TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በተለይም ኮድ 3 እና ኮድ 2 መኪና ይዘው እየተነቀሳቀሱ ሰዎችን የሚዘርፉ የዘነጡ ሌባዎች በከተማይቱ እንዳሉ በተለያዩ ቦታዎችም ዜጎች እየተዘረፉ መሆኑን ጥቆማ ሰጥተናችሁ ነበር።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድ መረጃ አጋርቷል።

መረጃው ምን ይላል ?

በተሽከርካሪዎች ላይ ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር በመለጠፍ ቅሚያ ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ይገልጻል።

ተጠርጣሪዎቹ ተሽከርካሪ
#በመከራየት በቂርቆስ፣ በቦሌ እና በጉለሌ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ  ሞባይል ስልክ  እየቀሙ እንደሚሰወሩ ፖሊስ ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል፡፡

ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው በተለምዶ " ወሎ ሰፈር " እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ተጠርጣሪዎቹ በኮድ 2 A-28629 አአ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3 B-35824 አአ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር ለጥፈው ግምቱ 12 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ ሳምሰግ ሞባይል ቀምተው ይሰወራሉ።

ወንጀሉን በፈፀሙ በአንድ ሰዓት ልዩነት  በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ጉለሌ ሸገር አካባቢ  ከአንድ ግለሰብ ላይ 8 ሺህ ብር የሚገመት ቴክኖ ሞባይል ይቀማሉ፡፡

የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመያዝ በክትትል ላይ እያለ ወንጀሉን በፈጸሙበት እለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።

በተመሳሳይ  ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በኮድ 2C -28629 አዲስ አበባ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ ኮድ 3A-21634 አዲስ አበባ የሚል ሀሰተኛ ሰሌዳ ቁጥር  በመለጠፍ  በተመሳሳይ የቅሚያ ወንጀል ለመፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 " ሸዋ ዳቦ " አካባቢ ተይዘዋል።

በተሽከርካሪ ውስጥ ከተለያዩ ግለሰቦች የተቀሙ ሶስት ሞባይሎች የተገኙ ሲሆን ከሶስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ሲሆን ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በቀን ገቢ ተሽከርካሪዎችን
በመከራየት እና ሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር አዘጋጅተው በመለጠፍ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ  ወንጀል ሲፈፅሙ መቆየታቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል።

የሞባይል ቅሚያ የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ንብረታቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ተሽከርካሪን ማከራየት የሚቻለው የህግ አግባብን ተከትሎ መሆን ስላለበት መኪና የሚያከራዩ ባለንብረቶች ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገበ ፖሊስ አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት እንዳይፈፀም ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ባሻገር አጠራጣሪ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ቁጥር ካጋጠመው ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።


መኪኖቻችሁን ለማን እንደምታከራዩ ለማንስ እንደምታውሱ እወቁ ፤ ተጠንቀቁ !

@tikvahethiopia