TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የ #AUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ። በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መረጃ ፥ የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ ጋር ውጤታማ ውይይት…
#Ethiopia 🤝 #Somalia

በሶማሊያ በሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት ተሰማርቶ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሁኔታን በተመለከተ አሠራር ለመዘርጋት የሁለቱ አገራት የጦር አዛዦች ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በኢትዮጵያው መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች የመከላከያ ሠራዊት አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኦዳዋ ዩሱፍ ራጌ መካከል የተደረሰው ስምምነት በሶማሊያ ያለው የኢትዮጵያ ጦር ስምሪትን፣ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም አጠቃላይ ክንዋኔዎች የሚመለከተውን 'ስታተስ ኦፍ ፎርስ አግሪመንት' ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው።

አንዲት አገር ጦሯን በሌላ ውጭ አገር በምታሰማራበት ወቅት የጦሩ ስምሪት፣ ተግባራት፣ ኃላፊነት፣ መብቶችን የሚመለከተው በአገራቱ መካከል የሚደረስ አሳሪ (ሕጋዊ ስምምነት) ስታተስ ኦፍ ፎርስ አግሪመንት ይሰኛል።

ይህ 'ስታተስ ኦፍ ፎርስ' ስምምነት በአውሮፓውያኑ 2023 በአገራቱ መካከል የተፈረመው የመከላከያ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ዋና አካል እንደሚሆን ተነግሯል።

በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራ ልዑክ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የካቲት 15/2017 ዓ.ም. ባደረገው የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ይህንን ስምምነት ጨምሮ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሶማሊያ እና በቀጠናው ሰላም፣ ደኅንነት፣ ፀጥታ እና የመረጋጋት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ሁለቱ የጦር አዛዦች የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ጅማሮ አድንቀው ከዚህ ቀደም በነበረው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት አትሚስ ስኬቶች ማስቀጠል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በኤዩሶም ስምሪት ላይ እንዲካተት የጦር አዛዦቹ በዚህ ወቅት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ውዝግብ በአንካራ ስምምነት መፈታቱን ተከትሎ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ውስጥ ላለማካተት አሳልፋው የነበረውን ውሳኔ ልትቀለብስ እና በተልዕኮው ለማካተት እያጤነች እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተዘግቦ ነበር።


#SomaliaNationalTV #BBCAMAHRIC

@tikvahethiopia
ወደ አቢሲንያ ፖስ ማሽን ስልክዎን ጠጋ ብቻ በማድረግ ይክፈሉ !
ፈጣንና አስተማማኝ የሆኑት የአቢሲንያ ባንክ ፖስ ማሽኖች ሁሉንም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶች የሚቀበሉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የተለያዩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን ያስተናግዳሉ። እርስዎ ብቻ ይፈልጉን - በየቦታው አለን! የሁሉም ምርጫ መሆናችን በምክንያት ነው!
#BankOfAbysinia #POSMachine #DigitalPayments #CashlessTransactions
#BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Ethiopia #Somalia

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

ሁለቱ ሀገራት ገብተውበት ከነበረው የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ውጥረት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነው።

የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ መሐሙድም ቱርክ ሁለቱን ሀገራት አንካራ ላይ ካስማማች በኋላ ባለፈው ጥር 3 ቀን አዲስ አበባን ጎብኝተዋል።

አስከትለውም በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ታድመው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋግረዋል።

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በጋራ በወጣው መግለጫ " ይህ ጉብኝት ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የተደረጉ ተከታታይ ግንኙነቶችን የተከተለ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትም ወደ መደበኛ ሁኔታ የሚመልስ ነው " ብሏል።

ሁለቱ መሪዎች ለጋራ ጥቅም ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ስለማረጋገጣቸው እና በዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትብብር " መተማመንን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል " ተብሏል።

የዚህ ጉብኝት እንደምታን በሚመለከት ቃላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡት ፤ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት የአፍሪካ ጉዳዮች የሥራ ክፍል ኃላፊ እና ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ግዛቸው አስራት ፥ ሁለቱ ሀገራት መተማመን በሚያስችል ሁኔታ መነጋገር የሚችሉበት ዕድል እንደሚሆን ገልፀዋል።

" የቴክኒክ ቡድኑ (የአንካራ ስምምነት) ከሁለት ሳምንት በፊት አንካራ ላይ ተገናኝቶ ሲነጋገር ተመልክተናል። መስማማቶች እና መግባባቶች ላይ የደረሱበት፣ መተማመን በሚያስችል ሁኔታ ንግግሮች እያደረጉ ያሉበት ሂደት ነው " ብለዋል።

" የቱርክ መንግሥት አካባቢውን ካላስፈላጊ ውጥረት ታድጓል "  ያሉት ተመራማሪው እንዲህ ያሉ መልካም ልምዶች በዚህ ቀጣና ብዙም አይታዩም ብለዋል። ይህን መሳይ የውይይት፣ የድርድር እና የሰላም መንገዶች ሲታዩ ማመስገን ያስፈልጋል ብለዋል። 

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ ጥቅሞችን በማሳደግ፣ ሰላምና ደህንነትን በማስፈን እና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ለዜጎቻቸውና ለሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውም ጉብኝቱን ተከትሎ በወጣው የጋራ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

ዶክተር ግዛቸው አስራት " ቀጣናዊ ትብብርን " የተመለከቱ ውይይቶች እንደሚኖሩ ገልፀዋል።

የዛሬውን ጉብኝት በሚመለከት አስቀድመው የወጡ ዘገባዎች ሞቃዲሾ ውስጥ ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ መደረጉን ያመለክታሉ።
#DW

@TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓድዋ እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ ! " ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት መቼ ተነሱና የወዳደቁት ምስጋና ለእነርሱ ለዓድዋ ጀግኖች ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች የጥቁር ድል አምባ ዓድዋ አፍሪካ እምዬ #ኢትዮጵያ ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ !!  " - ጂጂ መልካም የድል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ !! @tikvahethiopia
#ዓድዋ129

ዛሬ የካቲት 23 መላ የኢትዮጵያ ህዝብና ጀግኖች አርበኞች በአንድነት የኢጣሊያንን ቅኝ ገዢ ጦር ዓድዋ ላይ ድል ያደረጉበት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

ንጉሰ ነገስት አፄ ሚኒልክ የመሯቸዉ ኢትዮጵያዉን ጀግኖች ኢትዮጵያን የወረረ ጠላታቸዉን ዓድዋ ላይ መትተዉ አሳፍረዉ፣ አዋርደው ፣ አንገት አስደፍተው የመለሱት ልክ በዛሬው ዕለት ከ129 ዓመታት በፊት ነበር።

#ዓድዋ
#የመላአፍሪካውያንድል
#Ethiopia

@tikvahethiopia
ወጣትነት በዘህራህ ልዩ ከወለድ ነጻ የሴቶች ቁጠባ ሒሳብ ሲታገዝ፣ የስኬት ጉዞ ከመቼውም ይልቅ ይፋጠናል!

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#Ethiopia #Turkiye

ከቱርኪዬ የመጡ የሀኪሞች ቡድን በቅዱስ ጳዉሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት 3 የኩላሊት ንቅለ ተከላ በተሳካ ሁኔታ እንዳካሄዱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን የተመራ ልኡካን ቡድን የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለማቋቋም የሚስችል ፕሮጀክት ላይ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር ተወያይተው ነበር።

የህክምና ባለሙያዎቹ ቡድን ላደረጉት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል።

#MoH

@tikvahethiopia
#Ethiopia❤️

ኢትዮጵያ 🇪🇹 ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን አጠናቀቀች !

በቻይና ናንጂንግ ከተማ በተካሄደው 20ኛው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ኢትዮጵያ አምስት ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ አጠናቀቀች።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በውድድሩ ፦

  ሁለት የወርቅ እና
ሶስት የብር ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ለተከታታይ አራት አመታት የወርቅ ሜዳልያውን ማሸነፍ ችላለች።

ኢትዮጵያ በውድድሩ የሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ 1️⃣ኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ ከአለም 3️⃣ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሜዳልያ ያስገኙ አትሌቶች እነማን ናቸው ?

🥇 ጉዳፍ ፀጋይ ( 1500 )

🥇 ፍሬወይኒ ኃይሉ ( 3000 )

🥈 በሪሁ አረጋዊ ( 3000 )

🥈 ንግሥት ጌታቸው ( 800 )

🥈 ድርቤ ወልተጂ ( 1500 )

Via
@Tikvahethsport  
#አቢሲንያ_ባንክ
በረቀቀ ቴክኖሎጅ የተዘጋጀውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ
- በ5 የቋንቋ አማራጭ
- ከአቢሲንያ ወደ አቢሲንያ አካውንት ያለምንም ክፍያ እና ያለገደብ ገንዘብ ለማስተላለፍ
- ኪውአር ስካን አገልግሎት
ለማግኘት ዛሬውኑ ወደ አቅራቢያዎ ቅርንጫፍ በመሄድ አገልግሎቱን ያግኙ #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
አቢሲንያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ

ገደቡም ክፍያውም ተነስቷል!

ውድ ደንበኛችን! የባንካችንን አዲሱን የሞባይል መተግበሪያ ተጠቅመዉ ከሂሳብዎ ወደ ሌላ የባንካችን ሂሳብ ገንዘብ ያለ ገደብ እንዲሁም ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይችላሉ። #Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ