TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል።

#ከዓለም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲሁም #ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀችው።

በዓለም ሻምፒዮናው 4 ወርቆችን ያገኘን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

ከተገኙት አራት #ወርቆች 🥇 መካከል ታምራት ቶላ በማራቶን ያገኘው ወርቅ በዓለም ሻምፒዮናው በወንዶች የተገኘው #ብቸኛው ወርቅ ነው።

ለሀገራቸው ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶቻችን እነማን ናቸው ?

ወርቅ 🥇

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ጎተይቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 ታምራት ቶላ

ብር🥈

🇪🇹 ወርቅውሀ ጌታቸው
🇪🇹 ሞስነት ገረመው
🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ

ነሐስ🥉

🇪🇹 ዳዊት ስዩም
🇪🇹 መቅደስ አበበ

አጠቃላይ ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች ውድድር የተገኘ ነው።

የዓለም ሻምፒዮናው ምንም እንኳን ከፍተኛው ድል የተመዘገበበት ቢሆንም በወንዶች ውድድሮች ላይ የተሻለ መስራት እንደሚጠይቅ የሚጠቁም ነው።

የአትሌቲክስ ቡድናችን ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና ፣ የክብር አቀባበል እንደሚደረግለት ይጠበቃል።

ውድ አትሌቶቻችን ፤ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ላስመዘገባችሁት ድል ፣ የሀገራችሁን ህዝብ ክብር ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኃል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia @tikvahethsport
#USA #Election

" ስደተኞች የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ

ሪፐብሊካንን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች " የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " በማለት ተናገሩ።

ትራምፕ ይህ ያሉት #ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት " ኒው ሃምሻየር " ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው።

ትራምፕ ለ4 አመት የስልጣን ዘመን በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ህገወጥ ስደትን እንደሚያስቆሙ እና በህጋዊ ሰደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።

ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ በተጨማሪ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

" ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው መስከረም ወር " ናሽናል ፐልስ " ከተባለው የቀኝ ዘመም ዌብሳይት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስደተኞች " ደማችንን እየበከሉት ነው " የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በወቅቱ ይህ የትራምፕ ንግግር " ዘረኝነት እና ጥላቻ " የሚያንጸባርቅ ነው የሚል ትችት አስነስቶ ነበር።

የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን አሁንም ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል።

ፕሮሬሰሩ እንደተናገሩት ትራምፕ " የጀርመኖች ደም በጅዊሾች እየተበከለ ነው " የሚለውን የሂትለር ንግግር ያስተጋባ ነው ሲሉ ተችተውታል።

ስታሊ" ትራሞፕ ይህ ቃል በሁሉም የድጋፍ ሰልፎች ላይ እየደገሙት ነው። አደገኛ  የሆኑ ንግግሮችን መደጋገም እንዲለመዱ ያደረጋል " ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ እንደተናገሩት ይህ በአሜሪካ የሚኖሩ ስደተኞችን ስጋት ላይ እንዲወድቁ ያደርጋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቴቨን ቹንግ እንዲህ አይነት ቃላት በመጽሀፍ፣ በዜና እና በቴሌቪዥን የተለመድ ናቸው በማለት በትራምፕ የቀረበውን ትችት " ትርጉም የለሽ " ሲሉ አጣጥለውት ነበር።

Credit - AL AIN News

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Rwanda #UK ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል። የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና…
" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ

ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች።

የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ ሕግ ትላንት አጽድቋል።

ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ፥ " በቀጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን " ብለዋል።

ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል።

52,000 ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሩዋንዳ ይዘዋወራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቅርብ አመታት ፦
- #ከአፍሪካ
- ከመካከለኛው ምስራቅ
- ከኢስያ ጦርነት እና ድህነት የሚሸሹ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል።

እነኚህ ስደተኞች በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በትንንሽ ጀልባዎች ተጉዘው ነው ዩናይትድ ኪንግደም የሚገቡት። #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አስደናቂ ድል ተቀዳጅቻለሁ " - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ " አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ " አሉ። የሪፐብሊካኑ ዕጩ ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው የተናገሩት በፍሎሪዳ በተካሄደ መድረክ ነው። ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን እንደሚሆን ተናግረዋል። " ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል " ብለዋል። በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል…
#USA

ስደተኞች በትራምፕ የስልጣን ዘመን ምን ይገጥማቸው ይሆን ?

ከዚህ ቀደም በምርጫ ዘመቻ ወቅት ዶላንድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በስደተኞች ጉዳይ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር።

ትራምፕ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ነበር ያሉት።

ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

" ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው።

በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁንም ፕሬዜዳንት ሲሆኑ እንደሚያጠናክሩት ነው በዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ቃል የገቡት።

ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ነው የሚባለው።

ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር ግን እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ በተጨማሪም በዘመቻቸው ወቅት ፥ ለ4 አመት በስልጣን ሲቆዩ ህገወጥ ስደትን ከማስቆም ባለፈ በህጋዊ ስደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ ፥ " ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ ፣ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ፤ ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

ስደተኞችን " #የሀገራችንን_ደም_እየበከሉ_ነው " በማለት ተናግረውም ብዙዎችን አስቆጥተው ነበር።

በስደተኞች ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።

#TikvahEthiopia
#USA #deport

@tikvahethiopia