TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግንቦት20

ነገ የደርግ መንግሥት የወደቀበት የግንቦት 20 በዓል ይከበራል።

በዓሉ በተለይ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ በነበረበት ዓመታት በሀገር ደረጃ ስራ እና ትምህርት ተዘግቶ በድምቀት ሲከበር ቆይቷል።

ካለፉት 6 ዓመታት ወዲህ ግን በዓሉ የነበረውን ድምቀት አጥቶ ተቀዛቅዟል። ያም ቢሆን ግን የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዕለቱ ዝግ ይሆናሉ።

የዘንድሮው የግንቦት 20 በዓልስ ?

በቅርቡ ይፋ የተደረገው እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገና ያልጸደቀው " የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ " ተከብረው በሚውሉ ብሔራዊ ባላት ውስጥ ግንቦት 20ን አላካተተም።

በእርግጥ አሁን ላይ ባለውም አዋጅ ሳይካተት እንደ ብሔራዊ በዓል ሲከበር ነው የቆየው።

በዓሉ በሕግ በዓልነቱ ታውቆ አከባበሩም ተዘርዝሮ ያልወጣ ቢሆንም እንደ ብሔራዊ በዓል ሲከበር ቆይቷል ፤ በዕለቱም ሰራተኞች የእረፍት ጊዜ ያገኛሉ።

ከዚህ በተያያዘ በርካቶች " ስለ ነገው በዓል ግልጽ ይሁንልን " ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ብሎ ያሰባቸውን አካላት " ነገ ግንቦት 20 ስራ ተዘግቶ ነው የሚውለው ? "  ሲል ጠይቋል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " አዲሱ የበዓላት ሕግ ገና አልጸደቀም፤ ስለዚህ ዝግ ነው " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም " ነገ በሚከበረው የግንቦት 20 በዓል መስሪያ ቤት ዝግ ነው ወይስ ክፍት ? " ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።

እሳቸውም ፤ " በካላንደር ላይ የተለወጠ ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም። ካላንደር ይዘጋዋል " ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው፣ " ካላንደር እንደሚዘጋው ነው የምናውቀው ለምን እንዳወዛገበ አይገባኝም " ሲሉ አክለዋል።

አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች ሥራ እንዲገቡ ጠርተዋል መጥራት ይችላሉ ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ፣ " መስሪያ ቤቶች በራሳቸው ውሳኔ ሥራዎችን ሊያቅዱ ይችላሉ። ከሠራተኞቻቸው ጋር ተስማምተው " ብለዋል።

አክለው " መጥራት ይችላሉ ማን ይከለክላቸዋል። አብዛኞቻችን ሥራ የምንውልበት ጊዜ ይኖራል። ያ ማለት ግን ያንን አፍርሰው ሳይሆን መስሪያ ቤቶች፣ ሠራተኞች በፈቃዳቸው ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" እሁድም እኮ ሠራተኛ የምናስገባበት ወቅት አለ። እንጂ ከዚያ ያለፈ የተለዬ ነገር የለም " ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ ኤምባሲ ነገ የደርግ መንግሥት የወደቀበትን #የግንቦት_20 በዓል ምክንያት በማድረግ ሙሉ ቀን ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia