TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መካሄድ እንደሚጀምር ተገልጿል።

አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው ከቀናት በፊት በወሊሶ አካባቢ በብፁዕ አባ ሳዊሮስ መሪነት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ " የኤጲስ ቆጶሳት " ሢመትን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሠረት የሚካሄድ ነው።

በብፁዕነታቸው ጥሪ መሰረት ከእሁድ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እየገቡ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት አመሻሽ ላይ ይጀመራል ተብሏል።

#TMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቀናት በፊት ስምምነት ላይ የደረሱት አባቶች ስምምነቱን እንዲሁም ቀኖናውን ደግመው መጣሳቸውን አሳወቀች።

ይህንን በተመለከተ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ፅህፈት ቤት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተከታዩን ብለዋል ፦

" ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል።

በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ነው።

ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ' #አዲሱ_ሲኖዶስ ' በሚል አዲስ ስም እስካሁን ድረስ ከሚጠቀሙበት ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የ #ኤጲስ_ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስ እና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል። 

ሀይማኖቱን ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል።

ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል።

ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል።

ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል።

በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ።

አስተሳሰባቸው አነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል።

25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል።

ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይህንን አድርገው ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ ቤታቸው ውስጥ [ቤተ ክህነት] ገብተዋል።

... ቤተ ክርስቲያንም እስቲ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት እንየው በማለት ዝም ብለን እየተመለከትን ነው።

ስለዚህ ሕግን የጣሰ ሰው ስምምነትን ያፈረሰ ሰው ዛሬም ደግመው ደጋግመው እውነት ለማስመሰል ሐሰትን በሚለፍፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚመለከተው አካል ሊመለከተውና አሁንም በቃ ሊለው ይገባል ብለን መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"

#TMC

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ " አልታወቁም " በተባሉ የታጣቂ ኃይሎች በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ፤ በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መቃጠሉን የተዋሕዶ ሚዲያ አገልግሎት አሳውቋል።

" ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች  " ተፈፅሟል የተባለው ይህ የመቃጠል ተግባር ትናንት ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ መፈፀሙ ተመላክቷል።

" በቦታው ላይ የተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ ቆይቷል " ያለው ዘገባው ትላንንት ሙሉ በሙሉ ንዋዬ ቅድሳቱ የተቃጠለ ሲሆን የቤተ መቅደሱ የውስጥና የውጭ ክፍል ጉዳት ያደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ መድረሱ ተገልጿል።

ጉዳዩ ላይ ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።

#TMC

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሕንፃ እድሳት ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል ተብሏል።

ካቴድራሉ እድሳት እየተደረገለት ከሁለት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን ከ1 ወር በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል።

ለካቴድራሉ እድሳት እስካሁን 124,827,576 ብር የወጣ ሲሆን ያልተከፈለ 47 ሚሊዮን 672 ሺህ ብር ያለበት በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገረ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ቀሪ ክፍያውን ለማጠናቀቅ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የቀጥታ ስርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር እንዲሁም ታኅሣሥ 27 ቀን በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ልዩ የምስጋና መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

የካቴድራል የዕድሳት እና የጥገና ሥራ ከተጀመረ 773 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን በየጊዜው በገጠመው የሲሚንቶ ችግር እና ሌሎችም ምክንያቶች ተጨማሪ 225 ቀናት መውሰዱን ተጠቁሟል።

#TMC

@tikvahethiopia