TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ልጆቹ በስህተት ነው የተለቀቁት፤ እየታወቀ አይደለም!" - አቶ አይዛክ ሀሰን (የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ክትትል ሂደት መሪ)

(በአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

ከሞያሌ ለይቶ ማቆያ የተለቀቀው ግለሰብ ከወር በፊት ነበር ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው። በቦረና ዞን የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ባልደረባ አቶ አብዱዋ ዋቆ ግለሰቡን ከሌሎች 40 ሰዎች ጋር ወደ ለይቶ ማቆያ ያስገቡት የሱማሌ ክልል የጤና ባለሞያዎች ናቸው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ያኔ ከገቡት 40 ሰዎች በበሽታው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች ናሙና ለምርመራ የተላከ ቢሆንም የሱማሌ ክልል የጤና ባለሞያዎች ውጤቱ ሳይመለስ ሰዎቹን ለሳምንታት አቆይተዋቸው አርብ ዕለት ወደ ሀዋሳ እንደመለሷቸው ተናግረዋል።

የቦረና ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሮባ ዴንጌ ሰዎቹ የተሳፈሩባቸው የህዝብ አውቶብሶች መለየታቸው፤ ያቤሎ ሲደርሱ ያረፉበት ሆቴል ፀረ ተባይ መድሃኒት መረጨቱን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አቶ ሮባ በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ወደ #ሀዋሳ ያመሩት 40 ሰዎች፣ በዞኑ የተገናኙት ሌሎች ሰዎች በሙሉ ተለይተዋል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል የሞያሌ ወረዳ የጤና ቢሮ ክትትል ሂደት መሪ አቶ አይዛክ ሀሰን "ልጆቹ #ተሳስተው ነው የተለቀቁት፤ እየታወቀ አይደለም ፤ ኳረንቲን 14 ቀን ቢሆንም ልጆቹ 18 ቀን ነበር የቆዩት ፤ ውጤቱ ስለዘገየ ነው። ልጆቹ የተለቀቁት እየታወቀ አይደለም፤ በስህተት ነው" ብለዋል።

አቶ አይዛክ አንድ ላይ ከነበሩት መካከል የ4 ሰዎች ናሙና ለምርመራ የተላከ መሆኑን ገልፀው አሁን ሁሉም በደቡብ ክልል በለይቶ ማቆያ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሞያሌ በነበሩበት ወቅት 2 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እነሱን ሲንከባከቡ የነበሩ አጠቃላይ 9 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንደገቡ መደረጉን አስረድተዋል።

@tikvahethiopiaBot
#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (#ሀዋሳ እና #መቅደላ_አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ  በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...

በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።

እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።

" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።

ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።

የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።

እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ በድሶ አዲሳ  ፦

" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።

ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።

ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።

ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።

እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።

ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "

ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።

እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
#ሀዋሳ

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀምሌ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ለበዓሉ ሰላማዊነት ከመምሪያውና 8ቱም ክ/ከተማ ፖሊስ ማናጀመት ፣ከ8ቱም ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች፣ ለፀጥታው አጋዥ ከሆኑ ሀይሎች ፣ ከሀይማኖት አባቶች ፣ ከሁቴል ባለቤቶች ፣ከየክፍለ ከተማ የተደራጅ ማህበራት ጋር ውይይት ተደርጓል።

ፖሊስ ከፀጥታ ኃይሉ እና ከአጋዥ ኃይሎች በተጨማሪ በከተማው በተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች  የፀጥታውን ስራ አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጾ የደህንነት ካሜራዎች ተደራሽ ባልደረገባቸው ቦታዎችን ካሜራ የመግጠም ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል።

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚያን በጠቅላላ አከባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁና የወንጀል ድርጊትም ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲጠቁሙ መልዕክት ተላልፏል።

በተመሳሳይ የሲዳማ ክልል የፀጥታ ግብረሃይል ፤ በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቅ የፀጥታ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን እና ለፀጥታ ኃይሉ ስምሪት መሰጠቱን አሳውቋል።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት
ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህ መነሻ ከሐምሌ 18/04/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ፦
1. ከሎጊታ - ሱሙዳ ገብርኤል
2. ከማር ስል ቤተክርስቲያን - ሱሙዳ ገብርኤል
3. ከዋርካ አደባባይ - ሱሙዳ ገብርኤል
4. ከዳሽን- ሱሙዳ ድረስ ያሉ መንገዶች በዓሉ ተከብረው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ ማንኛውን ጥቆማ ካለው በ0462209164  እና 046 212 2468 ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን  እንዲሁም በ0462201046 ለሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ ጥቆማ መስጠት ይችላል።

ሀዋሳ የሚከበረው የሀምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር እጅግ በርካታ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #ቁልቢ #ሀዋሳ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓልን ተከትሎ ፤ ከታህሳስ 17 እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ባሉት ቀናት ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል ነው ተብሏል።

ታህሳስ 19 የሚከበረው ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጊዚያዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል አሳውቀዋል።

ለበዓሉ የሚያቀኑ አሽከርካሪዎች አካባቢው ዳገት፣ ቁልቁለት እና ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚበዛው ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የትራፊክ ህግና ደንብ አክብረው እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ተለልፏል።

ከታህሳስ 17 እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ባሉት ቀናት ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪ ፦

- የጸጥታ አካላት ቋሚና ተንቀሳቃሽ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።

- በበዓሉ ወቅት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ሲያዙ ፈጣን ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በአቅራቢያ ተቋቁሟል።

- ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ተቋቁሟል።

የበዓሉ ታዳሚዎች ንብረቶቻቸውን #በጥንቃቄ እንዲይዙ መልዕክት ተላልፏል። ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳይ ካጋጠመ በአቅራቢያ ላለ የፀጥታ አካል ጥቆማ መስጠት ይቻላል።

በተመሳሳይ ፤ በሀዋሳ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርዔል ዓመታዊ የንግስ በዓልን አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ብሎም ደህንነታቸው ተጠብቆ በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሁሉም አካል በትብብር እየሰራ ነው ተብሏል።

ስርቆት፣ ያለአግባብ ዋጋ ጭማሪ ፣ ማጭበርበር እንዳይፈፀም የጥንቃቄ ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በዓሉ በሚከበርበት ዕለትና ሥፍራ ወንጀል ተፈፅሞ ቢገኝ አፋጣኝ ፍትህ የሚሰጥ ጊዜያዊ ችሎት መሰየሙ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
#ሀዋሳ

" ... በነዳጅ እጥረት ስራችንን መስራት አልቻልንም። ተሰልፈን ነው የምንውለው " - አሽከርካሪዎች

" ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ ነው ችግር የተፈጠረው " - የከተማው ገበያ ልማት

በሀዋሳ ከተማ የነበረዉ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና ሰልፍ ተስተካከለ ተብሎ ጥቂት ጊዜያት ሳይቆይ ድንገት ችግሩ ማገርሸቱን ተከትሎ መጨረሻ የሌላቸው የሚመስሉ ሰልፎች በየማደያዉ እየታዩ ነዉ።

በከተማው ኑሯቸዉን ከህዝብ ትራንስፖርት ጋር ያደረጉ አሽከርካሪዎች ፤ " አሁን አሁን በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች እንደሚሉት ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ይገልጻሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

ችግሩ ወደፊት ይቀረፋል የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ገልጸዋል።

ለህዝብ አገልግሎት የማይሰጡ ታክሲዎች ሰልፍ ዉስጥ እየገቡ ስለመሆኑ መረጃዉ እንዳላቸውና እነዚህን ተሽከርካሪዎች ለመቆጣጠር ከከተማዉ መንገድ ትራንስፖርት ጋር በመነጋገር እንቅስቃሴ መጀመሩን  ጠቁመዋል።

ሀዋሳ ከተማ እጅግ በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ያሉባት ሲሆን ነዳጅ የሚቀዳው ግን በተለያየ የአሰራር ዘዴ ነው። ለአብነት ዛሬ አንዱ ማደያ ከቀዳ ፣ ነገ እዛ ላይቀዳ ይችላል። ተገልጋዮች ከተማው ያወጣውን መርሀ ግብር በቴሌግራም በማየት ነው ነዳጅ መቅዳት የሚችሉት።

ከዚህ ባለፈ እሁድ እሁድ እለት ነዳጅ  ማግኘት የማይታሰብ ነው።

በሌላ በኩል ፤ በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ በታሸገ የውሃ ፕላስቲክ እየተደረገ በየሱቁ የሚቸበቸብ ሲሆን ይህም ከመቶ ብር በላይ (110 ብር) ነው የሚሸጠው።

መረጃው አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሟቾች ቁጥር ከ8 ወደ 11 ከፍ ብሏል " - ኢስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ወደ ሐዋሳ ጉዞውን እያደረገ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ትላንት ማምሻውን መነሻውን ከአርባ ምንጭ አድርጎ ወዘ ሐዋሳ እያመራ የነበረ ተሽከርካሪ በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ አስከፊ…
#ሀዋሳ🕯

በቅርቡ ከአርባ ምንጭ ወደ ሐዋሳ ሲመለሱ በዎላይታ ዞን ውስጥ በመኪና አደጋ ህይወታቸዉ ላለፈ የሐዋሳ ከተማ ወጣቶች የሻማ ማብራትና የገቢ ማሰባሰቢያ  ፕሮግራም በከተማ ደረጃ ከንቲባዉ በተገኙበት ተካሄደ።

በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይዎታቸዉ ያለፉ የጤና ቡድን አባላትን ለመዘከር ያለመ የሻማ ማብራትና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተጎጅ ቤተሰቦች ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሲዳማ ባህል ሽማግሌዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በሻማ ማብራት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያዬ መርሻዬ ፤ " እንደሀዋሳ ብቻ ሳይሆን እንደሀገር አልቅሰናል  " ብለዋል።

ከዚህ አይነት አስከፊ የትራፊክ አደጋ ለመዉጣት ጥንቃቄ ብቻ ሳይሆን ጸሎትም ያስፈልገናል ሲሉ ገልጸዋል።

የተጎጅ ቤተሰቦችን ለመደገፍ ለተሰናዳዉ ፕሮግራም በከንቲባዉ ቢሮ 3 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም በግላቸዉ 10 ሽህ ብር በማበርከት ድጋፉን አስጀምረዋል።

ፕሮግራሙን ለመካፈል ተደግፎ የመጣዉና ከአደጋዉ የተረፈዉ ወጣት ፋሲል በበኩሉ ሀዘኑን መቋቋም ከባድ መሆኑን በመግለጽ በእንባ ታጆቦ ወደቦታዉ ተመልሷል።

በእለቱ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ  በጎፈንድሚና ለዚህዉ ተብሎ በተከፈተዉ የባንክ አካዉንት መሰብሰብ ተችሏል።

የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙን ያዘጋጀዉ ኮሚቴ  " በድንገት ያጣናቸዉ ጓደኞቻችን ልጆችና ቤተሰቦች ለመርዳት ሁሉም ወጣት ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጠይቋል።
 
ለዚህ ሲባል የተከፈተዉ የባንክ አካዉንት ቁጥር 1000610475667 መሆኑን ገልጿል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀዋሳ " ... በነዳጅ እጥረት ስራችንን መስራት አልቻልንም። ተሰልፈን ነው የምንውለው " - አሽከርካሪዎች " ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ ነው ችግር የተፈጠረው " - የከተማው ገበያ ልማት በሀዋሳ ከተማ የነበረዉ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና ሰልፍ ተስተካከለ ተብሎ ጥቂት ጊዜያት ሳይቆይ ድንገት ችግሩ ማገርሸቱን ተከትሎ መጨረሻ የሌላቸው የሚመስሉ ሰልፎች በየማደያዉ…
#ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ የህዝብ ትንራንስፖርት አገልግሎት (ታክሲ) የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ፤ " የነዳጅ ጉዳይ ስቃያችንን አበላን ፤ የመፍትሄ ያለህ !! " ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ፤ "ሰርተን ከምንገባበት ለነዳጅ ሰልፍ ቆመን የምንውለበት እየበለጠ ነው " ብለዋል።

የነዳጅ ችግሩ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑም በመግለፅ "
ካልሰራን ልጆቻን ምን ይብሉ ? ፤ እኛስ ምን በልተን እንደር ? ይህ ጉዳይ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።

ከሳምንታት በፊት በዚሁ በሀዋሳ ከተማ ያሉ አሽከርካሪዎች ፤ " በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " በሚል ምሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተው ነበር።

አሽከርካሪዎች ፤ ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ገልጸው ነበር።

በወቅቱ እየተነሳ ላለው ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ፤ ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ችግሩም " #ወደፊት_ይቀረፋል " የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ማመልከታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #ሀዋሳ #ክልከላ

በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ ባለ ሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና የሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር #ተከለከለ

ሰሞኑን በሀዋሳ ከመዝናኛ መልስ እየደረሰ ያለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሲባል ከምሽቱ 3:00 በኃላ ባለሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪው ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦
°  ምክንያት ?
°  ክልከላው ለምን አስፈለገ ?
° በማህበረሰቡ የእለት ተእለት ህይወትስ ላይ የሚያሳድረዉ ጫና አይኖርም ? ወይ ስንል ኢንስፔክተሩን ጠይቋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፤ " ሁሉንም ያደረግነው ለማህበረሰቡ ደህንነት ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እየተስተዋለ ነው " ሲሉ ገልጸው ከአደጋዎቹ አብዛኛዉ በባለሦሰት እግር ባጃጅና በባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል የሚደርስ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በዚህ አመት ብቻ በምሽት በሞተር ሳይክል የደረሰዉ አደጋ የሚያስገርም ቁጥር ያለው ነው " ያሉት ኢስፓክተር ተስፋዬ በቁጥር ስንት ? የሚለውን ወደፊት ዳታውን አጠናቅረዉ ለማህበረሰቡ የማሳየት እቅድ እንዳለቸዉ ጠቁመዋል።

ከአደጋዎቹ ውስጥ በአብዛኛው የሚከሰቱት በምሽት መሆኑን ጠቅሰው ፤ " ጠጥቶ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር  ትልቁ ምክኒያት ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም በመንግስት ሞተር ሳይክሎች ሳይቀር ሶስትና ከዚያ በላይ ሆኖ መንቀሳቀስ አደጋ እየፈጠረ ነው ይህን ችግር ለመቀነስ ሲባል #ክልከላው ወጥቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፤ " የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የወንጀል መፈጸሚያ እየሆኑ ነው " ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ " ለአብነት ኮንትራት ተብለዉ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ እና የሌሎችም ወንጀሎች ምንጭ ሆነው ተገኝተዋል " ብለዋል።

" ጥንቃቄ ለራስ በመሆኑ ማህበረሰቡ ለራሱ ሲባል የወጣዉን ክልከላ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ " ሲሉ አሳስበዋል።

" እለት ተእለት የሚከሰተው ዘግናኝ የትራፊክ አደጋ እንዲቆም የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል " ብለዋል።

ክልከላው የሚያበቃበትን ጊዜን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia