TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“መጪው ምርጫ ሁከትን ሊያቀጣጥል ይችላል” - ክራይስስ ግሩፕ #Election2020

ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘንድሮ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን ክፍፍል ሊያሰፋው እና ሁከትንም የበለጠ ሊያቀጣጥል እንደሚችል ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘው ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም አስጠነቀቀ። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ከተባባሰ የኢትዮጵያ መንግስት መጪውን ምርጫ የሚያካሄድበትን ጊዜ እንዲያዘገይ ተቋሙ መክሯል።

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ይህን ያለው የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 6 ባወጣው ዳሰሳ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ቀውስ አምጪ ሁነቶችን በመተንተን የሚታወቀው ይሄው ተቋም በኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎችየሚታዩትን ሁከቶች የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል ተንብዩዋል።

https://telegra.ph/crisis-group-12-16

(Deutsche Welle)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመምከር የባለድርሻ አካላትን ለውይይት ጠራ። የውይይት መድረኩ ከነገ በስቲያ፣ ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2012 በአዲስ አበባው ጁፒተር ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ምርጫ ቦርድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ያዘጋጀው የመጨረሻው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ተወስኖ ለህዝብ ይፋ ከመደረጉ በፊት ግብዓት ለማግኘት እንደሆነ ለተሳታፊዎች በበተነው የጥሪ ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

#ምርጫ2012 #Election2020 #Ethiopia

(ETHIOPIA ELECTION)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

በዛሬው የምርጫ ቦርድ የውይይት መድረክ ላይ የ2012 #ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ በቦርዱ ሰብሳቢ፤ ብርቱካን ሚደቅሳ፤ ከሚደረገው ገለጻ በተጨማሪ የቦርዱ "ኦፕሬሽን" አበይት ዕቅዶችም ለተሳታፊዎች ይቀርባል።

#Election2012 #Election2020

(ETHIOPIA ELECTION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ጥር 23 ይታወቃል...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ውይይት ያገኛቸውን ግብዓቶች ያካተተ ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የሚያሳውቀው የፊታችን ጥር 23 ቀን 2012 በርካታ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ኮንፍረንስ ላይ ነው።

#ምርጫ2012 #ELECTION2020

(ETHIOPIA ELECTION)
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#Election2020

የተረጋገጠ፦ ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በአውሮፓውያን የጊዜ አቆጣጠር : Revised key dates for General Elections 2020

#EthiopiaElection
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot