TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቢልለኔ ስዩም የፌስቡክ ገፅ የላትም!

#Billene_Seyoum ይህ የfacebook page #ሀሰተኛ ነው። ይህንን ጉዳይ የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከዚህ ቀደም ከራሳቸው አንደበት አረጋግጧል። ዋልታና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጨምሮ በርካቶች የቢልለኔ ስዩምን ፌስቡክ በመጥቀስ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የፊታችን ማክሰኞ የዩኔስኮን ፌሊ ሁፉዌ ብዋኚን የሰላም ሽልማት እንደሚቀበሉ እየገለፁ ነው።

ለመረጃ ያህል...

የፊታችን ማክሰኞ ጁላይ 9 የሽልማት ስነስርዓት #አይካሄድም። ጠቅላይ ሚንስትሩም ወደ ፈረንሳይ ፓሪ አይጓዙም። እርግጥ ነው ሜይ 2 ቀን 2019 ዩኔስኮ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም ሽልማቱን ማሸነፋቸውንና ጁላይ 9 ቀን ሽልማቱን እንደሚቀበሉ ገልፆ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ግን ለጊዜው የሽልማቱን መስጫ ቀን "ላልተወሰነ" ጊዜ ማራዘሙን ለማረጋገጥ ተችሏል። /#Petros_Ashenafi/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ #ምርጫ_እንዳይካሄድ ተወስኖባቸዋል።

- ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር አይተው ተገኝቷል፤ በዚህ ምክንያት 3 አስፈፃሚዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ደብዳቤ ተፅፏል።

ደምቢያ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን መነካካት ፣ መክፈት በጥብቅ የተከለከለ የወንጀል ተግባር በመሆኑን አስፈፃሚዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው ተልኳል።

በደምቢያ ምርጫ ክልል ምርጫው #አይካሄድም

- ተውለደሬ 1 እና 2 ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያሉእጩዎች እነማን እንደሆኑ ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ያሉትን እጩዎች የማየት (ፓርቲዎች ቅሬታ አለን ስላሉ ነው እዩ ተብለን ነው) በሚል ተክፍቶ ታይቷል።

በዚህ ምክንያት ተውለደሬ 1 እና 2 ነገ ድምፅ አይሰጥም፤ ታግዷል።

- ግንደበረት (ኦሮሚያ) ነገ ድምፅ #አይሰጥም ፦ ድምፅ የማይሰጥበት ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀት እና ቁሳቁስ ስለተከፈተ ሳይሆን የአስፈፃሚዎች እጥረት ነበር። ከዚህ ውጭ ግን ወረዳው አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ ለማስፈፀም ለማሰማራት ሲል በመገኘቱ ገንደበረት ላይ ድምፅ አይሰጥም።

- ነገሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ-ኦሮሚያ) ፦ በምርጫ ክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ቦርዱ ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮታል።

#TikvahEthiopia #SolianaShimeles

@tikvahethiopia