TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በፍቅር ከተማዋ ድሬ በፍቅር የተጠጣው ፔፕሲ ሽልማት ይዞ ገባ!!!!!

የቀኑን ግለት ሊያቀዘቅዝ ቀዝቃዛ ፔፕሲ ያዘዘው አቶ በላይ ሞላሮ ደስታው እንጂ ኤሌትሪኩ የማይነዝር ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና አሸናፊ ሆኖዋል።

ሕዳር 28 ቀን 2017ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተዘጋጀ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ባለዕድለኛው አቶ በላይ ሞላሮ ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው በርካታ ሽልማቶች ውስጥ 2ኛዋን የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ ተረክበዋል።

ድሬዎች እንኳን ደስ ያላችሁ!
አሁንም በርካታ በርካታ ሽልማቶች ተረኛ ዕድለኞችን እየጠበቁ ነው፡፡ የሞሐን ምርቶች እያጣጣምን ዕድላችንን እንሞክር - እናሸንፍ!

ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕ ያሸልማሉ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የኮሚሽነር ትዕዛዝ ለሌሎችም ከተሞች ምሳሌ ነው ! " - ነዋሪዎች

ከጫኝ እና አውራጆች ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ለከተማው ፀጥታ አመራሮች የሰጡት ትዕዛዝ እጅግ እንዳስደሰታቸው ፤ ይህ ትልቅ ተሞክሮ በሌሎች ከተሞችም ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው እንደሆነ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የኮሚሽነሩን መረጃ ተመልክተው ቃላቸውን ከሰጡን ነዋሪዎችና የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መካከል የአዲስ አበባ፣ ሸገር ሲቲ ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ ፣ ጅማ ... የሌሎችም ይገኙበታል።

ነዋሪዎቹ " የገዛ እቃችንን ለማውጣት እና ለማስገባት የሰፈር ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ማግኘት አለብን ይህ ምን አይነት ነገር ነው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ ተሞክሮ ወደ ሌላም ቦታ መሄድ እንዳለበት ገልጸዋል።

" የገዛ እቃችንን ማስገባት እና ማስወጣት ፈተና ነው ፤ ለትንሽ እቃ እንኳን የሚጠይቁት ክፍያ ደግሞ የሚያስደነግጥ ነው ፤ አንዳንዴ እኮ ከእቃውም በላይ ይጠራሉ " ብለዋል።

" ሲፈልጉ ' ያለኛ እቃው አይገባም ' ብለው ያስፈራራሉ ሲያሻቸው ለፀብ ይጋበዛሉ ያለነሱ ሰው ያለ አይመስልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ሰው በገዛ እቃው ስንት ሰዓት ሙሉ ተከራክሮ ትንሽ ይቀነስለትና ብሩን ይሰጣል። ይህ " ክፍያ ሳይሆን ዝርፊያ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አንዳንዴ ህግ እንኳን እነሱ ላይ የሚሰራ አይመስልም እንደልባቸው ገንዘብ ይጠይቃሉ ኧረ የህግ ያለህ ብለን የሚመለከታቸውን ስንጠይቅ " ተስማሙ " ይሉናል ብለዋል።

" ሰዎች ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃ ለማስገባት ይገደዳሉ ሰዎቹ አንዳንዴ ለሊት ሁሉ ተጠራርተው ይመጣሉ ፤ አንደንዴ ደግሞ ለሊት እቃ ማስገባት አይቻልም ይባላል " ሲሉ ችግሩን አስረድተዋል።

" ዛሬ ሰዎቹን እንቢ ብንላቸው ነገር መውጫና መግቢያ ስለሚያሳጡን ትንሽ ብርም ቢሆን አስቀንሰን እቃውን እናስገባለን " ሲሉ አክለዋል።

ይህ ቀላል ነገር አይደለም ስቃዩን እና እንግልቱን ያየ ብቻ ነው የሚያውቀው ብለዋል።

" ማንኛውም ሰው የገዛ እቃውን ቢፈልግ በራሱ ሰው ካስፈለገ እና ከፈቀደ አቅሙ በሚፈቅደው ተደራድሮ በጫኝ እና አውራጅ ማስወረድ መቻል አለበት " ሲሉ አክለዋል።

" የገዛ እቃችንን ለማስገባት የሰፈር ጎረምሳ ፍቃድ አያስፍልገንም ይህንን ማስከበር ያለበት የፀጥታው አካል ነው " ብለዋል።

ድሬዳዋ ለዚህ የዜጎች የሁል ጊዜ ስቃይ እና ሮሮ የሰጠችው መፍትሄ እጅግ ትልቅ ነው ሲሉ አወድሰዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ከፀጥታ ኃይል አመራሮች ጋር በነበራቸው ምክክር ፤ ህዝቡ በጫኝ እና አውራጅ የሚያየው ስቃይ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

" ሰፈር ላይ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም ፤ ከአሁን በኃላ ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

" እኔ ማህበር ነኝ እኔ እንደዚህ ነኝ " የሚሉ ማን እንካን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ ናቸው ብለዋል።

ሰው በፍርሃት እየኖረ እንዳለ በመሆኑም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር ሰው ከፈለገ በራሱ ካልፈለገ ሰው ጠርቶ ተደራድሮ በሚችለው ማስወረድ እንደሚችል ገልጸዋል።

ገና ለገና ቤት ሲቀየር ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ሰው የሚደራጅበት ስራ ትክክል እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

ጫኝና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ እንደሆነም ተናግረዋል።


#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
" በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

#EEP

@tikvahethiopia
" የወንጀሉ ተጠርጣሪ እራሷ አሰሪዋ ሆና ነው የተገኘችው " - ፖሊስ

የግድያ ወንጀል እንደፈፀመች አምና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረች የቤት ሰራተኛ ላይ በተደረገው እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀሉ ተጠርጣሪ አሰሪዋ ሆና እንደተገኘች የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ህፃን ሰላማዊት አስፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐድያ ዞን ነው ።

በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የአጎቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሴ ለህፃኗ ወላጆቿ እያስተማረች ልታሳድጋት ቃል በመግባት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኖሪያ ቤቷ ይዛት በመምጣት መኖር ትጀምራለች፡፡

መስከረም 3ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ሲሆን ለግዜው የፀቡ መነሻ ባልታወቀ ምክንያት ህፃን ሰላማዊት አስፋው ህይወቷ ያልፋል፡፡

ህፃኗን እያስተማረች ልታሳድጋት ያመጣቻች ተጠርጣሪ ታዳጊዋን የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በእንጨት በመደብደብ ከ20 ቦታ በላይ ጉዳት በማድረስ እና አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በህፃኗ ህልፈተ-ህይወት ተጠያቂ ላለመሆን ያሰቡት ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከባለቤቷ ጋር በመነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኝ የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት ተስፋነሽ ጀባኔን ህፃኗን በድንገት እንደገደለቻት ለፖሊስ ቃል እንድትሰጥና ለውለታዋም ደሞዟን በእጥፍ እንደሚጨምሩላት በተለያዩ መደለያዎች ያሳምናሉ።

በወንጀሉም ጉዳይ ጠበቃ እንደሚቀጥሩላት ካሳመኗት በኋላ ለፖሊስ የሰጠችው ቃል የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመች የሚገልፅ ነበር፡፡

ሆኖም ፖሊስ የተስፋነሽ ጀባኔን ቃል መነሻ በማድረግ የምርመራ ስራውን በማስፋት ሂደት ለጊዜው ተጠርጣሪ የሆነችው የቤት ሰራተኛ " እኔ ነኝ የገደልኳት " ብትልም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች መኖራቸውን የደረሰበት ፖሊስ ባደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀል ድርጊቱን የቤት ሰራተኛዋ እንዳልፈፀመች እና ልታሳድግ እና ልታስተምራት ባመጣቻት ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ ህፃን ሰላማዊት አሰፋ ህይወቷ እንዳለፈ ይደርስበታል።

የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ተጠርጣሪዋ ግለሰብም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሟን አምና በመኖሪያ ቤቷ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመች መርታ ማሳየቷን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪ ግለሰቧና ባለቤቷ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ፍ/ቤት እንዳዘዘ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደማይኖር ያስታወቀው ፖሊስ ንዴትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የወንጀል ድርጊትን መከላከል እንደሚቻል አስታውቆ ከቅድመ መከላከሉ ባሻገር ወንጀል ሲፈፀም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል። የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ…
#Update

" የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል

" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " ሲል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።

ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ተጠባበቁ ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል

በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው ፦
- በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ ፣
- በአዳማ፣
- በሀዋሳ፣
- በጅማ፣
- በአርባምንጭ፣
- በወላይታ ሶዶ፣
- በሻሸመኔ፣
- በወልቂጤ፣
- በመቐለ፣
- በዓድዋ፣
- በአላማጣ፣
- በዲላ፣
- በቦንጋ፣
- በሚዛን እና ሀገረማርያም ኃይል ተመልሶ ተገናኝቷል።

እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን የገለፀው ማዕከሉ በቀሪዎቹ አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ርብርቡ መቀጠሉን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አለመፈታቱ የተገለጸ ሲሆን ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

#EEP

@tikvahethiopia
#BREAKING🚨

የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።

የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል።

የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።

በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል።

ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።

ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገደዋል።

ተቃዋሚዎቹ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአላሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆናችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።

አላሳድ ከደማስኮ ወጥተው ሄደዋል ተብሏል።

የፕሬዜዳንቱን ከደማስቆ መልቀቅ ሁለት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

አሁን ላይ አሳድ የት እንደገቡ የሚታወቅ ነገር የለም።

የታጠቁት ተቃዋሚዎች ባወጡት መግለጫ ፤ " ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል " ብለዋል።

" ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም ገልጸዋል።

በሽር አላሳድ ሀገሪቱን ለቀው መጥፋታቸውንም አሳውቀዋል።

ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያውንም ተቆጣጥረውታል።

አንዳንድ ቪድዮዎች እንዲሁም ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በደማስቆ ጎዳናዎች ሶርያውያን ወጥተው ' ነጻነት ! ነጻነት ! ' እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

እነ ሩስያ ፣ ኢራን ፣ አሜሪካ እና ቱርክ ?

የአገዛዙ ዋነኛ አጋር የሆኑት ሩሲያ እንዲሁም ኢራን ለአሳድ ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ ቢሰነብቱም አገዛዙን ከመፍረስ አልታደጉም።

ሩስያ በዩክሬን በሚያደርገው ጦርነት የተጠመደች ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ እስራኤል በሊባኖስ ሔዝቦላህ ላይ በከፈተችው ዘመቻ ምክንያት ተዳክማለች።

ጦርነቱ ሲባባስ ሞስኮ የሩሲያ ዜጎች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ጥሪ ስታቀርብ ነበር።

በሶሪያ የረጅም አመታት የእርስ በርስ ጦርነት ዋና ተዋናይቷ አሜሪካም ብትሆን ሁኔታውን አይታ ዜጎቿን " በደማስቆ በረራዎች እስካሉ ድረስ " ሶሪያን ለቅቀው እንዲወጡ ስትጮህ ነበር።

ቱርክ በሶሪያ ያሉ አንዳንድ የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ትደግፋለች።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለወራት አሳድን ከተቃዋሚዎች ጋር ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ አንዲደርሱ ግፊት ሲያደርጉ ነበር።

ፕሬዜዳንቱ የተቃዋሚዎችን የቅርብ ጊዜ ግስጋሴ እንደሚደግፉ ተናግረው " አሳድ ጥሪዬን ቢቀበል ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር "  ብለዋል።

#ሶሪያ : እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በተቃውሞ ስትናጥ ከቆየች በኃላ በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ ሰዎች አልቀዋል። ሀገሪቱ እንዳልነበረ ሆናለች። ለሀገሪቱ እንዲህ መሆን የውጭ ኃይሎች አገዛዙን እና አማጽያንን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ድርሻ አላቸው።

መረጃው ከአልጀዚራ፣ ሮይተርስ እንዲሁም ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING🚨 የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ። የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል። የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር። በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት…
#Syria : የ24 ዓመታት የፕሬዜዳንት በሽር አልአሳድን አገዛዝ ያስወገዱት የታጠቁት ተቃዋሚዎች አልአሳድ ሀገር ጥለው መጥፋታቸውን ገልጸዋል።

የሶሪያ ተዋጊዎች በደማስቆ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያን ከመቆጣጠራቸው ጥቂት ጊዜ በፊት በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የአንድ አውሮፕላን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል።

የIL76 አውሮፕላን የበረራ ቁጥሩ ' የሶሪያ አየር 9218 ' ከደማስቆ የተነሳ የመጨረሻ በረራ ነበር።

ይኸው አውሮፕላን መጀመሪያ ላይ ወደ ምሥራቅ በረረ፣ ከዚያም ወደ ሰሜን ዞሮ ሲበር ነበር።

ለደቂቃዎች ሆምስን ከዞረ በኃላ ከራዳር እይታ ውጭ ሆኗል። አውሮፕላኑ የት ይገባ የት ምንም አልታወቀም።

በሽር አልአሳድ ከሀገር መውጣታቸው ይነገር እንጂ የት እንዳሉ እስካሁን አይታወቅም።

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

አሜሪካ ያሉ ወዳጅ ዘመዶቻችን በRemitly በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ እኛ በM-PESA ተቀብለን  በተጨማሪ 5% የገንዘብ ሽልማት እና 1ጊ.ባ ነጻ የኢንተርኔት ዳታ እንበሸበሻለን! 

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

 #FurtherAheadTogether
#DStvEthiopia

ደማቁ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥
👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው