TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቪዬሽን #ኢትዮጵያ

🔴 “ ድርጅታችንን እስከመዝጋት የሚያደርስ ኢፍትሃዊ ችግሮችን ተጋፍጠን ያለንበት ሁኔታ አለ ” - ካፒቴን ሰለሞን ግዛው

🔵 “ ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ የተሻለ ፓሊሲ እየቀረጸ ይገኛል ” - አለሙ ስሜ (ዶ/ር)


አቢሲኒያን የበረራ አገልግሎት አቬዬሽን አካዳሚ የፓይለት ማሰልጠኛ የግል ድርጅት ዛሬ የ25ኛ ዓመት የብር እዩበልዩ በዓሉን በስካይ ላይት ሆቴል አክብሯል።

በዓሉን ባከበረበት ወቅትም በዘርፉ ያሰለጠናቸውን ፓይለቶችን አስመርቋል።

የበረራ ትምህርት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ሰለሞን ግዛው፣ የአቬሽኑ ዘርፉ መንግስት ልዩ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል።

እንደ አቢሲኒያን ድርጅት በአቬሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ሥራ መስራት እንዲቻል በፓሊሲ የተደገፈና የማያሻማ ሁለንተናዊ ድጋፍ በመንግስት በኩል ሊደረግላቸው እንደሚገባ ነው የገለጹት።

ድርጅቱ ድጋፍ በማጣቱ እየሰራ ያለው 20 በመቶ ብቻ እንደሆነም በግልጽ ተናግረዋል።

“ በተለይም በከፍተኛ ካፒታል፣ ወጪ፣ ኢንሹራንስ የአቬሽን ዘርፍ ትልቅ ጫና እየተደረገበት ስለሆነ መንግስት የአቬሽን ዘርፉን ልዩ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ ድጋፍ ሊያደርግልን ይገባል ” ነው ያሉት።

“ ድርጅታችንን እስከመዝጋት የሚያደርስ ኢፍትሃዊ ችግሮችን ተጋፍጠን ያለንበት ሁኔታ አለ ” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ “ የአቬሽን እንቅስቃሴ ድርግም ከማለቱ በፊት መንግስት በባለጉዳይነት እንዲታደገን እጠይቃለሁ ” ብለዋል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ ለዘርፉ “ የግሉ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው። መንግስትም ይህንን ስለተመለከተ ነው ለባለሃብቶች ዘርፉን ክፍት ያደረገው ” ሲሉ ተደምጠዋል።

“ የግሉ ሴክተር በአየር ትራንስፓርት መሳተፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ካመደገፍ አንጻር የማይተካ ሚና አለው ” ብለዋል።

“ ካፒቴኑ የገለጿቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ተግዳሮቶቹ ተጠንተው ውይይት እየተደረገባቸው ነው። መንግስት የሚጠበቅበትን ሚና የሚጫወት መሆኑን እገልጻለሁ ” ሲሉ ካፒቴን ሰለሞን ለጠቀሷቸው የዘርፉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ፣ “ ጥቂት የግል ሴክተሮች በዘርፉ ቢሳተፉም በተለይ አቢሲኒያን ፍላይት የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ከመስጠቱ አንጻር እጅግ ሊመሰገን ይገባል ” ብለዋል።

“ ግን ከኢትዮጵያ ስፋት፣ ሕዝብ ብዛት፣ ኢኮኖሚ አንጻር አሁን ያለን የበረራ አገልግሎት ኦፕሬተሮች ብዛት በቂ አይደለም። ያሉትም ራሳቸውን ማሳደግ፣ ማስፋፋት አለባቸው። አዳዲስ ኦፕሬተሮችም ወደ ዘርፉ መግባት አለባቸው ” ነው ያሉት።

መንግስት ዘርፉ ለግል ባለሃብቶች ምቹ እንዲሆን እንቅፋቶች እንዲቀረፉ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ “ ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ የተሻለ ፓሊሲ እየቀረጸ ይገኛል ” ብለዋል።

ተግዳሮቶቹንም ጥናት አጥንቶ ጨርሶ ውይይት እየተደረገበት ስለመሆኑ አስረድተው፣ ዘርፉ ገና ያልተየካ የኢንቨስትመንት ዘርፉ በመሆኑ አቅሙና እውቀቱ ያላቸው የግል ባለሃብቶች ኢንቨስት ኢንዲያደርጉ ማኒስትሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopiaFamyAA

@tikvahethiopia