TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሶማሌ ክልል⬇️

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይፈጸምበት ነበር የተባለውን ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራው #ማእከላዊ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት #ተዘጋ

የሶማሌ ክልል መንግስት በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ እየወሰደ ከሚገኘው የለውጥ እርምጃዎች መካከል ባለፉት አመታት በክልሉ ህዝብ ላይ ሲፈጸሙ የነበሩትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ዋነኛው ነው፡፡

የክልሉ መንግስት ካቢኔ ከትላንት ወዲያ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ ባለፉት አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሚታጎሩበትና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸምበት የነበረ ነው በሚል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውን ማእከላዊ ማረሚያ ቤት እንዲዘጋ ወስኗል፡፡

በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፤ ታዋቂ ግለሰቦች ፤ ሙሁራን እንዲሁም ለረጅም አመታት በተለያዩ የአለም ክፍሎች በመዟዟር በክልሉ የሚፈጸሙትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችን ሲቃወሙና ሲታገሉ የቆዩት አክቲቪስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ አብዱላሂ ሁሴንና አክቪስቲስት አብዱረሺድ አሊ ሸአ በተገኙበት ማረሚያ ቤቱ በዛሬው እለት በይፋ ተዘግቷል፡፡

በዛሬው እለት የተዘጋው የጅግጅጋ ከተማ ማእከላዊ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ህጉን መሰረት በማድረግ እንደሚለቀቁም ከክልሉ መንግስት ለኢቢሲ የተላከው መግለጫ ያለክታል፡፡

የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርም በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የማሰቃያ ማዕከሉን መንግስት ለመዝጋት መወሰኑ መልካም እርምጃ ሲል በትዊተር ገፁ አወድሶታል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

"ጠዋት #ከአዲስ_አበባ ተነስቶ መድረሻውን #ድሬዳዋ ያደረገው ባቡር በመጀመሪያ መንገድ #ተዘጋ ተብለን 7:30 እስከ 11 ሰአት ድረስ ቆምን ከዛ 11:45ሲሆን ጉዞ ጀመርን እደገና 1:00 ሲል #የረር ስንደርስ #ግመል_ገጨ ተብሎ እስካሁን ቆመናል። ብዙ ህፃናት በረሀብ እያለቀሱ ነው። እደምናድር ወይም እደምንሄድ የደረሰን መረጃ የለም ማንም #አያናግርንም። አንድ የ4ወር ህፃን እራሱን ስቷል! መረጃው ለሚመለከተው አካል ይድረስ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia