TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " እዚህ ላይ ባይገታ እሳቱ ሰፊ አካባቢዎች ላይ  ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ሃብትም ይወድም ነበር " - አቶ ፍቅሬ ግዛው በመርካቶ ሸማ ተራ የደረሰው ውድመት አሳዛኝ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው አሁናዊ ሁኔታውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኮሚሽነር ፍቅሬ ፤ " አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ፤ የማጥፋትና…
🔈#መርካቶ

" እኔ የመርካቶ ልጅ ነኝ፤ እዛውም ነው የምሰራው።

ዛሬ በአይኔ ያየሁት የእሳት አደጋ እጅግ አስከፊ ነው።

በጣም ብዙ ንብረት ወድሟል። የአላህ ጥበቃ ሆኖ እኔ በአካባቢዬ ላይ የሰው ህይወት አልተጎዳም።

ነገር ግን በእሳት አደጋው እጅግ በጣም አዝነን እያለ ተጨማሪ ሃዘን የፈጠረብን ብዙ አለ።

አንዱ የተለያዩ አካላት ለዝርፊያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው።

አንዳንድ ሰው በዚህ የከፋ ጊዜ አብሮ ተጋግዞ እሳቱን ማጥፋት ሲገባው የራሱ ያልሆነን ንብረት ለመዝረፍ ሲሯሯጥ ማየት እጅግ ያሳዝናል።

ሌላው በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተከታይ ለማፍራት ሲባል ያልተባለውን በማለት፣ ያልተደረገውን ተደርጓል በማለት ' ላይክ ፣ ሼር ፣ ፎሎው ' አድርጉን እያሉ በዚህ የችግር ወቅት ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ሰዎችን መመልከቴ አሳስዝኖኛል።

አንዳንዶቻችን ህሊናችንን በዚህ ልክ ማጣታችን እጅግ አሳፋሪ ነው። ነገ እኛን ምን እንደሚገጥም እኮ አናውቅም።

ይህ ከባድ አደጋ እውነተኛ መንስኤው እና የጉዳቱ መጠን በፍጥነት እንዲጣራልን እንፈልጋለን።

ብዙ ለፍቶ አዳሪ ዜጋ እጅግ የደከመበት ፣ የለፋበት ንብረቱ በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል። " - ሃሚ (
መርካቶ)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነጋዴዎች #ደረሰኝ #መርካቶ

" ደረሰኝ መቆረጥ አለበት በዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለውም " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በተለይ በግዙፉ የገበያ ማዕከል ' መርካቶ ' በንግድ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ነጋዴዎች ሱቅ የመዝጋትና ስራ የማቆም እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ሰሞነኛውን የመርካቶ ገበያ ሁኔታ በተመለከተም ነጋዴዎቹ ከከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተቀምጠው ነበር።

በውይይቱ በነጋዴዎቹ በኩል በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው ነበር። ለተነሱት ጥያቄዎች የመንግሥት አካላት ምላሽ ሰጥተዋል።

ነጋዴዎች ሃሳባቸው ፣ ጥያቄያቸው፣ ቅሬታቸው ምንድነው ?

➡️ ደረሰኝ መቁረጥ ፣ ግብር መክፈል ለሀገር ወሳኝ ፤ ለራስም ይጠቅማል። ግን አከፋፈሉ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

➡️ እኛ ስንገበያይ ደረሰኝ እናገኛለን ወይ ? አንዳንድ ምርት የሚነሳው ከገበሬ ነው። ከገበሬ ነጋዴ ይሰበስባል ይከፍላል፣ ተረካቢው ይረከባል ይከፍላል፣ ተጭኖ ይመጣል እኛ እንረከባለን ይሄ ሁሉ ይከፍላል ብዙ ነገር ነው ያለው። የቆረጠው ይቆርጥልናል የሌለውን ንግድ ፍቃድ እናያይዛለን። እንዲህ ስንሰራ ነው የቆየነው።

➡️ ሁሉም እየመጣ ባለድርሻ ነኝ ይላል።
መርካቶ እንደምንታመስ ያውቃል ሌባው ይገባና " ሄደህ 100 ሺህ ብር ከምትቀጣ ለኔ ይሄን ስጠኝ " ይላል።

➡️ እቃው በደላላ ነው የሚመጣው ፤ ድሮ አስመጪ በእያንዳንዱ ሱቅ ሄዶ እቃ ይበትን ነበር አሁን ግን አስመጪው ለደላላ፣ ለቤተሰብ ፣ ለዘመዱ ፣ ለጎረቤት፣ ለጓደኛ ነው የሚሰጠው። እቃው ይመጣና በተለያየ መጋዘን ይቅመጣል ከዛ በስልክ ነው ልውውጥ የሚደረገው ነጋዴው ደላላውን ' ደረሰኝ ስጠኝ ' ካለው ነገ እቃ አይሰጥም።

➡️ ቁጥጥር እየተባሉ የሚመደቡ ሰዎች ባጅ የላቸው፣ ምናቸውም አይታውቅ፣ ሱቅ የሚገቡት እንደ ሌባ 3 እና 2 እየሆኑ ነው ስለዚህ ህጋዊ ይሁኑ ህገወጥ ምናቸው ይለያል ?

➡️ ባልተማከለ ሲስተም ውስጥ ነው ያለነው። ደረሰኝ አልቆረጣችሁም በሚል መቶ ብር አትርፈን 100 ሺህ ብር ነው የምንጠየቀው።

➡️ እስቲ ኢንዱስትሪውን ተቆጣጠሩ ደረሰኝ ቼክ ይደረግ የሚወጣው አንደርኢንቮይስ ከሆነ በምን አግባብ ነው ነጋዴው የሚጠየቀው ?

➡️ " ደረሰኝ ቁረጡ ደረሰኝ ቁረጡ " ሲባል ሌላ ነገር ነው የሚመስለው ደረሰኝ ይዞት የሚመጣው ገንዘብ ነው። መጀመሪያ የንግድ ስርዓቱ መስተካከል አለበት።

➡️ ለ100 ሺህ ብር ቅጣት በዚህ ፍጥነት ከተሰራ ነጋዴውን ለማገዝ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠቱን ዕድሎች ተፈጻሚ ለማድረግ ለምን አልተቻለም ?

➡️ አሰራሩ እኮ ብዙ ነው። አልታየም። እንደ ከተማ አንድም አስመጪ የለም። አስመጪዎቹ '
መርካቶ መጥተን አንሸጥም ጅግጅጋ መጥታችሁ ግዙ ' ይሉናል። በደረሰኝ ስንት ስቃይ ነው ያለው። እዛ ተኪዶ ነው ሚገዛው ? እሺ እዚህ ስናመጣ ገቢዎች ላይ ብዙ ነገር አለ ፤ ደረሠኝ ይጥላሉ፣ ' አንቀበልም ' ይላሉ የት እንሂድ ?

➡️ አሰራሩ ላይ ትልቅ ችግር አለ።

➡️ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ አስመጪዎች ደረሰኝ ይሰጣሉ ወይ ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።


ለነጋዴዎች ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ምን መለሱ ?

🔴 የገቢዎች የቁጥጥር ሰራተኞችን በተመለከተ መታወቂያ አላቸው፣ 3 እና 4 ሆነው ነው የሚገቡት። መታወቂያ የሌለው ካለ ህገወጥ አጭበርባሪ ነው ተከላከሉት።

🔴 " የገቢዎች ሰራተኛ ነን " ብለው ሲያጭበረብሩ የተያዙ ሰዎች አሉ።

🔴 ለገቢዎች ሰራተኞች መታወቂያ ተሰጥቷል። መታወቂያ ማሳየት አለባቸው። እናተም ጠይቋቸው።

🔴 ደረሰኝ ላለመቁረጥ የሚሰጡትን ምክንያቶች በጋር እየተነጋገርን እንፈታለን እንጂ ደረሰኝ መቁረጥ እንዲቆምላችሁ የምትጠይቁትን ጥያቄ መንግስት መመለስ አይችልም። ይሄን በግልጽ እወቁት።

🔴 በገቢዎች ውስጥ ያሉ ችግሮች ይታወቃሉ መፈታት አለባቸው። ከብልሹ አሰራር፣ ከሌብነት ጋር በተያያዘ የተነሱ ችግሮች ይታረማሉ።

🔴 ቫትን በተመለከተ በአዲሱ አሰራር 7 ሺህ ብር ነው የቀን ግምቱ የተቀመጠው። ቀደም ሲል ቫት የነበረ ወደ ታች ሊወርድ አይችልም። በቀን 7 ሺህ ብር የሚሸጥ ሰው ምን ያክል ነው የሚለውን እናተው ታውቃላችሁ። ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው ቫት ውስጥ መግባት እያለበት ቫት ውስጥ ያልገባው ነጋዴ በተለይ
መርካቶ እሱ ባለመግባቱ በሚሸጠው እቃ ላይ የዋጋ ልዩነት እየመጣ ስለሆነ ቫት ውስጥ መግባት ያለበትን ቫት ውስጥ እያስገባን ነው።

🔴 ቫት ውስጥ የነበረ ነጋዴ ልወርድ ይገባል ብሎ ተጨባጭ ማስረጃ ካቀረበ ይታያል። አሁን ባለው የዋጋ ንረት እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እንጂ እላይ የነበረው ወደ ታች አይወርድም።

🔴 የቁጥጥር ስርዓቱ እየጠበቀ ነው የሚሄደው።

🔴 እኛ ስለትላንቱ አለነሳንም አሁን ግን
መርካቶ የሚደርገው ግብይት በደረሰኝ እና በደረሰኝ ብቻ መሆን አለበት። ይህን የሚያደርገውን ነጋዴ እንደግፋለን።

🔴 ነጋዴው በህጋዊ መንገድ ይጠቀም አልን እንጂ ነጋዴውን የሚያስቀይም ፣ የሚያሳድድ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈልግ አካል የለም።

🔴
መርካቶ የሚደረገው እንቅስቃሴ በክልል ጥያቄ ያስነሳል። መረካቶ ደረሰኝ ስለማይቆረጥ የንግዱ ማህበረሰብ ክልል ሄዶ ሲነግድ ደረሰኝ አቅርቡ ሲባል " ያለ ደረሰኝ ነው የገዛነው እዛ ደረሰኝ አልተቆረጠም " የሚሉ አሉ።

🔴 የዚህ አመት እቅዳችን ግዙፍ የሆነ ገቢ ለመሰብሰብ አቅደናል። ይህን የምናደርገው የታክስ ቤዛችንን በማስፋት፣ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ በመቀየር ነው።

🔴 ኢ-መደበኛ እናሳድዳለን አላልንም ግን ወደ መደበኛ ይግባ እያልን ነው።

🔴 ብዙዎቻችሁ (ነጋዴዎች) ያነሳችሁት ጥያቄ ደረሰኝ እንዳይቆረጥ የሚጠይቅ ዝንባሌ አለው። " ደረሰኝ አያስፈልግም " አትሉም ግን ጅምላውን፣ አከፋፋዩን ፣ አምራቹን ቅድሚያ ስጡ ነው የምትሉት። ጅምላውም ላይ፣ አከፋፋዩም ላይ ፣ አምራቹም ላይ እንሰራለን ቸርቻሪም ላይ እንደዛው ይሰራል። ሁሉም ደረሰኝ መቁረጥ አለበት።

🔴 ደረሰኝ ለመቁረጥ የማይስችል ሁኔታ ካለ ማስረዳት ነው እንጂ " ደረሰኝ አንቆርጥ " የሚል እሳቤ ተቀባይነት የለውም።

🔴 በደረሰኝ መቆረጥ አለበት ምንም አይነት ድርድር የለውም በዚህ ጉዳይ። እኛ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ እናስገባለን።

🔴 አቤቱታ ካላችሁ በማንኛውም ጊዜ አቅርቡ። ገቢዎች አካባቢ ያለውን ነገርም እንፈትሻለን።

#AddisAbaba #Merkato

@tikvahethiopia