ክሪፕቶከረንሲ የሚደግፉ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ተመራጩ ፕሬዝደንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት " አሜሪካን የፕላኔታችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ለዲጂታል መገበያያዎች የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል። ይህን ተከትሎ በክሪፕቶ ኢንዱስትሪ ላይ የተጣለው ቁጥጥር ይላላል የሚል እምነት አለ።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " ሲሉ ተናግረው ነበር።

የዓለማችን ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይት ከትራምፕ መመረጥ በኃላ በማይታመን ሁኔታ ጨምሮ ዛሬ ላይ ከ91,000 (ዘጠና አንድ ሺህ) ዶላር በላይ ሆኗል።

ሌሎች እንደ ዶጅኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችም ዋጋቸው ከፍ እያለ ነው። የዶናልድ ትራምፕ ቀኝ እጅ የሆነው ኢላን መስክ ዶጅኮይን በስፋት ያስተዋውቃል።

ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው ?

ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን " የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ " ይለዋል።

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ።

በስፋት ከሚታወቁት መካከል ፦
- ቢትኮይን፣
- ኤቴሪያም፣
- ሪፕል እና ቢትኮይን ካሽ የሚባሉት ከበርካታ ክሪፕቶካረንሲዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል + ገንዘብ + መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል።

ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የወረቀት ገንዘብ ወይም ሳንቲም ሳይሆን በበይነ መረብ ላይ የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው።

ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው።

ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች አማካኝነት ቁጥጥር ይደረግበታል።

ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጠ/ጡ ይታመናል።

የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን ከ17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል ተብሎ ይታመናል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

#USA #Bitcoin #BBC #Mario #Crypto

@tikvahethiopia