TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #USA

አሜሪካ በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን " የርስ በርስ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው " ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ይህንን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት እንደሆነ ተነግሯል።

ብሊንከን "በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችን ጨምሮ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ " በፕሪቶሪያው ስምምነት እና አፈጻጸሙ ዙሪያ " መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት የሀገራቸው እገዛ እንደማይለያት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊነክን በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና እየተባባሰ ነው ያሉት ውጥረት እንዲረግብም በዚሁ ጊዜ መጠየቃቸውን ተዘግቧል።

#AFP #DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከወዲሁ ለትራምፕ የደስት መልዕክት ከላኩት ውስጥ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አንዱ ሆነዋል። ኔታንያሁ ትራምፕ ምርጫውን እንዳሸነፉ ባመላከቱበት የደስታ መልዕክት " ይህ ትልቅ ድል ነው " ብለውታል። የትራምፕን ወደ ዋይትሃውስ መመለስን " ታራካዊ " ሲሉ ገልጸውታል። " ለአሜሪካ አዲስ ጅምርና በእስራኤል እና በአሜሪካ መካከል ላለው ታላቅ ህብረት ዳግም ጠንካራ የሆነ ቁርጠኝነትን…
#ETHIOPIA #USA

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ " የእንኳን ደስ አለዎት " መልዕክት አስተላለፉ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን እና ዳግም ወደ ፕሬዜዳንት ስልጣን መመለሳቸውን ባለመላከተው የደስታ መልዕክታቸው " የእንኳን ደስ አለዎት !! " ብለዋል።

በስልጣን ዘመናቸእ የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አስደናቂ ድል ተቀዳጅቻለሁ " - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ " አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ " አሉ። የሪፐብሊካኑ ዕጩ ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው የተናገሩት በፍሎሪዳ በተካሄደ መድረክ ነው። ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን እንደሚሆን ተናግረዋል። " ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል " ብለዋል። በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል…
#USA

ስደተኞች በትራምፕ የስልጣን ዘመን ምን ይገጥማቸው ይሆን ?

ከዚህ ቀደም በምርጫ ዘመቻ ወቅት ዶላንድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በስደተኞች ጉዳይ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር።

ትራምፕ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ነበር ያሉት።

ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

" ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው።

በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁንም ፕሬዜዳንት ሲሆኑ እንደሚያጠናክሩት ነው በዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ቃል የገቡት።

ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ነው የሚባለው።

ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር ግን እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ በተጨማሪም በዘመቻቸው ወቅት ፥ ለ4 አመት በስልጣን ሲቆዩ ህገወጥ ስደትን ከማስቆም ባለፈ በህጋዊ ስደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ ፥ " ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ ፣ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ፤ ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

ስደተኞችን " #የሀገራችንን_ደም_እየበከሉ_ነው " በማለት ተናግረውም ብዙዎችን አስቆጥተው ነበር።

በስደተኞች ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።

#TikvahEthiopia
#USA #deport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው " ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ' ትዕዛዝ ' እንዲሰጡ ያስችላቸዋል " ብለዋል።

ይህም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት / በገፍ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ (ማስ ዲፖርቴሽን) እንደሆነ ጠቁመዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ይህ ሰነድ አልባዎችን በብዛት ከአሜሪካ የማስወጣቱ /ማስ ዲፖርቴሽን/ ተግባር የትራምፕ የመጀመሪያው ቀን ስራ ይሆናል ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በሚመለከት " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

#TikvahEthiopia
#USA #massdeportation

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል። የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው። ሌቪት ፥ ትራምፕ…
#USA #MASS_DEPORTATION

ትራምፕ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎችን ከአሜሪካ ለማስወጣት ምን ያህል በጀት ያስፈልጋቸው ይሆን ?

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልክ በፕሬዜዳንትነት ስራ ሲጀምሩ የመጀመሪያ ስራቸው ይሆናል የተባለው በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎችን ከሀገር ማስወጣት / የዲፖርቴሽን ስራ ነው።

ይህ ግዙፍ የተባለ ዲፖርቴሽን በቢሊዮን ዶላሮችን ሊጠይቅ ይችላል።

እሳቸው ግን ይህ የዲፖርቴሽን ጉዳይ " ምንም ዋጋ የሚወጣለት / ዋጋ የሚለጠፍለት አይደለም " ብለዋል።

ከአሁን በኃላ የአሜሪካ ድንበሮች እጅግ ጠንካራ ደህንነት ያለባቸው ኃይለኛ ድንበሮች እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

" እውነት ለመናገር ምንም ምርጫ የለንም " ያሉት ትራምፕ ፤ በሀገሪቱ ሰዎች እየተገደሉ እና የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪ ጌቶች ሀገሪቱን እያወደሙ የሚኖሩበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።

" አሁን እነዚህ ሰዎች እዚህ አይቆዩም ፤ እንዲቆዩም አይደረግም ወደነዛ ሀገራት ይመለሳሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

ለዚህ ደግሞ ምንም ዋጋ የሚለጠፍለት እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎችን ለማስወጣት የገቡትን ቃል እንደሚተገብሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

" በቀላል መመሪያ ነው የማስተዳድረው " ያሉት ትራምፕ " የገባሁትን ቃልኪዳን አክብራለሁ አስፈጽማለሁ " ብለዋል።

እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያስፈጽሙት ባይታወቅም ትራምፕ ከ11 ሚሊዮን እስከ 21 ሚሊዮን ሰዎችን ከአሜሪካ ሊያስወጡ እንደሚችሉ ተነግሯል።

ትክክለኛ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ አይታወቅም። ምናልባትም አሁን ከሚባለው 21 ሚሊዮን ሊያንስ እንደሚችል ነው የሚነገረው።

' ፒው ሪሰርች ሴንተር ' 2021 ላይ ይፋ ባደረገው ዳታ 10.5 ሚሊዮን ዶክመንት የሌላቸው ሰዎች አሜሪካ ውስጥ አሉ።

#USA #NBC #TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Bitcoin

" በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " - ትራምፕ (በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት)

የዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆኖ መመረጥ ለክሪፕቶ ማህበረሰቡ ትልቅ ብስራት ነው የሆነው።

ትራምፕ መመረጣቸው ከተሰማ በኃላ ቢትኮይን ታይቶ ባይታወቅ እና በማይታመን ሁኔታ ጨምሯል።

ዛሬ ላይ አንድ ቢትኮይን ከ91,000 ዶላር በላይ ገብቷል።

ልክ ትራምፕ ሲመረጡ በክሪፕቶ ማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ደስታ የተፈጠረ ሲሆን " የመጀመሪያው የክሪፕቶ ፕሬዝዳንት ተመረጠ " ነው የተባለው።

ትራምፕ የመጀመሪያው በይፋ ቢትኮይን እና ክሪፕቶከረንሲ የሚደግፉ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ተመራጩ ፕሬዝደንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት " አሜሪካን የፕላኔታችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ለዲጂታል መገበያያዎች የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል። ይህን ተከትሎ በክሪፕቶ ኢንዱስትሪ ላይ የተጣለው ቁጥጥር ይላላል የሚል እምነት አለ።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " ሲሉ ተናግረው ነበር።

የዓለማችን ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይት ከትራምፕ መመረጥ በኃላ በማይታመን ሁኔታ ጨምሮ ዛሬ ላይ ከ91,000 (ዘጠና አንድ ሺህ) ዶላር በላይ ሆኗል።

ሌሎች እንደ ዶጅኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችም ዋጋቸው ከፍ እያለ ነው። የዶናልድ ትራምፕ ቀኝ እጅ የሆነው ኢላን መስክ ዶጅኮይን በስፋት ያስተዋውቃል።

ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው ?

ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን " የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ " ይለዋል።

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ።

በስፋት ከሚታወቁት መካከል ፦
- ቢትኮይን፣
- ኤቴሪያም፣
- ሪፕል እና ቢትኮይን ካሽ የሚባሉት ከበርካታ ክሪፕቶካረንሲዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል + ገንዘብ + መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል።

ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የወረቀት ገንዘብ ወይም ሳንቲም ሳይሆን በበይነ መረብ ላይ የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው።

ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው።

ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች አማካኝነት ቁጥጥር ይደረግበታል።

ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጠ/ጡ ይታመናል።

የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን ከ17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል ተብሎ ይታመናል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

#USA #Bitcoin #BBC #Mario #Crypto

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA

የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋን ጨምሮ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ሚኒስትር ስፔራ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ፀሀፊ ፋሬል እና ሌሎችም የተካተቱበት ልዑክ ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ጋር መክረዋል።

በወቅቱም ኢንጂነር አይሻ ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ላላት የረዥም ጊዜ ወታደራዊ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እንደገለጹና ይህንኑ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳለት መናገራቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለው ከሆነ ደግሞ በምክክሩ ላይ #በአማራ እና #ኦሮሚያ ያለው ግጭት ጉዳይ ተነስቷል።

ሌላው የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም ስለሚደረገው ስራ (DDR) ውይይት ተደርጓል።

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር በማጠናከር ላይም ትኩርት ያደረገ ምክክር መደረጉን ከኤምባሲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

#USA #USEmbassy

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

" እውነት ነው " - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን በገፍ በጅምላ ከሀገር ለማባረር ጦሩን (መከላከያውን) ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሏል።

ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፤ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው በገቡት ቃል መሰረት ሰነድ የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደየመጡበት ሀገር ያባርራሉ።

ለዚህም በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ እንደሚችሉ እንዲሁም ስደተኞቹን ለማባረር የአሜሪካን ጦር ሃብት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ተነግሯል።

የጁዲሻል ዋች ፕሬዜዳንት የሆኑት ቶም ፊቶን ፥ ከዛሬ 10 ቀናት በፊት ትሩዝ በተሰኘው የትራንፕ የማህበራዊ ሚዲያው ላይ ቀጣዩ አስታዳደር በገፍ ስደተኞችን ከሀገር ለማባረር ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ ሊያውጅ እና ወታደራዊ ንብረቶችንም ሊጠቀም እንደሚችል ፅፏል።

ትራምፕ ዛሬ " እውነት ነው !!! " ሲሉ የፊቶንን መረጃ አጋርተዋል።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ የመጀመሪያ ስራቸው ስድተኞችን ከሀገር ማባረር እንደሆነ እየተነገረ ነው። በዚህም በርካታ ስድተኞች " ከአሜሪካ ልንባበረር ነው " በሚል ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቀዋል።

አንዳንድ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች የትራምፕ በጅምላ ስደተኞችን ማባረር የሚያተኩረው በ ' ወንጀለኞች ላይ ብቻ ነው ' የሚል ተስፋ አድርገዋል።

#USA #deportation

@tikvahethiopia
#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን እንደሚያግዱ ተነገረ።

ትራምፕ ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው ያምናሉ።

ይህን ተከትሎም ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ዘ ታየምስ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።

ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውታል።

ይህን መረጃ ዘ ታይምስን ዋቢ በማድረግ ያጋራው አል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA " እውነት ነው " - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን በገፍ በጅምላ ከሀገር ለማባረር ጦሩን (መከላከያውን) ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሏል። ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፤ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው በገቡት ቃል መሰረት ሰነድ የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደየመጡበት ሀገር ያባርራሉ። ለዚህም በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ እንደሚችሉ…
" ቤተሰብ መበታተን አልፈልግም ፤ ቤተሰቦች የማይለያዩበት ብቸኛው መንገድ ሁሉንም አንድ ላይ ከአገር ማባረር ነው " - ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከNBC ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

በዚህም ቆይታቸው ከስድተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ምን አሉ ?

ትራምፕ ወላጆቻቸው በውጭ አገራት ቢወለዱም በአሜሪካ የተወለዱ ልጆቻቸው ዜግነት የሚያገኙበትን መብት እሽራለሁ ብለዋል።

ወላጆቻቸው ሌላ ቦታ ቢወለዱም በአሜሪካ የሚወልዷቸው ልጆች የአሜሪካ ፓስፖርት የማግኘት መብት የሚሰጠውን በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት ለማስቆም ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ አሳውቀዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደው ወደ አሜሪካ የሄዱ ሰዎች የመኖሪያም ሆነ የዜግነት መብት ባያገኙም አሜሪካ ውስጥ የወለዷቸው ልጆች ዜግነትን ማግኘት ይችላሉ ታዲያ ትራምፕ ስራ ሲጀምሩ ይህንን ነው የሚሽሩት።

ሆኖም በልጅነታቸው ወደ አሜሪካ የመጡ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ለመርዳት ከዴሞክራቶች ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

🇺🇸 በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት የአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14ን መሰረት ያደረገ ነው። '' ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ወይም ተገቢውን ግዴታዎች የተወጣ ሰው የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ሙሉ መብት አለው '' ይላል።

በሌላ በኩል ፤ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ያላቸውን ጨምሮ ህጋዊ ሰነዶች ያላሟሉ ስደተኞችን ከአገር ለማባረር የገቡትን ቃል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

" ቤተሰብ መበተታተን አልፈልግም " ያሉት ትራምፕ " ስለዚህ ቤተሰቦች የማይለያዩበት ብቸኛው መንገድ ሁሉንም አንድ ላይ ከአገር ማባረር ነው " ብለዋል።

ትራምፕ በአንድ ወቅት ለመሰረዝ ሞክረው የነበረውን ወደ አሜሪካ ብቻቸውን ለሚመጡ ህጻናት ከለላ የሰጠውን የኦባማ 'ዲፈርድ አክሽን ፎር ቻይልድ ሁድ አራይቫልስ' በተሰኘው ፕሮግራም የታቀፉትን በተመለከተ ከምክር ቤቱ ጋር አብሬ እሰራለሁ ብለዋል።

" ከዴሞክራቶች ጋር በአንድ ዕቅድ ላይ እሰራለሁ " ያሉት ትራምፕ ከነዚህ ስደተኞች መካከል ጥቂቶች ጥሩ ስራ የያዙ በንግድ ላይ የተሰማሩም አሉ ሲሉ አክለዋል።

መረጃውን ኤንቢሲን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።

#USA #MASSDEPORTATION

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA #Starbucks

የአሜሪካው ' ስታርባክስ / Starbucks ' ኤክስኪዩቲቭ ቫይስ ፕሬዝዳንት ሚሼል በርን ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ እና የUSAID ዳይሬክተር ሆክላንደር ለበርን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል የስታርባክስን አመራር " እንኳን ወደ ኢትዮጵያ፤ ወደ ቡና መገኛዋ ሀገር በደህና መጡ " ብላለች።

የስታር ባክስ አመራር ሚሼል በርን በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላለው አስደናቂ እድገት፣ በምርታማነት ላይ ስላሉ ኢንቨስትመንቶች ይመክራሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ በተመለከተ ይወያያሉ።

ስታር ባክስ (starbucks) በቡና አቅርቦቱ በመላው ዓለም የሚታወቅ ከፍተኛ ሃብት ያለው ኩባንያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

በአሜሪካ ሀገር በደቡባዊ ካሊፎርኒያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

19 ሰዎችም ተጎድተዋል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ፉለርተን በተሰኘ ከተማ በአንድ የፈርኒቸር ውጤቶች ማምረቻ ህንጻ አናት ላይ ነው።

በህንጻው ውስጥ 200 የሚደርሱ ሰራተኞች ስራ ላይ ነበሩም ተብሏል።

የሞቱት ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት መካካል እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ በህንጻው ውስጥ ስራ ላይ የነበሩት ናቸው።

አውሮፕላኑ ፉለርተን ከተባለ ኤርፖርት በተነሳ ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው በህንጻው አናት ላይ የተከሰከሰው።

መንስኤው እየተጣራ መሆኑን የኤፒ መረጃ ያሳያል።

ሰሞኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአውሮፕላን ጋር የተያያዙ አደጋዎች ተደጋግመው ተሰምተዋል።

በደቡብ ኮሪያ ሙዋን ሲያርፍ የነበረ አውሮፕላን ላይ አደጋ ደርሶ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 179 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

ሌላው ምንም እንኳን የተመዘገበ እጅግ የከፋ ጉዳት ባይኖርም በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ 71 መንገደኞችን የጫነ አውሮፕላን በእሳት መያያዙና በሚያስደነግጥ ሁኔታ መቆሙ ሰሞኑን ከተሰሙት ክስተቶች መካከል ነው።

@tikvahethiopia