TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደኢህዴን~አርባምንጭ‼️

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ #በአርባምንጭ_ከተማ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ከደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በስብሰባው በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን የስድስት ወራት አፈጻጸም ይገመግማል፡፡ የፖለቲካና የድርጅት ጉዳዮች፣ ሃገራዊና ክልላዊ የፖለቲካና ጸጥታ ጉዳዮች ላይም ይወያያል፡፡

በእድገትና ትራንስፎሜሽን እቅዱ መሰረት በከተማና ገጠር አካባቢዎች የተከናወኑ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም ላይም ይመክራል፡፡

ስራ አስፈጻሚው በስብሰባው እነዚህን ጉዳዮች እስከ መጪው አርብ ከገመገመ በኋላ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ደግሞ በተመሳሳይ አጀንዳ እንደሚመክር የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው በደኢህዴን 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የተላለፉ የውሳኔ አቅጣጫዎች አፈጻጸም በዝርዝር እየተገመገመ ነው። የጉባኤ አቅጣጫን ተከትሎ በ2011 ዓ.ም በ6 ወራት ውስጥ የተከናወኑ የፖለቲካና የድርጅት ሥራዎች እንዲሁም የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አፈጻጸም እየተገመገመ ሲሆን የክልሉ ጸጥታ ሁኔታን ጨምሮ ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችም እየተገመገመ ይገኛል፡፡ በግምገማው ማጠቃለያ በጥንካሬና በጉድለት በተለዩ ዋና ዋና ጉዳዮች ጠንካራ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via SEPDM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሚክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ወቅታዊ #ሀገራዊና #ክልላዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም የድርጅትንና የመንግስት ተግባራትን #በአርባምንጭ ከተማ ላይ እየገመገመ ይገኛል፡፡ የደኢህዴን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከየካቲት 12/2011 አስከ የካቲት 14/2011 ዓ.ም ድረስ በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እና የድርጅትና የመንግስት አፈፃፀሞች ላይ የመከረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በተመሳሳይ አጀንዳዎች ላይ #እየተወያየ ይገኛል፡፡

Via SEPDM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትብብር ጥሪ፦

#በአርባምንጭ_ከተማ ለምትገኙ የሆቴል ባለቤቶች እና የህትመት ድርጅት ባለቤቶች፦

እኛ TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ #በሚያስፈራ ሁኔታ እየተንሰራፋ የመጣውን የጥላቻ ንግግርን ለማስቆም ያለመ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ የStopHateSpeech ዘመቻ እያከናወንን እንገኛለን። የመጀመሪያው ምዕራፍ ስራም በሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያው ዝግጅትም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

ይህ ዘመቻ ያለምንም ድጋፍ በቻናሉ ብቻ ነው የተጀመረው፤ በመጀመሪያው ዝግጅትም ከፍተኛ ወጪ በግል አውጥተናል በተለይ ለህትመት እና ለፕሮግራም ዝግጅት። እኛ እንደግል ይህን ማድረግ ከቻለን ድርጅቶች በትንሹ ብትተባበሩን በርካቶችን በጥላቻ ንግግሮች እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት እንችላለን። ሀሳብችንን ለሚደግፉ አካላት አሁንም ጥሪ እያቀረብን እንገኛለን።

በአርባምንጭ የምትገኙ የሆቴል ባለቤቶች እና የህትመት ድርጅቶች ይህን ሀገር አድን ጥሪ ሰምታችሁ የዘመቻው አካል በመሆን ከጎናችን እንድትቆሙና እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።

ሰላም ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!
ሁላችንም ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ!

ልትደግፉን የምትችሉ ፦ 0919 74 36 30 ላይ ደውሉልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: የTIKVAH-ETHIOPIA 40 #የቤተሰቡ_አባላት #በአርባምንጭ ከተማ የነበራቸው የሁለት ቀን የተሳካ ቆይታ👆

#StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia