TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD🇪🇹

" ግብፅ #የቅኝ_ግዛት ዘመን አስተሳሰቧን ይዛ በመቀጠል ወደ ስምምነትና ትብብር የሚወስደውን መንገድ ዘግታለች " - ኢትዮጵያ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን አዲስ አበባ ውስጥ የሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ሂደትን የተመለከተ መመሪያ ላይ የሦስትዮሽ ድርድር ሲያካሂዱ ነበር።

ድርድሩ ያለ ስምምነት ነው የተጠናቀቀው።

ኢትዮጵያ ምን አለች ?

- ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ እና በፍትሐዊ ድርድር የሶስቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ የመፍትሔ ሀሳብ ላይ ለመድረስ ያላትን ቁርጠኝነት ይዛ እንደምትቀጥል ገልጻለች።

- አራት ዙር ድርድር ተካሂዷል ፤ ይህ ድርድር የተካሄደው በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ የጋራ መግባባት ነው።

- በአራት ዙሮች ኢትዮጵያ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ልዩነቶችን ለመፍታትና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት አድርጋለች።

- ግብፅ #የቅኝ_ግዛት ዘመን አስተሳሰቧን ይዛ በመቀጠል ወደ ስምምነትና ትብብር የሚወስደውን መንገድ ዘግታለች።

- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ አሞላል እና ዓመታዊ አሰራር መመሪያ እና ደንቦች ላይ የተደረገው ድርድር በሶስቱ ሀገራት መካከል መተማመን ለመፍጠር እንጂ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ የኢትዮጵያን መብት ለመንጠቅ ያለመ አይደለም።

- ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ ላይ በመመስረት የአሁንና የመጪውን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለች።

- አራተኛው ዙር ድርድር ከተጠናቀቀ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌን የሚጻረር መግለጫ ግብጽ አውጥታለች። ኢትዮጵያ በግብፅ በኩል የቀረበባትን የተሳሳተ መረጃ አትቀበለውም።

ግብፅ ምን እያለች ነው ?

* " ኢትዮጵያ የሦስቱንም አገራት ጥቅም ሊያስጠብቅ እና ሊያስማማ የሚችል የሕግም ሆነ የቴክኒክ መፍትሄዎችን ለመቀበል ዝግጁ አይደለችም " የሚል ነገር ይዛ ብቅ ብላለች።

* " የግድቡን አሞላል እና ኦፕሬሽን በቅርበት በመከታተል መብቴን አስከብራለሁ " ስትልም ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥታለች።

* ግብፅ " በግድቡ ምክንያት የትኛውም አይነት ጉዳት ቢደርስብኝ በዓለም አቀፍ ቻርተሮች እና ስምምነቶች መሠረት የውሃ ድርሻዬን እና ብሔራዊ ደኅንነቴን የመጠበቅ መብቴ የተጠበቀ ነው " ስትልም መግለጫ አውጥታለች።

🇪🇹 ኢትዮጵያ #በተደጋጋሚ ጊዜ አንዳቸውም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በአባይ ግድብ ምክንያት ጉዳት እንደማይደርስባቸው ይልቁንም እነሱኑ እንደሚጠቅም አሳውቃለች።

@tikvahethiopia