TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
⚫️ #ኢትዮጵያ ⚫️

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ምን ያልተፈጸም ፤ ምንስ ያልተደረገ ግፍ አለ ?

እጅግ በጣም ሚያስደነግጠው እንዲሁም ፍጹም ከሰውነት ተራ እየተወጣ መሆኑን የሚያሳየው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ልክ ጀግንነት ፣ በጎ ተግባር፣ ፍቅርን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ይመስል ግፍና ጭካኔያቸውን በቪድዮ ማስረጃ እራሳቸው ቀርጸው ለትውልድ እያስቀመጡ መሆናቸው ነው።

በእርግጥም እንዲህ እየቀረጹ ማስቀመጣቸው ህዝቡን ለሚፈልጉት ዓላማ ለማነሳሳትና እርስ በርስ ለማባላት፣ ህዝቡን ወደ ግጭት ለማስገባት ሊሆን ይችላል።

በጥላቻ የሚፈጽሙት የግፍ ተግባራቸው አላረካ ብሏቸው ፣ " እዩልን ምን ያህል አውሬ እንደሆንን " የሚለውን ለማሳየትም ይሆናል።

በሀገራችን ፦
🔴 ሰው ከነህይወቱ ሲቃጠል
🔴 በድንጋይ ተወግሮ ሲገደል
🔴 በጅምላ በጥይት ተደብድቦ ወደ ገደል ሲከተት
🔴 አስክሬን ሲጎተት
🔴 አስክሬን አደባባይ ላይ ሲጣል
🔴 ተዘቅዝቆ ሲሰቀል
🔴 በስለት ተቀልቶ ሲገደል
🔴 የጥይት በረዶ ሲዘንብበት ... ኧረ ብዙ ብዙ በቪድዮ ተቀርጾ አይተናል።

ይኸው ዛሬ የሰው ልጅ ልክ እንደ ዶሮ " በስመአብ " ተብሎ ሲታረድ በቁማችን አየን።

ይህ ጭካኔ በማስረጃ በቪድዮ ተቀርጾ የወጣ ነው ለመሆኑ ስንት በቪድዮ ያልተቀረጸ ፣ በየአካባቢው የተፈጸመ ግፍ ይኖር ይሆን ?

እነዚህ ግፍ ፈጻሚ ሰዎች ሰይጣናዊ ስራቸውን በቪድዮ ቀርጸው ማስቀረታቸው በቤተሰብ ፣ በህዝብ ላይ የማይረሳ ቂም፣ ቁርሾና ቁስል ለማኖር ይመስላል።

የትም ይሁን ማንኛውም የግፍ ድርጊት ሲፈጸም ግን የሚቀድመው ድርጊቱን ከልብ አዝኖ ማውገዝ  ነው። ፍትህ ተጠያቂነት እንዲሰፍን መጠየቅ ፤ ለፍትህ መታገል ነው።

ልክ ሰው በሞተ ቁጥር ያለ አንዳች ሀዘን እና መከፋት ወደ ፖለቲካ ንትርክ መግባትና የሰው ደም ፈሶ እንዲቀር ለማድረግ መሯሯጥ የግፍ ግፍ ነው።

ከዚህ ቀደም ብዙ ታዝበናል።

ሰው በግፍ ይገደላል ከዛም ሰዎች በየማህበራዊ ሚዲያ ይመጡና " የኔ ወገን ሰው አይገድልም፤ ፍጹም ነው ፣ ፃድቅ ነው ፣ እንዲህ እንዲያደርግ ተፈጥሮው አይፈቅድለትም " እያሉ ድርጊቱ ያራክሱታል።

ሌላው ወገን ይመጣና በሞተው ንጹህ ሰው ደም ፖለቲካ ይሰራል። በጅምላ ጥላቻውን ይተፋል። በዚህ መንገድ የስንት ሰው ደም ፈሶ ቀረ ?

ላለፉት ዓመታት ሰው በግፍ ይገደላል ከዛ የቀናት የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ ሆኖ ያልፋል፤ ይረሳል። ከዛ ሌላ ግፍ ሌላ ግድያ ይፈጸማል።

አንዳንዱ እውነት ከልቡ አዝኖ ፤ አንዳንዱ ደግሞ የይስሙላ ያዘነ ይመስል ሸፋፍኖ በማህበራዊ ሚዲያው ይጽፋል ፤ ይለፍፋል። ከሰዓታት በኃላ ሁሉም ረስቶት ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ህይወቱ ይመለሳል። ማህበራዊ ሚዲያ ሲገባ ትዝ ሲለው ለቀናት ስሜቱን ይፅፍ ይሆናል።

እስከ ህይወት ፍጻሜ ድረስ በሀዘን የሚቃጠሉትና ልጃቸውን የማይረሱት እናት አባት፣ ወንድም ፣ እህት ቤተሰብ፣ ዘመዶች ናቸው።

በተለይ እናት እና አባት ሲያለቅሱ ነው የሚኖሩት።

ይህ አዙሪት መቆም አለበት። ደመ በፈሰሰ ቁጥር ቁርሾ ቂም እየተወለደ እንጂ ፍቅር አንድነት አይመጣም።

ልጆቹን የተነጠቀ ቤተሰብና አካባቢ እንደሌላው የማህበራዊ ሚዲያ አርበኛ የአንድ ቀን ሀዘን አድርጎ አያልፈውም። የተፈጸመበትን ግፍና በደል መቼም አይረሳውም ! ቂም በውስጡ ያድራል። ይህ በሀገር ህዝብ ትስስር ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ከባድ ነው።

ከምንም በላይ ለተጎዱ ወገኖች ፍትህ በማስፈን ፣ ሌላ የአንድ ሰው ደም እንዳይፈስ በማድረግ አዙሪቱን ማቆም ካልተቻለ የከፋ ነገር መምጣቱ አይቀርም።

እዚህች ምድር ላይ ነገ ሳይሆን ዛሬ የሰው ልጅ ደም መፍሰስ እንዲቆም ማድረግ ይገባል።

ፍትህ ሊሰፍን ፤ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል።

ታጣቂም ሆነ አልሆነ ፤ የአካባቢው ፣ የክልሉ የመንግሥት አካል ሆነ አልሆነ ሁሉም በየድርሻው በየደረጃው ሊጠየቅ ይገባል።

እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር በምንም አይነት መንገድና ሁኔታ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ስራው ሊሆን የሚገባው እና ችግርም ሲፈጠር ለህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ከማህበራዊ ሚዲያው ጩኸት በኃላ ለመናገር ሲወጣ መታየቱ ነው።

ለመሆኑ የሚፈጸመውን የሚሰማው ከህዝብ ጋር በሚዲያ ነው ? ነዋሪው በሚዲያ ባይጮህ ላያወግዝ ነው ?

ቆይ ልክ እንደማንኛውም ሌላ አካል " አወገዝኩ " ብቻ ነው የሚባለው  ወይስ ስለተፈጸመ ግፍ በዝርዝር አጣርቶ ለህዝብ ወጥቶ መረጃ መስጠት ነው የሚገባው ? የመንግሥት ስራ ድርሻው ምንድነው ? ለስንቱ ፍትህ ለተነፈገ እያነባ ላለ ወገን ፍትህ ሰጠ ? ተጠያቂነትን አሰፈነ ? በደል የደረሰባቸውን ካሰ ? ዳግም ደም እንዳይፈስ ተከላከል ? እኚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ ይሻሉ።

ህዝብ በሀገሩ የሚሆነውን ሁሉ ያያል ፣ ይታዘባል፣ ይገመግማል ፣ ነጥብም ይይዛል።

በምንም አይነት ሁኔታ የሰው ደም አይፈስስ ፤ ደም ሲፈስ ቂምና ቁርሾ እንጂ ፍቅርና አንድነት አይወለድም።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia
#ናውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Bitcoin

የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ98,000 ዶላር በላይ ሆነ።

" የመጀመሪያው የክሪፕቶ ፕሬዝዳንት " የተባሉትና " አሜሪካን የፕላኔታችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ከተረጋገጠ በኃላ ቢትኮይን ወደላይ ተተኩሷል።

ዛሬ የተመዘገበው የቢትኮይን ዋጋ በታሪክ ከፍተኛ ሆኗል።

አንድ የቢትኮይን ዋጋ 98,149 የአሜሪካ ዶላር ገብቷል።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት " በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ  " ሲሉ ለክሪፕቶ ማህበረሰቡ መልዕክት አስትላልፈው ነበር።

@tikvahethiopia
በሕብረት እንደግ!

እኛ ኢትዮጵያውያን የሕብረት ተምሳሌቶች ነን፡፡ ደስታችንም ሆነ ሀዘናችን ስራችንም ሆነ እረፍታችን ብቸኝነትን አያውቅም፡፡ በጋራ መስራታችን ደግሞ ማህበራዊ ትስስራችንን እያጠናከረ ጉድለታችንን እየሞላ ዛሬ ላይ እንድንደርስ የረዳን እሴታችን ሆኗል፡፡ ይህን እሴት እያጠናከርን እና እርስ በእርሳችን እየተደጋገፍን ጠንካራ ሀገራዊ ኢኮኖሚ እንገነባለን፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#Hibretbank #Yourpartner #securebanking
#InfinixEthiopia

የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ ኩፖን በመውሰድ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽ ታግ በመጠቀም እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ማሸነፍ ይችላሉ ይፍጠኑ የዚህ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም አካል ይሁኑ፡፡

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
#Update

ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እንደሚገነባ ጠቁመዋል።

" እስከዛው ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን " ብለዋል።

ከንቲባዋ ፤ " በአካባቢው ያለውን ጥግግትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል " ሲሉ ገልጸዋል።

#MayorOfficeofAddisAbaba #Merkato #ShemaTera

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
⚫️ #ኢትዮጵያ ⚫️ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ምን ያልተፈጸም ፤ ምንስ ያልተደረገ ግፍ አለ ? እጅግ በጣም ሚያስደነግጠው እንዲሁም ፍጹም ከሰውነት ተራ እየተወጣ መሆኑን የሚያሳየው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ልክ ጀግንነት ፣ በጎ ተግባር፣ ፍቅርን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ይመስል ግፍና ጭካኔያቸውን በቪድዮ ማስረጃ እራሳቸው ቀርጸው ለትውልድ እያስቀመጡ መሆናቸው ነው። በእርግጥም እንዲህ እየቀረጹ ማስቀመጣቸው…
የእውነት ያለቀስነው መቼ ነው ?

አሁን ላይ ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ምን ያህል ግፍ ምን ያህል ጭካኔ ሀገራችን ውስጥ እንደተፈጸመ መናገር መቼም ለቀባሪው ማርዳት ነው።

ግን ግን እውነት አብረን ያለቀስንበት ቀን መቼ ነው ? ትዝ የሚለውስ አለ ?

አንዱ በሀዘን ተሰብሮ ሲያለቅስ አንዱ ይስቃል  ይደሰታል ፤ አንዱ ሲደሰት አንዱ ያለቅሳል። ሁሉንም አንድ የሚያደርገው የሰብዓዊነት ስሜትም እየታየ ጠፍቷል ፤ ሞቶ አፈር ለብሷል።

ለማዘን ቅድሚያ ጥያቄው " ማነው ? የትኛው ወገን ነው ? " ብሎ መጠየቅ ተለማምደነዋል። " የኔ " የምንለው ሲሆን ማልቀስ " የሌላው ነው " ብለን ስናስብ ምንም እንዳልተፈጠረ ማለፍ ከዛም ከፍ ሲል ግፉን ኖርማል ለማድረግ መሮጥ ስራችን ሆኗል።

ሌላው ይቅር ግፍና መጥፎ ተግባር ማውገዝ እንኳን ሂሳብ ተሰልቶ ጥቅምና ጉዳቱ ታይቶ፣ ጩኸቱንና የህዝቡን ቁጣ ተመልክቶ ሆኗል።

ከምንም በላይ የሚስፈራው ጭካኔና ግፍ ለሚፈጽሙ ግለሰቦች ያውም ከነማስረስረጃቸው ለሚታዩ ሰዎች ጥብቅና መቆም ለነሱ መከራከር ልምድ እየሆነ መምጣቱ ነው።

" እባካችሁ ነገሩ በደንብ ይጣራ " ማለት አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ሰው የግፍ ፈጻሚዎቹ ማንነት የኔ ወገን ነው ብሎ ካሰበ " በፍጹም እንዲህ አያደርጉም ፤ የተፈጠሩበት ተፈጥሮና ስነልቦና አይፈቅድም " ብሎ ድምዳሜ በመስጠት ሌላ ግፍ መፈጸም ተለምዷል።

በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአማራ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ... በሌሎችም ክልሎች በመንግሥት ታጣቂዎች፣ መንግሥትን እንፋለማለን ብለው በወጡ ታጣቂዎች ፣ ፓለቲከኞች በሚሰሩት ጥላቻ የተመረዙ ከማህበረሰቡ በወጡ ሰዎች ለማየት የሚከብድ ብዙ ግፍ ተሰርቶ ያውም በቪድዮ ተቀርጾ ታይቷል ዛሬም እዚሁ መንደር አለ።

ድርጊቶቹ ይፋ ሲወጡ አብሮ በጋራ ከማዘን ፍትህን ከመጠየቀ ይልቅ የፈጻሚዎቹ ደጋፊ ሆነው የሚቀርቡ ሰዎች በዘመቻ ነገሩን ለማራከስ እና እንዳልተፈጸመ ለማሳየት የሚሄዱበት ርቀት እውን ነገ ለወጥ ይመጣል ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

በሌላኛው ጎራ በንጹህ ሰው ደም ጥቅም ያስገኝልኛል ያለውን ፖለቲካ ይጫወታል። ከበፊትም እጠላዋለሁ የሚለውን አካል መርጦ ሌላ እልቂት ይቀሰቅሳል።

በዚህም መሃል በርካቶች እንደወጡ ቀርተው ፍትህ አላገኙም።

ለማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች እና ሰላም ያለበት ከተማ ለሚኖሩ ነገሩ የሁለት ቀን ግፋ ቢል የሶስት ቀን አጀንዳ ሆኖ ያልፋል። ከዛ ሌላ ግፍ ይፈጸማል።

እናት አምጣ የወለደችውን ፤ ለፍታ ያሳደገችውን ልጅ እያሰበች ዘላለም በለቅሶ ትኖራለች። ወዳጅ ዘመድ ግፉን እያሰበ አመለካከቱ ተቀይሮና በመጥፎ ስሜት ተሞልቶ ለሌላው እንዳያዝን ሆኖ ይኖራል።

የስንቱ ቤት በሀዘን ፣ የስንቱ ሰው ልብ በቂምና ቁርሾ ፤ ሳይወድ በግዱ በመጥፎ አመለካከት ተሞልቶ ይሆን ?

ይህ ነገር ማብቃት አለበት። ተስፋ የሚሰጥ ትንሽ ሰብዓዊነት ሊኖር ይገባል። ማንም ይሁን ማን ተጠያቂነት ሊፈጠር፣ ፍትህ ሊሰፍን ይገባል።

እናቶች የሞተው ልጆቻቸውን ባይመልስላቸውም ፍትህ ሲያገኙ ቢያንስ እንባቸው ይታበስ ተስፋቸው ይለመልም ይሆናል።

ፍትህ ሲገኝ ዜጎች በሀገራቸው ተስፋቸው ያብባል።

በምንም አይነት ሁኔታ በግጭት ፣ በጦርነት ሆነ በምንም መንገድ በምድሪቱ ደም አይፈሰስ ፣ ሰው አይበደል ፤ የሰው ደም በፈሰሰ ቁጥር ፤ በደል በተፈጸመ ቁጥር ቂም ጥላቻ፣ አለመተዛዘን እየተወለደ እየተስፋፋ ይመጣል።

ደስታውስ ይቅር እውነት አብረን መቼ ነው በጋራ ያለቀስነው ? ብለን እንጠይቅ። ከልብ እንኮንን፣ ሂሳብ አንስራ ፤ የሰው ደም ላይ ፖለቲካ አንቆምር ፤ ለፍትህ እንታገል ! ካልሆነ የሁላችን እጣ ፋንታ እንደወጡ መቅረት ፍትህ አለማግኘት ይሆናል።

#TikvahEthiopia
#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ናውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ። የማህሌት አስክሬን አጋቾች ከቀበሩበት ወጥቶ የአስከሬን ምርመራ ተጠናቅቆ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዓድዋ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን የቀብር ስነ-ሰርዓት ተፈጽሟል። የቀብር ስነ-ስርዓቱ የክልል ፣ የዞን እና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም በርካታ የዓድዋ ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር። ተማሪ ማህሌት ተኽላይ በዓድዋ  ከተማ " ዓዲ ማሐለኻ " የሚባል…
#Update

ወጣት እንስቶችን በግፍ ከገደሉ ውስጥ አንዱ በእድሜ ልክ አስራት ሲቀጣ ፤ የተቀሩት ለፍርድ ተቀጥረዋል።

የመቐለ የማእከላዊው ፍርድ ቤት ትላንት ባዋለው ችሎት ኣፀደ ታፈረ በተባለች እንስት ወጣት በተፈፀመ የግድያ ወንጀል በይን የሰጠ ሲሆን ዓድዋ ከተማ ላይ በተገደለችው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ግድያ ተጠርጣሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል። 

ሟች ወጣት ኣፀደ ታፈረን በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ አስራት እንዲቀጣ  የመቐለ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ህዳር 12/2017 ዓ.ም ወስኗል። 

ገዳይ ወንጀለኛ ቢንያም ገብረሚካኤል ሟች እንስት ኣፀደ ታፈረ በመቐለ ልዩ ስሙ እንዳ ገብርኤል የተባለ ቦታ አንቆ ከገደላት በኋላ በአከባቢው ወደ ሚገኘው ጫካ ወርውሯት እንደሄደ በአቃቤ ህግ የቀረበው የክስ ማስረጃ ያስረዳል።

ገዳይ ወንጀለኛ ቢንያም በፈፀመው አሰቃቂ የግድያ ወንጀል የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ጥፍተኝቱ አረጋግጦ በእድሜ ልክ አስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የመቐለ ፍትህ ፅህፈት ቤት አስታውቀዋል።

ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ፤ " ገዳይ ወንጀለኛው የእድሜ ልክ አስራት ያንሰዋል ፤ በሞት ፍርድ መቀጣት ነበረበት " ብለዋል። 

በተያያዘ ዜና ፍርድ ቤቱ ባለፈው 2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ ለወራት ታግታ ተሰውራ ቆይታ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ሞታ ተቀብራ አስከሬንዋ የተገኘው እንስት ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ በማህሌት ግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም በአቃቤ ህግ የቀረበላቸው የምስክሮች ማስረጃ እንዲከላከሉ ለህዳር 12/2017 ዓ.ም የቀጠረ ቢሆንም ተጠርጣሪዎች መከላከል ስላልቻሉ የውሳኔ ፍርድ ለመስጠት ለህዳር 23/2017 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።  

ባለፈው ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ የመቐለ እና የውቕሮ ከተሞች በቅርብ የትዳር እና የፍቅር አጋሮቻቸው የተገደሉ ሁለት እንስቶች ጉዳይ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ተይዘው የህግ የምርመራ ሂደት መጀመሩ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
🔥 እስከ 35% ቅናሽ ከ1 ዓመት የጥቅል ስጦታ ጋር በተመረጡ ስልኮች ላይ!!

እንደምርጫዎ ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን ጨምሮ የተለያዩ የሞባይል ስልኮች በልዩ ቅናሽ ለገበያ ቀርበዋል፤ የእጅ ስልኮቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ሲገዙ:-

▶️ የ2 ጊ.ባ ወርኃዊ የዩትዩብ ጥቅል ለአንድ ዓመት እንዲሁም

🌐+📞 ተጨማሪ የዳታና የድምጽ ጥቅል ለ3 ወራት በስጦታ ያገኛሉ!

📍 በመዲናችን በሚገኙ የአገልግሎት ማዕከሎቻችን ያገኟቸዋል!

ቅናሽ የተደረገባቸውን ስልኮች እና ዋጋ ለመመልከት https://bit.ly/3OjZLhK ይጎብኙ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
🔈 #የመምህራንድምጽ

🔴 “ ‘ለምን ደመወዛችን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህን  ታስረዋል” - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር

🔵 “የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ

🟢 “ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም”  - የዞኑ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው በመቆረጡ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የዞኑ መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፣ “‘ደመወዛችን ለምን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህራን ታስረዋል” ብለዋል።

“‘የተቆረጠው ደመወዝ ከኛ ፈቃድና ስምምነት ውጪ ስለሆነ ይመለስልን’ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነው የታሰሩት። ያለፈቃዳቸው ደመወዛቸው መቆረጡ፤ መታሰራቸው አግባብ አይደለም። አግባብ አለመሆኑን ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል” ነው ያሉት።

“ከዞኑ መምህራን ማኀበር የታሰሩትን ለማነጋገር ሂደው የወረዳ አመራሮች የታሰሩት እንዳይጠየቁ ጭምር ከልክለዋል” ያሉት ሰብሳቢው፣ “ጥያቄያቸውን በውይይት መመለስ ሲገባችሁ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታቱ ስህተት ነው” በሚል እየሞገቱ መሆኑን አስረድተዋል።

ስለጉዳየለ ማብራሪያ የጠየቅነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኀበር በበኩሉ፣ የመምህራኑ መታሰር ከዞኑ መምህራን ማኀበር ሪፓርት እንደተደረገለት በመግለጽ፣ “ያለአግባብ ማንም ተነስቶ ደመወዝ ቆርጦ መውሰድ ሕገወጥነት ነው” ሲል ወንጅሏል።

ከላይ ላሉት ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቃችኋል? በማለት የጠየቅናቸው የማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ፣ የመምህራኑን መታሰር አረጋግጠው፣ “ትላንት ነው ከዞኑ ሪፖርት የተደረገልን። ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀናል” ብለዋል።

ያለፈቃዳቸው ደመወዝ መቁረጥና ለምን? ብለው የጠይቁ መምህራኑን ማሰር አግባብ ነው? የሚል ጥያቄ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረበላቸው የኮሬ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰረበ አሻግሬ፣ “ደመወዛቸው የተቆረጠው በፈቃዳቸው” ነው ሲሉ አስተባብለዋል።

ማኀበሩ ለእናንተም እንዳሳወቀ፤ ያለፍቃዳቸው እንደተቆረጠ፣ መምህራኑ እንደታሰሩ ነው የገለጸው፣ ፤ ይሄ ለምን ሆነ? በሚል ላቀረበሰነው ጥያቄ፣ “የሰርማሌ ወረዳ መምህን ጋር ተገናኝቻለሁ። ደመወዛቸው የተቆረጠው አሁን አይደለም፤ ፈቅደውም ነው” ብለዋል።

የኃላፊው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው?

“ አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ የሚል በሁሉም አካባቢ ወላጅም፣ ሠራተኞችም፣ ተማሪም እንዲተባበር የሚል አገር አቀፍ ጉዳይ አለ። የዞኑ አመራሮች ተስማምተው ነው ወደ ታች የወረደው።

የትምህርት ቤቱ መምህራን ባለሉበት ውይይት ተካሂዷል። ተስማምተው ደመወዛቸው ከተቆረጠ ቆይቷል። ሐምሌና ነሐሴ አካባቢ ነው የተቆረጠው። በተቆረጠ ጊዜ ነበር መቆረጡ ልክ አይደለም ብለው ማመልከት የነበረባቸው።

ተስማምተው ከተቆረጠ በኋላ የሳርማሌ ወረዳ ብቻ ይህንን ተግባሪዊ ሲያደርግ የከተማ አስተዳደርና ጎርካ አላደረገም። ግን ዞን ማዕከሉም ተግባራዊ አድርጓል 25 ፐርሰንቱን።

በመምህራኑ ‘እንዴት ሌሎች አካበቢ ያሉ መምህራን ሳይቆርጡ የኛ ብቻ ተቆረጠ? ስለዚህ ገንዘባችን ይመለስ’ የሚል ጥያቄ ነው የተነሳው መጀመሪያ። ገንዘብ ይመለስ የሚለው ነገር በጋራ እንነጋገራለን።

መምህራን በሁለት ነው የተከፈሉት። ግማሹ ‘እያስተማርን እንጠይቅ’፤ ግማሹ ‘ሙሉ ለሙሉ ትምህርት እናቁም’ የሚል ነው። የተወሰኑት ለማስተማር ክፍል ሲገቡ የተወሰኑት ደግሞ ድንጋይ ይዞ የሚሄድ፤ ተማሪ ይውጣ የሚል አለ።

በመምህራን መካከል ግጭት ተፈጠረ። የተቆረጠው ገንዘብ ይመለስ በመባሉ ሳይሆን በመምህራኑ መካከል በተፈጠረው ግጭት ነው የታሰሩት። ችግር የፈጠሩ ሰባት መምህራን ነበሩ ትላንት የታሰሩት። 

መምህራኑ የታሰሩት ችግር ፈጥረው ነው ሳይፈጥሩ? የሚለውን  እንዲያረጋግጡ ለአራት ዞኑን መምህራን ማኀበር ወደ ታች እንዲወርዱ አሳይመንት ሰጥቻሁ። ትላንት ነበር አሳይመንት የሰጠሁት እነርሱ ግን የወረዱት ዛሬ ነው።

‘እንደገና ደግሞ ሌሎች መምህራን ታስረዋል’ ሲባል በምን ምክንያት ? ስል በፊት የታሰሩት መምህራን ለምን ታሰሩ ? ብለው ሊረብሹ መጥተው ነው የሚል መረጃ አለ። 

አሁን የዞኑን መምህራን ማህበር፣ ትምህርት ጽሕፈት ቤትንም አግኝታለሁ ውይይት ላይ ናቸው። 

የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው እንጂ ያ በውይይት የሚፈታ ነው። በዚህ ተስማምተናል።
” ብለዋል።

መምህራኑ ለምን ታሰሩ ? በሚለው ጉዳይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኮሬ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ፣ “ ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም ” በማለት ለማብራሪያ ቀጠሮ ከመስጠትም ተቆጥበዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ ምላሽ ሲሰጥ፣ ጉዳዩንም እስከመጨረሻው በመከታተል ተጨማሪ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔴 "... አጭበርባሪዎቹ ከቦታው ዘወር ሲሉ በአካውንቱ ላይ ምንም ገንዘብ አይገኝምና እንደ አገር ታንቀው የሞቱ ወገኖች ጭምር እንዳሉ እናውቃለን " - የተወካዮች ምክር ቤት አባል

🔵 " ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሥራ እየደሰራን ነው "  - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

የተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በታሪክ ለመጀመሪያ በመስሪያ ቤቱ በአካል በመገኘት የሳፋሪኮም  ኢትዮጵያን የሥራ አፈጻጸምን ገምግሟል።

ኮሚቴው እስከዛሬ ድረስ ድርጅቶችን ሲገመግም የነበረው በሚላክለት ሪፖርት ብቻ የነበረ ከመሆኑ አንጻር የአሁኑ ግምገማ በአካል በመገኘት መሆኑ ግምገማውን ለየት ያለ አድርጎታል።

ድርጅቱ በግምገማው ወቅት፣ የሳፋሪኮም ደንበኞች ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚዎች በሚደውሉበት ወቅት ተጨማሪ ክፍያ እየከፈሉ መሆኑን ጠቅሶ፣ ይኼው ክፍያ እንዲቀርላቸው፣ የታወር ማስፋፊያ ፈቃድ በቅድመ ሁኔታ እንዲሰጥ ኮሚቴው ለመንግስት እንዲያሳስብለት ጠይቋል፡፡

ኮሚቴው በበኩላቸው፣ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ለተጠየቀው የድጋፍም ሆነ የፈቃድ ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጡ ቃል ገብቷል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በሦስት አመታት ውስጥ ከ6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንዳፈራ፣ ከ12 ባንኮች ጋር እየሰራ መሆኑን፣ በዘጠኝ የክልል ከተሞች የኔቶርክ አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑት ገልጸዋል፡፡

በግምገማው የተገኙት የምክር ቤት አባላት ስለሳፋሪኮም የሥራ ሁኔታ የቀረበላቸውን ገለጻ ካዳመጡ በኋላ በአጭር አመት ውስጥ ድርጅቱ ያሳየው ውጤት ከፍተኛ መሆኑን በአንክሮ ገልጸው፣ በአንጻሩ ደግሞ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንሸራሽረዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ?

➡️ ወ/ሮ ሙሉነሽ የተባሉ የም/ቤት አባል፣ “ ድጅታል ካሽ ፓይመንት ከፋይናንሻል ሰርቪስ አንፃር ለከስተመሩ ምን ያህል ሴኩይር ነው ?

ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ማጭበርበሮች ይከናወናሉ፤ አንዳንድ የንግድ / የሽያጨ ተቋማት ኦንላይን ላይ ሽያጭ ተሽጧል ይባልና ገንዘቡ በአካውንት እንደተላከ የሚያሳይ ጊዜያዊ መልዕክት ይገባል ፤ ከዚያ በኋላ አጭበርባሪዎቹ ከቦታው ዘወር ሲሉ በአካውንቱ ላይ ምን ገንዘብ የማይገኝበት ሁኔታ በመኖሩ እንደ አገር ታንቀው የሞቱ ወገኖች ጭምር እንዳሉ እናውቃለን፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተጭበረበሩ እንዳሉም እናያለንና ይህን ጉዳይ ምን ያህል አስተማማኝ ነው ?

ድርጅቱ የሚሰራው ከ12 ባንኮች ብቻ ጋር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ለምን ከቀሪ ባንኮች ጋር አብሮ አልሰራም ? ከሌሎች ባንኮችም ጋር በመስራት ሰርቪሱ ሰፋ እንዳይል ያደረገው ቻሌንጅ ምንድን ነው ? ”
ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

➡️ አቶ ከድር የተባሉ የምክት ቤት አባል ደግሞ ፥ " ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የምትሰሯቸው ሥራዎች ውጤታማ ናቸው ውይ ? ድርጅቱ ከመንግስት ጋር በገባው ውል አንጻር ተጽዕኖ አለበት ወይ ? ድርጅቱስ በውሉ መሠረት እየሰራ ነው " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

➡️ ሌላኛው የምክር ቤት አባል ፥ " የድርጅቱ ዓላማ ኢትዮ ቴሌኮም ተደራሽ ባላደረጋቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን ተደራሻ ማድረግ ከመሆኑ አንጻር፣ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት በሌለባቸው አካባቢዎች በቂና የተለዬ ቴክኖሎጅ ከመጠቀም አንጻር ምን አድርገችኋል?

የኔቶርክ ጥራቱ ከኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ተብሎ ነው የቀረበቀው ነገር ግን አዲስ አበባ ራሱ የኔቶርክ ጥራት አለ ወይ ?
" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የሳፋሪኮም በበኩሉ፣ " ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሥራ እየደሰራን ነው " ሲል የኮሚቴ አባል ላነሱት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

'ተጭበረበርን' የሚሉ ሰዎች ሪፖርት እንዳደረጉ ገንዘቡ ሆልድ እንዲሆን እንደሚያደርግ፣ ከዚያ ጉዳዩ በሕግ ታይቶ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚያደርግ ድርጅቱ አስረድቷል፡፡

ከ12 ባንኮች ባለፈ ከሌሎች ባንኮች ጋር ለምን እንዳልተሰራ ለቀረበው ጥያቄ ፥ የባንኮቹ ዝግጅትና የድርጅቱ ዝግጅት የተጣጣመ አለመሆኑን በምክንያት ጠቅሶ፣ ይህ ሲስተካከል ከሁሉም ባንኮች ጋር አብሮ መስራቱ የማይቀር እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

ቴሌ ተደራሽ ባላደረጋቸው፣ የመሰረተ ልማት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ምን እየሰራ እንደሆነ መጠይቅ የቀረበለት ድርጅቱ፣ የተቻለውን ያክል እየሰራ እንደሆነ፣ የጸጥታ ችግር ግን ፈተና እንደሆነበት ተናግሯል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያለው ሥራና ውድድር ከባድ ቻሌንጅ እንዳለው የገለጸው ድርጅቱ ከውል ጋር በተያያዘ ለቀረበለት ጥያቄ በእርግጥ በውሉ መሠረት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

የኔቶርክ ጥራት በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄም፣ የኔቶርክ ጥራቱ የተሻለ እንደሆነ በመጥቀስ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Mekelle

ዛሬ በመቐለ ከተማ በሚገኝ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት በራፍ በጠራራ ፀሐይ ነዋሪዎችን ያስደነገጠ ድርጊት ተፈጽሟል።

አንድ መምህር በተማሪው በስለት ብዙ ቦታ ተውግቶ በህክምና እርዳታ ህይወቱ ተርፏል።

ተማሪው በምሳ ሰአት መውጪያ ላይ የደበቀውን ስል ቢላዋ በማውጣት መምህሩን 2 ጊዜ ደረቱ ላይ፣ 1 ጊዜ በሆዱ ላይ ፣ 1 ጊዜ በጀርባው ላይ ፣ 1 ጊዜ ጉኑ ላይ በአጠቃላይ 5 ቦታ ላይ ወግቶታል።

መምህሩን ወድያውኑ ወደ ዓይደር ሆስፒታል ማድረስ በመቻሉ በከባድ የቆዶ ህክምና ህይወቱ መታደግ ተችሏል። 

ይህንን መረጃ ያጋሩት የዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ " ብዙ ተማሪዎች ስለት ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ እየሰማን ነው እንደ ማህበረሰብ አንድ ነገር ማድረግ አለብን " ብለዋል።

ድርጊቱን በተመለከተ ከፖሊስ በኩል የተባለ ነገር የለም።

ሆኖም ወላጆች እባካችሁ የልጆቻችሁን ውሎ ተከታተሉ። ካልተገባ ተግባርም እንዲርቁ ምከሩ ፤ ቸል አትበሏቸዋል እንላለን።

በሌላ በኩል ፤ በዛው መቐለ 6 ቀናት ያስቆጠረ ህፃን እናቱ ከቤት ትታው ወደ መፀዳጃ ቤት ታመራለች ፤ ዳናዋን ተከትሎ ህፃኑ ወደ ተኛበት ክፍል የገባ የቤታቸው ውሻ የህፃኑ መራብያ አካል ላይ ጉዳት አድርሷል።

እናቲቱ ወድያውኑ ደርሳ ልጇን ወደ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ይዛው እንደመጣች ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ አጋርተዋል።

በእነዲህም አለና ወላጆች ልጨቅላ ልጆቻቹ የምታደረጉት ጥንቃቄ አይለያችሁ።

የተከሰቱት ድርጊቶች ምንም እንኳን ለመስማት የሚከብዱ ቢሆኑም ለወላጆች ጥንቃቄ ሲባል ያጋራናቸው ናቸው።

#Mekelle #AyderHospital

@tikvahethiopia