TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ።

በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ  ፊርማ መስከረም 8/ 2017  ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል።

ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች አልፈፅምም ማለትና ማደናቀፍ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።

ሁለቱ የዞን የስራ ሃላፊዎች ከመስከረም 8/2017 ዓ.ም ከነበራቸው የስራ ሃላፊነታቸው ተሰናብተው የተሰጣቸው የመንግስት ንብረትና ስራ እንዲያስረክቡ በተፃፉላቸው የስንብት ደብዳቤዎች ተገልፆላቸዋል።

አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት በቅርቡ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተመረጡት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ተክተው  የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና  አስተዳዳሪነት እንዲመሩ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾሙ ናቸው። 

በተመሳሳይ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 6/2917 ዓ.ም " ከአባላትና ከድርጅታዊ ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ ደብዳቤ የፃፈላቸው የህወሓት ማእካላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ማእከላይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የአክሱም ከተማ የፀጥታ ሃላፊ ፣  የተምቤን ዓብዩ ዓዲ ከተማ ከንቲባና ሁለት የዞን የስራ ሃላፊዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ በማደናቀፍ በሚል ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸው መዘገባችን ይታወሳል።  

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ። በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ  ፊርማ መስከረም 8/ 2017  ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል። ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ…
#Tigray

" የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል።

ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር።

ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት አመራሮች ክፍፍል እና ስለ ጸጥታ ኃይሉ ተነስቷል።

ካቢኔው " ከጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና ውጪ ፦
- መንግስታዊ የስራ ምደባ ማካሄድ ፣
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ማፍረስ
- የመንግስት መዋቅር ለመረበሽና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

" መንግስት ለዚህ መሰል ተቀባይነት የሌለው እንቅስቃሴ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ከህወሓት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ካቢኔው " በአሁኑ ወቅት በህወሓት አመራሮች ዙሪያ የተፈጠረው መከፋፈል በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረ ተደርጎ መወሰዱ ልክ አይደለም " ብሏል።

" ክፍፍሉ በጥቂት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረ ነው " ያለው ካቢኔው " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከህወሓት ከሙሁራን ከፀጥታ አካላትና ከተፎካካሪ ድርጅቶች በተወጣጡ አካላት የተደራጀ መሆኑ ከግምት ውሰጥ በማስገባት ከህወሓት ክፍፍል ጋር አቆራኝቶ መግለፅ ልክ አይደለም " ሲል ገልጿል።

ካቢኔው ስለ ፀጥታ ኃይሎች ባነሳው ነጥብ " የፀጥታ አካላት ሁሉም ዓይነት ችግሮችና ፈተናዎች ተቋቁመው የህዝብ ፀጥታ ለማስከበር እያደረጉት ያለውን ጥረት አወንታዊ እና እውቅና የሚቸረው ነው " ብሏል።

" ስራዎቻቸው ከማንኛውም የፓለቲካ አስተሳሰብ ነፃ በማድረግ ገለልተኛ አቋም ይዘው እንዲሰሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ይደግፋል ያበረታታል " ሲል አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " እኔ ድርድር ያስፈልጋል በሰላም ይፈታ ስል ፤ እሱ ግን ' ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ' ነበር ያለው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ። በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች…
#Tigray
 
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።

ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው " ቡድን " ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል።

መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ " የህዝብ ምክር ቤቶች የትግራይ ጊዚያዊ መንግስትና የህዝቡ አካል እንጂ የህወሓት መዋቅር አለመሆናቸው አውቆ ' ቡድኑ ' የራሱ መሳሪያ ለማድረግ እያካሄደ ያለውን መሯሯጥና ውንብድና ማቆም አለበት " ይላል።

ስለሆነም ምክር ቤቶቹ የመንግስትና የህዝብ መዋቅር መሆናቸው በማመን ' ቡድኑ' ምክር ቤቶቹ በመጠቀም ያልደገፉትንና ሃሳቡ ያልተቀበሉት የመንግስት ሹመኞች ጥላሸት ለመቀባትና ከሃላፊነት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት መቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።

ምክር ቤቶቹም ይህንን የመንግሰትና የፓለቲካ ድርጅት የሚቀላቅል ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ አለባቸው ብሏል።

" ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ህግና ስርዓት ለማስከበር ሲባል ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት መሸጋገር የግድ ይሆናል " በማለት አክለዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ከቀናት በፊት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ  ያወጣውን የአቋም መግለጫ የሚቃወም መግለጫ  አውጥቷል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ያወጣው  ባለ 4 ነጥብ የተቋውሞ መግለጫ ፤ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጊዚያዊ  ስራዎች ለመስራት መቋቋሙ ተዘንግቶ ከተቀመጠለት የቆይታ የጊዜ ሰሌዳ በላይ እንዲቆይና ራሱን ወደ ተሟላ የመንግስት ሃላፊነት  ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ፀረ ዴሞክራሲና ኢ-ህገመንግስታዊ ነው " ብሏል።

ምንም እንኳን " ኢ-ህገመንግስታዊ " ብሎ ቢገልጽም የአገር ወይም የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀፆችን አላጣቀሰም።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን " ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ተልእኮ ወደ ጎን በመተው ህወሓት ለማፍረስ ፣ ሰራዊት ለማዘዝና የመንግስትና ህዝብ ሃብት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበተን እየሄደበት ያለውን የተሳሳተ መንገድ ሊያቆም ይገባል " ሲል አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " አስቸኳይ " ያለውን ሰብሰባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። ዛሬ መሰከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት አዳራሽ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን ህወሓት በይፋ የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ካድሬዎች ተገኝተዋል።  አቶ ጌታቸው በሰብሰባው መክፈቻ…
#Update

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሚመራው የህወሓት ቡድን ጋር ያላቸው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደሚሰራ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን ተናግሯል።

በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች መስከረም 20/2017 ዓ.ም በመቐለ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።

ውይይቱ ለሁለት የተከፈለው ድርጅት ለማዳንና የትግራይ ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ያለመ  ነው ተብሏል።

በዚህም ወቅት በአቶ ጌታቸው የሚመራው ቡድን የተፈጠረው ልዩነት እንዲሰፋ እየሰራ ያለው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይሳካ የተሰለፈ የሰላም ፀር የሆነ ሃይል ነው " ብሏል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የህወሓት ህጋዊነት እንዳይመለስ እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይፈፅምና የተገኘው ተነፃፃሪ ሰላም እንዳይቀጥል እንቅፋት የሆነው " የሰላም ፀር " ሲሉ የጠሩትን በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራውን ህወሓት ከሰዋል። 

" በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ሃይል ጉባኤ አካሂጃለሁ በሚል ሽፋን ራሱን እንደ ህጋዊ በመቁጠር የወረዳና የከተማ ምክር ቤቶች እየሰበሰበ ይገኛል " በማለት አክለዋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ሃይል በስም ማጥፋት ተግባራት መሰማራቱ የገለፀው በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው የሚመራ ህወሓት ከዚህ ተግባሩ እንዲቆጠብና ሰርዓት እንዲይዝ ጠይቋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ዛሬ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ላይ መሰረት ያደረገ ውይይት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል…
#ትግራይ

" ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን "  ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል ሲል በድጋሜ ከሷል።

" ህጋዊ ያልሆነው ቡድን " በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች " ህጋዊ ያልሆነ " የስራ ምድባ በማካሄደ የመንግስት ግለበጣ በማካሄድ የቀን ተቀን ስራ የማደናቀፍ ኢ-ህጋዊ ተግባሩ ቀጥሎበታል ሲል ጠቅሰዋል።

" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ህጋዊ ያልሆኑ የስራ ምደባዎች በማካሄድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ከማደናቀፍ አልፎ ስራውን በሚመሩት ላይ አላስፈላጊ ጫና በመፍጠር የመንግስት ስራ እንዲቆም እያደረገ ነው ሲልም ገልጿል።

በየደረጃው የሚገኙ የጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅሮች ፣ በትግራይ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላት እና ተቋማት ፣ የፌደራል መንግስት እንዲሁም የዓለም ማህበረሰብ " ህጋዊ ባልሆነው መንገድ " የሚመድቡ እና የሚመደቡ በማንኛውም መንግስታዊ ሃላፊነት ስም እንዲንቀሳቀሱ ምንም እውቅና የሌላቸው እንደሆኑ እንዲገነዘቡ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመልክቷል።

" ህጋዊ ባልሆነው ቡድን " የሚመደቡት አካላት የሚያስተዳድሩት ማንኛውም ሃብት የለም ያለ ሲሆን የፀጥታ አካላት ፣ የፍትህ መዋቅር እና ባንኮች ይህንኑ በመገንዘብ ህግ እንዲያስፈፅሙ ሲል አስገንዝበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ህጋዊ ያልሆነ ቡድን " ሲል በፈረጀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተመደቡ የአስተዳደር አካላት ስም ጠቅሶ ማንኛውም የመንግስት ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ የሚያግድ ደብዳቤ ወደ ባንኮች ፅፏል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray 🔴 " ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ 🟠 " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት 🔵 " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል። የጊዚያዊ…
#Update

የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ወንጀል ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፁ በሰጠው ማብራርያ ፤ " ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 :00 ሰዓት አካባቢ ከአክሱም ወደ መቐለ ከተማ በመኪና በመጓዝ ላይ የነበሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁመዋል " ብሏል።

አጣሪ ቡድኑ ከፓሊስ እና ከፍትህ አካላት የተወጣጣ እንደሆነ ገልጿል።

የግድያ ሙከራ ወንጀሉ ተፈፅሟል ተብሎ በማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፆች ከተሰራጨበት ደቂቃ ጀምሮ ጥብቅ የማጣራት ስራ መጀመሩ አብራርቷል።

ኮሚሽኑ የማጣራት ሂደቱ እንዲሳካ የህብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል። የማጣራት ሂደቱ የሚጎዱ በማህበራዊ ሚድያ የሚነዙ ሁለት ፅንፍ የያዙ አሉባልታዎች እንዲቆሙ አሳስቧል።

የሚደርስበትን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

የግድያ ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የማይቅነጣል ወረዳ ሲሆን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ማለታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ። የማህሌት አስክሬን አጋቾች ከቀበሩበት ወጥቶ የአስከሬን ምርመራ ተጠናቅቆ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዓድዋ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን የቀብር ስነ-ሰርዓት ተፈጽሟል። የቀብር ስነ-ስርዓቱ የክልል ፣ የዞን እና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም በርካታ የዓድዋ ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር። ተማሪ ማህሌት ተኽላይ በዓድዋ  ከተማ " ዓዲ ማሐለኻ " የሚባል…
#Update

ወጣት እንስቶችን በግፍ ከገደሉ ውስጥ አንዱ በእድሜ ልክ አስራት ሲቀጣ ፤ የተቀሩት ለፍርድ ተቀጥረዋል።

የመቐለ የማእከላዊው ፍርድ ቤት ትላንት ባዋለው ችሎት ኣፀደ ታፈረ በተባለች እንስት ወጣት በተፈፀመ የግድያ ወንጀል በይን የሰጠ ሲሆን ዓድዋ ከተማ ላይ በተገደለችው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ግድያ ተጠርጣሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል። 

ሟች ወጣት ኣፀደ ታፈረን በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ አስራት እንዲቀጣ  የመቐለ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ህዳር 12/2017 ዓ.ም ወስኗል። 

ገዳይ ወንጀለኛ ቢንያም ገብረሚካኤል ሟች እንስት ኣፀደ ታፈረ በመቐለ ልዩ ስሙ እንዳ ገብርኤል የተባለ ቦታ አንቆ ከገደላት በኋላ በአከባቢው ወደ ሚገኘው ጫካ ወርውሯት እንደሄደ በአቃቤ ህግ የቀረበው የክስ ማስረጃ ያስረዳል።

ገዳይ ወንጀለኛ ቢንያም በፈፀመው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ጥፍተኝቱ አረጋግጦ በእድሜ ልክ አስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የመቐለ ፍትህ ፅህፈት ቤት አስታውቀዋል።

ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ፤ " ገዳይ ወንጀለኛው የእድሜ ልክ አስራት ያንሰዋል ፤ በሞት ፍርድ መቀጣት ነበረበት " ብለዋል። 

በተያያዘ ዜና ፍርድ ቤቱ ባለፈው 2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ ለወራት ታግታ ተሰውራ ቆይታ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ሞታ ተቀብራ አስከሬንዋ የተገኘው እንስት ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ በማህሌት ግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም በአቃቤ ህግ የቀረበላቸው የምስክሮች ማስረጃ እንዲከላከሉ ለህዳር 12/2017 ዓ.ም የቀጠረ ቢሆንም ተጠርጣሪዎች መከላከል ስላልቻሉ የውሳኔ ፍርድ ለመስጠት ለህዳር 23/2017 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።  

ባለፈው ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ የመቐለ እና የውቕሮ ከተሞች በቅርብ የትዳር እና የፍቅር አጋሮቻቸው የተገደሉ ሁለት እንስቶች ጉዳይ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ተይዘው የህግ የምርመራ ሂደት መጀመሩ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችን በውይይት መፍታት ካልቻልን ትግራይን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው በግልፅ ነግሮናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ወደ ሁለት በተከፈሉ የህወሓት አመራሮች እየታመሰ የሚገኘው የክልሉ የፓለቲካ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ ተናግረዋል።

" በምንገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የፓለቲካ የአሰላለፍ ለውጥ እየተፈጠረ ነው ፤ የትግራይ ሁኔታም ከሚታየው ለውጥ ተያይዞ ያሉት ዕድሎች እና ፈተናዎች መተንተን ያስፈልጋል "  ብለዋል።

" የትግራይ ፓለቲካ ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ መገንዘብ ትቶ በአመራሮቹ እየታመሰ ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችንን እንድንፈታ እየገለፀ ነው ካልተቻለ ግን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው ግልፅ አድርጓል " ሲሉም አክለዋል።

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ለሚካሄደው በፕሪቶሪያ የሰላም አፈፃፀም የሚመለከት የግምገማ መድረክ ከወዲሁ " እኔ ነው መሳተፍ ያለብኝ " ወደ ሚል መሳሳብ ተገብቷል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

" የህወሓት አመራር ሉአላዊ የትግራይ ግዛት ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ነጻ ሆኖ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ዋና አጀንዳ ዘንግቶ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የእለት ተእለት ስራዎች በማድናቀፍ ተጠምዷል " ሲሉም ከሰዋል።

" ከፕሬዜዳንት ስልጣን ወርደዋል ፤ ወደ ውጭ አገር ሊወጡ እያመቻቹ ነው ፤ ውጭ ሀገር ወጥተው እንዲቀሩ መንግሥት እያመቻቸላቸው ነው "  ተብሎ ሲወራባቸው ስለ መሰንበቱ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለስራ በምወጣበት ጊዜ ከሁለቱ ምክትሎች አንዱ መወከል የተለመደ አሰራር ነው መወከሌም እቀጥላሎህ ፤ ' ከሀገር ሊወጣ ነው ' ተብሎ የተነዛው ወሬም ከሃቅ የራቀ መሰረተ ቢስ የውሸት ወሬ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

' ለስልጣን መቆራቆስ ትተን በጦርነት እና ጦርነት ወለድ ችግሮች የተጎሳቆለው ህዝባችን መካስ ማስቀደም አለብን " ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በእሳቸው የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው የህወሓት ከፍተኛ አመራር ጋር የሃይማኖት አባቶች በጀመሩት የእርቅ ጥረት ችግሮቻቸው ለመፍታት ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችን በውይይት መፍታት ካልቻልን ትግራይን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው በግልፅ ነግሮናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ  ወደ ሁለት በተከፈሉ የህወሓት አመራሮች እየታመሰ የሚገኘው የክልሉ የፓለቲካ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ ተናግረዋል። " በምንገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ…
" አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው " - አቶ አማኑኤል አሰፋ

በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው " ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም " ብለዋል።

አቶ ጌታቸውን " የቀድሞው ፕሬዝዳንት " ሲሉም ጠርተዋቸዋል።

አቶ አማኑኤል " የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው ሲሉ " ወንጅለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመት ያለ እቅድ እየተመራ ይገኛል።

- ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቆጠረው የተሰጡት ተልእኮዎች ከመፈፀም ይልቅ በተቃራነው ነው እየሰራ ያለው።

- ህወሓት በጊዝያዊ አስተዳደሩ ያለውን የስልጣን ውክልና ካነሳ ወራት ተቆጥሯል።

- በጊዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ክፍፍል ላይ ህወሓትን የሚተካ አመራር ከፌደራል መንግስት በመወያየት ይተገበራል። ይህንን ለመተግበር የሚያስችል ተከታታይ ውይይት ከፌደራል መንግስት እየተካሄድ ነው። ስምምነት ከተደረሰበት በኋላ መግለጫ ይሰጥበታል።

- በዲሞብላይዜሽን (DDR) አሰራር ታጣቂዎች ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀል ከፌደራሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በትግራይ ግዛት ያሉ የውስጥ እና የውጪ ታጣቂዎች ተሟልተው ወጥተው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ከመመለስ ጎን ለጎን መፈፀም እንዳለበት የፕሪቶሪያ ውል አስቀምጠዋል አሁን ግን የታጣቃዎች ዲሞብላይዜሽን (DDR) እየተመራበት ያለው አሰራር ትክክል አይደለም።

- በዲሞብላይዜሽን ትግበራ (DDR) ለሚሰናበት ታጣቂ የሚሰጠው ማቋቋምያ አነስተኛ እና በቂ አይደለም። በዳታ አሰባሰብ (ባዮሜትሪክስ) ያለው አካሄድም ግልፅነት የጎደለው ነው።

- እየተካሄደ ያለው የDDR ትግበራ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አግባብ ውጪ ነው።

- ጊዚያዊ አስተዳሩ የተሰጡት ሃላፊነቶች ወደ ጎን በመተው ህወሓት በማፍረስና እና ሌላ ህወሓት በማዋለድ ይውላል።

- ሰራዊት ተቆጣጥሮ ወታደራዊ ስርዓት ለመትከል ይንቀሳቀሳል፤ በሪፎርም ስም የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ያፈርሳል ፤ የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት ለመበተን ይንቀሳቀሳል።

- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ልኡክ በምርጫ ስልጣን የሚይዝ መንግስት እንዲቋቋም ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። ይሁን እንጂ ተከታታይ ውይይቶች በማካሄድ ራሱ ወደ መደበኛ መንግስት ለመቀየር እየሰራ ነው።

... ብለዋል።

ከቀናት በፊት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ በሰጡበት ወቅት በደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ቡድን አስተዳደሩ ስራ እንዳይሰራ እያደናቀፈ ስለመሆኑ የወረዳ ምክር ቤቶችን በመጠቀምም አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ መሆኑን ይህም " መፈንቅለ መንግስት " እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈ ለሁለት የተሰነጠቁት የህወሓት አመራሮች ተስማምተው ክልሉን መምራት ካልቻሉ ብልፅግና የትግራይ አስተዳደርን ሙሉ በሙሉ ለመረከብ እንደሚገደድ ከፌደራል መንግስት ጋር በተካሄደ ወይይት መነሳቱን ተናግረው ነበር።

NB. ዛሬ መግለጫ የሰጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ካሉና ህወሓት በአስተዳደሩ ያለውን ውክልና ካነሳ ወራት መቆጠሩን ከገለጹ በኃላ " በጊዚያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ክፍፍል ህወሓትን የሚተካ አመራር ከፌደራል መንግስት በመወያየት ይተገበራል። ይህንን ለመተግበር የሚያስችል ተከታታይ ውይይት ከፌደራል መንግስት እየተካሄደ ነው " ሲሉ ቢገልጹም ከየትኛው የፌዴራል መንግስት አካል ጋር ንግግር እየተደረገ እንዳለ በግልጽ አውጥተው አልተናገሩም። የፌዴራል መንግስት እስካሁን በህወሓት አመራሮች ክፍልል ጉዳይ ምንም አይነት ይፋዊ ቃል ሰጥቶ አያውቅም።

#TikvahEthiopiaMekelle #VOATigrigna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" አየር መንገዱ ላደረገው ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ  ማብራርያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በክልሉ ትራንስፓርት እና መገናኛ ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ህዳር ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሳተፍ በተጓዙ ወገኖች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል አለ።

ይኸው የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ " ኢ-ፍትሃዊ እና አስደማሚ ነው " ብሎታል።

ቢሮ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለፌደራል የትራንስፓርት ሚንስቴር በፃፈው ድብዳቤ እንደጠቆመው፤ " ተቋሙ የፈፀመው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ታማኝነቱ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ የሚያስይዝ ነው " ሲል አብራርተዋል።  

ስለሆነም የበደላቸው ተጓዥ ደንበኞቹ እንዲክስ ፣ እንዲደግፍና ተግባሩ እንዲፈፅም ምክንያት የሆነውን በቂ ማብራርያ ለህዝብ እንዲሰጥ ቢሮው ጠይቋል።

ከአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል ተጓዥ ተሳታፊዎች ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገው የትኬት ጭማሪ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ካቢኔ መወያያ አጀንዳ እንዳደረገው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት። አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው። ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል። …
#Mekelle

በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ።

ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ባገኘው መረጃ አዲሱ ከንቲባ ከዛሬ ጀምሮ የከንቲባ ስልጣናቸው የሚፀና ይሆናል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት ፤ " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም ፤ አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያውም መንግስት የመደበው ብቻ ነው። በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም ፤ ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል።

ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ የሾመ ሲሆን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሹመቱ ውድቅ ማድረጉ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

ከቀናት በፊት ዒግራይ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐለም አረጋዊን ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን ከንቲባ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቀድሞ / ነባር ነኝ አይደለሁም የሚለውን ከፓሊስ እንነጋገርበታለን ፤ ያኔ ግልፅ ይሆንላቸዋል !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሳምንት ህዳር 17/2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ አማኒኤል አሰፋ በሰጡት መግለጫ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞ ፕሬዜዳንት " ሲሉ ጠርተዋቸው ነበር። ህዳር 22/2017…
#ሹመት

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን 6 አዳዲስ ሹመቶች ሰጥተዋል።

ከስድስቱ ሽመቶች ሁለቱ በደብረፅዮን ገ / ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተሾሙትን በማንሳት የተሰጠ ነው።

በዚሁ መሰረት ፕሬዜዳንቱ ከህዳር 20/2017 ዓ.ም  ጀምሮ የሚፀና በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ በመሆኑ የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በመሻር በብርሃነ ገ/ዮሱስ ተክተዋል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ምክትል የስራ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው ከህዳር 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የዓዲግራት ከንቲባ በመሆን የተሾሙት ረዳኢ ገ/ሄር ምትክ ኪ/ማርያም ወ/ሚካኤል ምክትል የቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ፕሬዜዳንቱ በጡሮታ በተገለሉት ሓዱሽ ካሱ ምትክ ዶ/ር ገብሩ ካሕሳይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አድርገዋቸዋል።

ኮማንደር ተስፋይ ገ/ማርያም በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል ማጣራት ሃላፊ ፤ ኮማንደር ጌታቸው ኪሮስን በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል መከላከል ሃላፊ እንዲሁም አቶ ሃይላይ ኣብራሃ በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የሰው ሃይል ልማት ዘርፍ ሃላፊ አደርገው ሹመዋል።

በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው በተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ምትክ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ደብዳቤ መሾማቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። በውይይቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዛዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር። ከነሱ በተጨማሪ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ነበሩ። ምንም እንኳን የውይይቱ ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት…
#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " በትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክህደት የፈፀመ ቡድን " ሲል ፈረጀ።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " ብሄራዊ ክህደት ፈፅሟል " ሲል የፈረጀው ማእከላዊ ኮሚቴ " ቡድኑ ከአፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ " መላው የትግራይ ህዝብ እና አባላት እንዲታገሉት ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የትግራይ ህዝብ መብት እና ራስን በራስ የማስተዳደር መገለጫ የሆኑት ምክር ቤቶች እንዲፈርሱ ለፌደራል መንግስት ጠይቀዋል " ሲል ገልፀዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ካካሄደው ውይይት መልስ ባወጣው መግለጫው ነው ይህን ጠንከር ያለ ፍረጃ ያቀረበው።

በተጨማሪ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ሳይረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የትግራይ ሰራዊት በዲሞብላይዜሽን (DDR) ምክንያት በችኮላ እንዲሰናበቱ እያደረገ ነው ብሏል።

በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚን ጥያቄ ውስጥ በሚከት መልኩ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ባለቤት ማን እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲወስን " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ጠይቀዋል ሲልም አክሏል።

በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እየተካሄደ ነው ከሚባለው ህገ ወጥ የወርቅ ማእድን ማውጣት እና ማዘዋወር ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያን በትግራይ ክልል ከኤርትራ በሚያዋስኑዋት አከባቢዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሰፍር በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ለፌደራል መንግስት ጥያቄ እንዳቀረበም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ገልጿል።

እስካሁን በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች ! " - ሰልፈኞች

በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመቐለ ተካሂደዋል።

ሰልፉ የተዘጋጀው በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት አማካኝነት ነው።

ምክር ቤቱ ዛሬ " ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " በሚል መሪ ቃል በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

ሰልፈኞቹ ፦

- ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሱ !
- ህገ-መንግስት ይከበር !
- ፍትህ ለእህቶቻችን ነፃነት ለሁሉ !
- ሂጃብ መልበስ ሃይማኖታዊ መብትና ግዴታ ነው !
- ሂጃቤ መልኬ ነው !
- የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር !
- ሰላም እና ፍትህ ለትግራይ !
- መብታችን ይጠበቅልን !
- ከተበዳዮች ጎን እንቁም !
- ፍትህን እንጠይቃለን !
- ከሂጃባችን ጋር ታግለናል፤ ሂጃባችን ለብሰን እንማራለን !
- ሂጃባችን ምርጫችን እና መብታችን ነው !

... የሚሉና እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።

በመቐለ ሮማናት አደባባይ ለተሰባሰቡት ሰልፈኞች መልእክት ያስተላለፉት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዜዳንት ሸኽ አደም ዓብደልቃድር  ፥ " ትግራይ የሃይማኖቶች የመቻቻል የነፃነት ተምሳሌት ነች፤ ይሁን እንጂ ይህንኑ ስልጡንነት ወደ ኋላ በሚመልስ መልኩ ልጆቻችን ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ ከዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እንዲቀሩ ተደርገዋል "  ብለዋል።

ችግሩ ሳይባባስ እንዲፈታ ለሁለት ወራት በላይ የተለያየ ጥረቱ መደረጉ ያወሱት ፕሬዜዳንቱ  " ትምህርት ቤቶቹ የክልሉ እና የአገሪቱን ህግ በማክበር የሂጃብ ክልከላውን በአጭር ጊዜ ማንሳት አለባቸው ፤ ጥያቄያችን በአጭር ጊዜ ካልተመለሰ ግን ጥያቄያችን እስከ መጨረሻው ድረስ በሰላማዊ መንገድ እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ክርስትያን ወንድሞቻችን ችግሩ ክጅምሩ እንዲፈታ ብዙ ጥረት  አድርጋችሃል " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስም የጀመራችሁት ትግል ተጠናክሮ ይቀጥል " በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም የሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ጉዳዩ ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት እንዳያመራ የሚያስገነዝብ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትምህርት ገበታቸው የተስተጓጎሉ ሴት ተማሪዎች መካካሻ ትምህርት እንዲያገኙ ያለሙ የሚያወሱ 12  ጥሪዎች እና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ መልእክቶች ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር በማቅረብ እና  በማስተላለፍ ከረፋዱ 4:30 ሰልፉ ተጠናቋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የከተማዋ የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥበቃ ያደረጉ ሲሆን በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፥ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ክልከላ አድርገዋል የተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የጋራ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል።

ት/ቤቶቹ ምን አሉ ?

" 1. የሴት ሙስሊም ተማሪዎች የሂጃብ አጠቃቀም አስመልክቶ በትግራይ ያለው ህግ እና አተገባበሩ ምን ይመስላል ?

ትምህር ቤቶቻችን የትግራይ ትምህርት ቢሮ በ1995 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ነው እየተጠቀሙ ያሉት ። አዲስ ፖሊሲ ወይም መመሪያ እና ደንብ በትምህርት ሚንስቴር ከወጣ ደግሞ ከትምህርት ቢሮ ጋር ተነጋግሮ ይህንን መመሪያ እና ደንብ ተጠቀሙ ብሎ ይልክልናል ። እኛም ተግባራዊ እናደርጋለን። ይህን ባለልሆነበት ' እህያውን ፈርቶ ዳውላውን ' የሆነ ጥያቄ እና ጫና ግን ግራ የሚያጋባ ነው።

በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደግሞ ተማሪዎች መምህራን ወላጆች ተወያይተው ያፀዱቁት ላለፉት 22 ዓመታት እየተጠቀሙት ያለ መመሪያ ደንብ ነው።

በ1995 ዓ.ም የወጣው የትምህርት አደረጃጀት መመሪያ ደንብ ደግሞ እንዲታይ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ከወላጅ ተማሪዎች ጥያቄ ተነስቶ ነበር ። የተነሳው ጥያቄ መሰረት በማድረግ በመመሪያ እና ደንቡ ውይይት ተካሂዶ ታህሳስ 6/2017 ዓ.ም በአንድ ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ፀድቀዋል።

በውይይት እና ድምፅ አሰጣጡ የሙስሊም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ተሳትፈውበት በሙሉ መግባባት መተማመን የተደረሰበት ነው። ታድያ ከአሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሂጃብ ክልከላ ጥያቄ ከየት ? እንዴት መጣ ? ትምህርት ቤቶታቻችን ግራ ገብቶዋቸዋል።

2. የትምህርት ቤት ዩኒፎርም አለባበስ ደንብ እና ስነ-ሰርዓት ምን ይመስላል ?

በ1995 ዓ.ም በፀደቀው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መምሪያ እና ደንብ መሰረት ትምህርት ቤቶቻችን የሚከተለውን የአለባበስ ስርዓት እንዲተገብሩ ያስገድዳል።

የቤተክርስትያን ካህናት እና ዲያቆናት ተማሪዎች ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ነጠላ ማድረግ አይፈቀድም። ወንድ ተማሪዎች ባንከር ፣ ፍሪዝ የፀጉር አቆራረጥ አይፈቀድም።

ሴት ተማሪዎችም ነጠላ ፣ መሃረብ ፣ ሻሽ መጠምጠምያ ፣ ጥቁር የሃዘን ሻርፕ ፣ ሂል ጫማ ፣ ሱሪ ፣ የማንኛውም ሃይማኖት አለባበስ የሚያንፀባርቅ ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድም። ይህ የሆነበት ደግሞ በመካከላቸው የሃብት የሃይማኖት ልዩነት ፈጥሮ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዳይታወክ ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ ህግ ደግሞ ክርስትያን ፣ ሙስሊም መምህር የተማሪ ወላጅ ተወያይተው ያፀደቁት እና የሚተዳሩበት ነው። አሁን ታድያ ምን አዲስ ነገር ተፈጥሮ ነው በትምህርት ቤቶቻችን ላይ የሚዘመተው ? 

 3. ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች መሬት ላይ ያለው መረጃ ምንድነው ?

በአክሱም አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ።  በአራቱ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ ለ12ኛ ክፍል አገር  አቀፍ ፈተና የሚቀርቡት  ተማሪዎች 1044 ናቸው።

ከነዚህ 1044 ተማሪዎች 17 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ 17 ሴት ተማሪዎች ለ22 ዓመታት በቆየው የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ እና ደንብ በመቀበል 7 ሴት ተማሪዎች ፈተናው ለመውሰድ ፎርም ሞልተዋል።

10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ከአክሱም ከተማ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በተዘረጋ የውጭ ተፅእኖ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸው ፎርም አልሞሉም። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ' 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲስተጓጎሉ ተደረገ ' እየተባለ ነው የሚወራው። 142 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን የሌሉ የፈጠራ ድርሰቶች ናቸው።

የተቀሩት 10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ቢሆኑ ፎርም መልተው ለመፈተን ፍላጎት አላቸው ፤ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ ከመቐለ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በየቀኑ እየተደወለ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ የቆየውን አብሮነት እና መቻቻል የሚጎዳ ለህዝብ እና አገር የማይጠቅም መወገዝ ያለበት ተግባር ነው። "

... ሲሉ ትምህርት ቤቶቹ በጥምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በላኩት የፅሁፍ ምላሽ ገልጸዋል።

#UPDATE ትምህርት ቤቶቹ ዘግይተው በላኩት መልዕክት ደግሞ " ሁሉም ተፈታኞች ፎርም ሞልተዋል ለፈተናም ብቁ ናቸው " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle
#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " በየመዋቅሩ ያሉ ም/ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ በመሆኑ መሾምና መሻር አይችሉም " ብሎ የነበረው የትግራይ  ክልልጊዚያዊ  አስተዳደር ምክር ቤቶቹ ህጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ደንብ አፅድቀዋል። የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የወረዳ ምክር ቤቶች የሚያጠናክር እና ህጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ያለውን ደንብ ከሰሞኑን አፅድቋል። " የፀደቀው ደንብ…
የትግራይ ጉዳይ ወዴት ?

በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች እንደሆኑ የገለጹ መኮንኖች ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ' የተዳከመ ' ያሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር መወሰናቸውን ገልጸዋል።

" የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ አሳልፈናል " ብለዋል።

" በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም የሌሎች መጠቀሚያ ሆኗል " የሚል  ክስም አቅርበዋል።

" በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁልፍ ሥልጣን የነበራቸው አመራር እና አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ ውጪ የሕዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው ክህደት በመፈጸም የውጭ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል" ብሏል።

በሕዝብ ጥቅም ላይ ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ " የውጭ ኃይል " ያሉት አካል ማንነትን በተመለከተ በግልጽ የተናገሩት ነገር የለም።

የወታደራዊ አመራሮቹ በሰጡት መግለጫ በስፋት ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ድክመት ሲናገሩ የነበረ ሲሆን " የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም እየሞከረ ነው " የሚል ክስም አቅርበዋል።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ለተካሄደው (በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን) የህወሓት 14ኛ ጉባኤ እውቅና በመስጠት በጉባኤው ውሳኔ መሠረት የጊዜያዊ አስተዳደር የአመራሮች ለውጥ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንን ጉባኤ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እውቅና እንደነፈጉት ይታወሳል።

ወታደራዊ አመራሮቹ " ህወሓት የትግራይን ጊዜያዊ አስተዳደር ለማሻሻል ያሳለፈው ውሳኔ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን " ያሉ ሲሆን " ሠራዊቱን ወክለው በጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት የሆኑትን ግለሰቦች በመገምገም እምነት የሚጣልባቸው ያልሆኑትን በሌሎች እንዲተኩ ወስነናል " ብለዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደሩን በሠራዊቱ ላይ የሚካሄደውን የስም ማጥፋት ዘመቻን መከላከል አልቻለም " በሚል ' በክህደት ' ወንጅለውታል።

በአሁኑ ወቅት በትግራይ ውስጥ ያለው ችግር " ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚሻ ነው " ያሉት አመራሮቹ " ማንኛውም ነገር ከትግራይ ሠራዊት አቅም በላይ አይደለም ይህንን ሰበብ በማድረግ የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን አንቀበልም " ብለዋል።

አመራሮቹ በደብረፅዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን በግዚያዊ አስተዳደር ያለው 50+1 ድርሻ እንዲረከብ እንደሚፈልጉ ተናግረዋን።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ኃይሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር እንደሆኑ የገለጹት መኮንኖቹ በግልጽ ለደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ቡድን ያደላ አቋም ይዘዋል ፤ ይህ ደግሞ አሁን ላይ በክልሉ ያለውን ሁኔታ አስፍሪ አድርጎታል የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ መመልከት ችለናል።

ህወሓት በአቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሁለት ተከፍሎ ላለፉት ወራት እጅግ በጣም በከረረ የመግለጫ እና የሚዲያ ምልልስ ላይ ሲሆን የታጣቂ ኃይሎች እስካሁን በክልሉ ጉዳይ በይፋ አቋማቸውን ሲገልጹ አልታዩም ፤ የዛሬው ለደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ያደላ የድጋፍ መግለጫ ጉዳዩ ወዴት ያመራ ይሆን ? የሚል ስጋት ደቅኗል።

ትግራይ በርካቶች ያለቁበትን እጅግ አስከፊ የሆነ ጦርነት አስተናግዳ ከህመሟ  ገና ያላገገማች ሲሆን አሁን በክልሉ ያለው መካረር መፍትሄ አለማግኘቱ ብዙዎችን እያሳዘነ ይገኛል።

#BBCTigrigna
#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia