TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ገንዘብ እያሰባሰበች ነው ?

👉 " ምዕመናን ፤ ቅዱሳን ገንዘባችሁን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ " -  መጋቢ ለወየሁ ስንሻው

" የሚታየው የባንክ አካውንት ሆነ መልዕክት እኛ የማናውቀው ነው " - አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ


" በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ያሉ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ከፓስተር/መጋቢ ዮናታን አክሊሉ ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ / ገንዘብ መሰብስበ ስራዎች እየሰሩ ነው " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገልጸ።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰጠችው ይፋዊ መግለጫ ፥ የባንክ ቁጥር ጭምር በመግለጽ የተለያዩ ፖስተሮችንም በማሰራት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተደረገ ያለው የገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ፍጹም የማታውቀው ስራ እንደሆነ ገልጻለች።

የቤተክርስቲያኗ ምክትል ፕሬዜዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ፤ " ከወንድማችን ዮናታን አክሊሉ ጋር በዚህ ስራ ዙሪያ ንግግር አላደርግንም ይህንን መግለጽ እንፈልጋለን " ብለዋል።

የባንክ አካውንቶቹ በአንድ ግለሰብ ስም እንደተከፈቱ እንደተደረሰበትና ቤተክርስቲያኗ በሚመለከተው አካል በኩል ጉዳዩን እንደምትሄድበት ተገልጿል።

ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን ያሳሰበና ያስደነገጠ እንደሆነ ተመላክቷል።

መጋቢ ለወየሁ ፤ " ምዕመናን ፣ ቅዱሳን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስራ የተባለው በፍጹም ማታለል እና ማጭበርበር የተሞላበት በመሆኑ በዚህ የማታለል ተግባር ገንዘባችሁን እንዳትበሉ፣ እንዳትሳተፉ " ሲሉ አሳስበዋል።

በተመሳሳይም አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ፥ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያናት እና ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ እያካሄዱ እንደሆነ የሚገልጹት መልዕክቶች ፍጹም ሀሰተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

" በስሜ የተከፈተ ለዚህ የሙሉ ወንጌል አገልግሎት የሚውል የባንክ አካውንት እንደሌለ አሳውቃለሁ " ብለዋል።

አካውንቱን ማነው የከፈተው (በማስታወቂያዎች ላይ ያለውን) ስለሚለው ጉዳይም ፤ ማን እንደከፈረው እንደተደረሰበትና የቤተክርስቲያኒቱ እና የእሳቸውም የህግ ክፍል ጉዳዩን እንደሚከታተለው ጠቁመዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚታየው የባንክ አካውንት ሆነ መልዕክት እኔን እና ቤተክርስቲያናችንን የአዲስ ካህናት ቤተክርስቲያን የማይመለከት የማናውቀው ነው " ብለዋል።

" እራሳችሁን ከዚህ የማታለል ስራ ጠብቁ ፤ ምንም ተሳትፎም እንዳታደርጉ " ሲሉ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመሬት መንቀጥቀጡ የቦታ ለውጥ አድርጓል ?

" በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " - ፕ/ር አታላይ አየለ

በትላንትናው ዕለት በቀን፣ በምሽትና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸው ዓለም አቀፍ ጁኦሎጂካል ተቋማት ዘግበዋል።

ትላንት ምሽት 2:10 የተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ ከተመዘገበው መንቀጥቀጥ በተጨማሪ ለሊት 7:20 ላይ 5.1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በተጠቀሰው መጠን መከሰቱን እና ዛሬ ጠዋት 2:11 ላይም ሌላ መንቀጥቀጥ በመታየቱ የመተንተን ስራ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ትላንት ለሊት 7:20 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከደብረ ሲና 52 ኪሜ ርቀት ላይ ምሽት ላይ የተከሰተው ደግሞ ከአዋሽ 14 ኪሜ ርቀት ላይ የተከሰተ ነው መባሉ ከዚህ ቀደም ይከሰት ከነበረበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አለ ማለት አለመሆኑን አስረድተዋል።

ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

" ትላንትና ከሰዓት ጀምሮ በጣም የተደጋጋመ ከፍተኛ መጠን ያለው ከ4.6 ጀምሮ እስከ 5.0 የተመዘገበ መንቀጥቀጥ ተከስቷል ፤ ነገር ግን ደብረ ሲና ሲል ከፈንታሌ በወፍ በረር ሲለካ ነው ከተለያየ አቅጣጫ በማየት ነው እንጂ መነሻው ስለተቀየረ አይደለም።

አንድ አካባቢ ላይ መሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በአቅራቢያው ያለው ከተማ የትኛው ነው ? የሚለው ይታያል ከዛ የተለያዩ ከተሞችን እንደ ሪፈረንስ ይጠቅስና ከዛ ከተማ ምን ያህል ነው የሚርቀው የሚለውን ሪፈር ያደርጋል፤ እንደዛ ሲሆን ሌላ ሰው መንቀጥቀጡ ለዛ ከተማ ቀርቧል ማለት ነው የሚል ስጋት ሊያድርበት ይችላል ነገር ግን እስካሁን የተቀየረ ነገር የለም፤ ፈንታሌ ዙሪያ ነው እንቅስቃሴው እየተታየ ያለው።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እና የጀርመኑ የጂኦ ሳይንስ ተቋማት የሚጠቀሙት ዳታ አውቶማቲክ ነው ሲስተሙ ቶሎ አናላይዝ አድርጎ የተከሰተበትን መጠን እና አካባቢ ከርቀት ጋር ይናገራል ነገር ግን ይህ አይነቱን አዘጋገብ የሚከተሉት ለማህበረሰቡ በምን ያህል ርቀት ላይ ነው የተከሰተው የሚለውን ለማስረዳት ነው።

ለምሳሌ፦  አንድ ብቻ አይደለም የተለያዩ ቦታዎች ይጠቅሳሉ  ከመተሃራ፣ከደብረሲና ፣ከደብረ ብርሃን እና ከአዲስ አበባስ ምን ያህል ርቀት ላይ ይገኛል ሊል ይችላል በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም።

አዲስ ነገር አይደለም ስንመዘግብ የኖርነው ነገር ነው ነገር ግን መሃንዲስም፣ ኢንቨስተርም ሆነ የሚመለከተው አካል ጆሮ ሰጥቶ ጥንቃቄ አድርጎ አያውቅም አሁን የሚከሰተውንም መአት እንደተከሰተ አድርጎ የሚያወራ አለ እንደዛ አይደለም በተለያየ ጊዜ ይመዘገባል።

በ1997 በአፋር ታይቶ የማይታወቅ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር ብዙ አለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ሁሉ መጥተው አብረን የሰራናቸው ስራዎች አሉ፣ ፈንታሌም በፈረንጂዎቹ 1981 እንደ አሁኑ 3 እና 4 ወር የቆየ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር።

የመረጃ ውንዥብር እየተፈጠረ ነው ሳይንቲስት የምንለው ማነው ? ታማኝነቱስ ምን ያህል ነው ?የሚለው አስቸጋሪ ሆኗል ያልሆነውን ሆኗል እያሉ የሚያወናብደውም ብዝቷል ተማረ የምንለውም መሬት ላይ ያለውም ህብረተሰብ።

መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም።

ከትላንት እኩለ ቀን ጀምሮ ጎላ ጎላ ያሉት መንቀጥቀጦች የመደጋገም ፍጥነታቸው ጨምሯል ቀጣይነትም ያለው ሊሆን ይችላል እየተከታተልን እየመዘገብን እንገኛለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#AAU
#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
ወደ ኖርዌይ ለልምድ ልውውጥ የሄዱ የሁለት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ ሀገር ሳይመለሱ ቀሩ።

የኢዜማ እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ለልምድ ልውውጥ ከሃገር በወጡበት አለመመለሳቸው ተሰምቷል።

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦሮ) የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ደቻሳ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በመስከረም አጋማሽ ለልምድ ልውውጥ ወደ #ኖርዌይ ባቀኑበት ወቅት አለመመለሳቸው ተነግሯል።

ሁለቱ አባላት ወደ ኖርዌይ ያቀኑትና ያልተመለሱት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የልምምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በተላኩበት ወቅት መሆኑን የም/ ቤቱ ጸሃፊ አቶ ደስታ ዲንቃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አባላቱ በጋራ ምክር ቤቱ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢነት እና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ነበር።

አቶ ደስታ ፥ " የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማጠናከር በሃገር ደረጃ ከፓርላማ አባላት ጋር እና የሲቪክ ተቋማት ጋር እየተገናኙ ብዙ ስራዎችን ሲሰሩ ነበር " ብለዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የኢዜማ አባል ፤ አባሏ በስራ ገበታቸው ላይ አለመኖራቸው በማስረዳት " ለምን እንዳልተመለሱ የምናውቀው ነገር የለም " ብሏል።

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በበኩሉ ከልጆቿና ከባለቤቷ ጋር በፖለቲካ ምክንያት ለእስር ተዳርገው እንደነበር የገለጸ ሲሆን ለመቅረቷም ምክንያት ይህ ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ይህንን የገለጸው አዘጋጁ የኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት ማኅበር ነው።

የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ይህ የዝማሬ መርሐግብር በበዓሉ ዋዜማ ታኅሣሥ 28/ 2017 ዓ/ም ይካሄዳል።

በአዲስ አበባ ከተማ የዝማሬ መርሐግብሩ አምና በተካሄደበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) እንደሚካሄድ ነው አዘጋጆቹ ያሳወቁት።

" የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት በዝማሬ እናክብር " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የልደት በዓልን ዋዜማ በቤተክርስቲያን ተገኝተው በዝማሬ እንዲያከብሩ ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ካዘጋጁት " የአእላፋት ዝማሬ  / The Melody of Myriads " መርሐግብር ውጭ ሌላ እንዳላዘጋጁ እንዲሁም ለዚህ መርሐግብር ተብሎ የሚደረግ ምዝገባም እንደሌለና ምዕመኑ ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ  ጥሪ አቅርበዋል።

ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በተካሄደው " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የልደት ዋዜማን በዝማሬና በፀሎት ተቀብሎ ነበር።

መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና ብፁአን አባቶች ተገኝተው እንደነበር አይዘነጋም።

ከመርሐግብሩ ቀደም ብሎ ምዕመናን በተለይም ወጣቶች የተዘጋጁ መዝሙሮችን አጥንተው እንዲመጡ መዝሙሮቹ በኦንላይን ሲሰራጩ ነበር።

ዘንድሮም በተመሳሳይ ለመርሃግብሩ የተዘጋጁ መዝሙሮች በማኅበሩ  የማህበራዊ ሚዲያዎች (Janderbaw Media Youtube) ተጭነው ምዕመኑ ጋር እንዲዳረሱ እየተደረገ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ADDIS ABABA NO 3 Total Tax Payers.pdf
6.4 MB
#እንድታውቁት

" 12 ሺ ለሚሆኑ ግብር ከፋዮች የታክስ መክፈያ ማዕከል ቅያሪ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ ለማድረግ እና ካለው የተገልጋይ ብዛት አኳያ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስቸግር በመሆኑ ለ12 ሺህ የመካከለኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ክፍያ ማዕከል (Tax Center) ቦታ ቅያሪ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ " የቦታ ቅያሪው የተደረገው በቦታው የበርካታ ግብር ከፋዮች ጫና በመኖሩ የተወሰነውን በመቀነስ ግብር ከፋዩ በአቅራቢያው ማግኘት የሚችልበትን እድል ለመፍጠር ነው " ብለዋል።

ቅያሪው የተደረገው ከስታዲየም አካባቢ የሃ ህንፃ ወደ ጉርድ ሾላ ከሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው ሜሪዲያን ኮንቬሽን ሴንተር ነው።

በአዲስ አበባ 11 የአንስተኛ ፣ 5 የመካከለኛ እና 1 የከፍተኛ ግብር ከፋይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚገኙ ሲሆኑ የአሁኑ 17ኛው ቅርንጫፍ ነው ተብሏል።

የቦታ ቅያሪው የሚመለከታቸው ተገልጋዮች ስማቸውን ከላይ በተያያዘው ፋይል በመመልከት ከጥር 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#HaileResortJimma

“ ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ተደርጎበታል" - ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ

የሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ ሆቴልና ሪዞርት 10ኛ መዳረሻ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ዛሬ (ሐሙስ ታኀሳስ 24 ቀን 2017 ዓ/ም) ተመርቋል።

ሆቴሉ 3 የመመገቢያ አደራሾች፣ የልጆች መጫወቻ፣ ሞሮኮ ባዝ እንዳሉት፣ ለ210 ሰዎች ቋሚ የሥራ እድል እንደፈጠረ፣ ለወደፊት ደግሞ ወደ 400 ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተነግሮለታል።

ሆቴሉ አሁን የተጠናቀቁ ወደ 106 ክፍሎች እንዳሉት፣ ሁሉም ሰጠናቀቁ ደግሞ ወደ 114 ክፍሎች እንደሚኖሩት ተመልክቷል።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት ሻለቃ ኃይሌ ባደረጉት ንግግር፣ በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት የሆቴሉን ግንባታ በአጭር ጊዜ ላጠናቀቁት ሠራተኞች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ጅማ ላይ የኮንስትራክሽን እቃ ውድ መሆኑን የገለጹት ሻለቃ ኃይሌ፣ “ብሎኬት ከአዲስ አበባ እየተጓጓዘ ነው የተሰራው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ኮንስትራክሽኑን ውድ ያደረገው የመንገዱ መበላሸት ነው” ያሉት ኃይሌ፣ “ብሎኬቶች እየተሰባበሩ ነበር። ሁሉ ሰው በአውሮፕላን መጓጓዝ አይችልም” ነው ያሉት።

የሆቴሉን ወጪ በተመለከተ በገለጹበት አውድ ደግሞ፣ “ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ተደርጎበታል” ብለዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ባደረጉት ገለጻ ደግሞ፣ “ጅማ አባጅፋር ሁሉንም የምታቅፍ ከተማ ናት። ባለሃብቶች ጅማን ለመቀየር ከኅይሌ እንዲማሩ ማሳያ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር ፥ “ኃይሌ ሲጠራ እንስቃለን፣ ኃይሌ ሲጠራ እንባችን ይመጣል፣ ኃይሌ እንኳን አገኘንህ” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።

“ሱልልታ ላይ የኃይሌን ሆቴል ሳይ እንዲህ አይነት ሆቴል ጅማ ላይ ቢገነባ ብዬ ተመኝቼ ነበር። አሁን እንደዚህ ተሰርቶ አየሁትና እንባዬ ነው የመጣው። የተመረቀው ለኃይሌ ሳይሆን ለጅማ ህዝብ ነው” ሲሉ አመስግነዋል።

በ10ሩም የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች 900  ሩሞች እንዳሉ፣ ለ2500 ሠራተኞች የሥራ እድል እንደተፈጠረ ተመልክቷል።

ፎቶ ፦ በግዛቱ አማረ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Haile " ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " - ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከዚህ በፊት በሻሸመኔ በጸጥታ ችግር ስለወደመው ሆቴል ሁኔታ እና በጎንደር  ከተማ በሚገኘው ሪዞርት በኩል በጸጥታ ችግር የገጠማቸውን የገቢ መቀዛቀዝን በተመለከተ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሆቴል ምረቃ መርሀ ግብር በተገኙበት ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከዚህ…
“የካሳዋን ጉዳይ አሁንም እየጠበኳት ነው። ግን የለችም” - ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ

የሻሸመኔ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት የሚታወቅ ሲሆን ፣ አፍርሰው እየሰሩ እንደነበር ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ገልጸው ነበር።

ከ10 ወራት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሙሉውን አፍርሰን እየሰራን ነው። ከመንግስት ምንም አይነት ማካካሻ አልተሰጠኝም ” ነበር ያሉት።

“ እኔ አላቃጠልኩትም። መንግስት እንደ መንግስት መወጣት ነበረበት ” ብለው፣ “  እኛ ለብዙ አመታት እንግዲህ በኢንቨስትመንት ተሰማርተን እየሰራን ነው ” ማለታቸው አይዘነጋም።

አሁንስ ከመንግሰት ካሳ ተከፈላቸው ?

የሻሸመኔው ሆቴልና ሪዞርት ለደረሰው ውድመት መንግስት ከሳ እንዳልከፈለዎት ገልጸው ነበር፣ ተከፈለዎት ? ተብሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሻለቃ ኃይሌ አሁንም ካሳ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።

“ የካሳዋን ጉዳይ እየጠበኳት ነው ግን የለችም። እሷን ነገር እብቃለሁ ” ነው ያሉት።

የውጪ ኢንቨስተሮች እንዲመጡ እንዲህ አይነት አደጋዎች ሲደርሱ ካሳ ቢከፈል መልካም መሆኑን አስረድተው፣ “ ዞሮ ዞሮ ግን አልሆነም። አልተቀበልኩም ” ብለዋል።

ሆቴሉን ከባለሦስት ወደ ባለአራት ኮከብ አድርገው እየሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ “ ህንፃ እያፈረሱ መስሪት ሁለት ሥራ ነው አንደኛ ማፍረስ፣ ሁለተኛ ደግሞ መገንባት አለ ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ በአጠቃላይ ግን ስለሆቴልና ሪዞርት ሲወራ እከሌ ሆቴል ከፈተ፣ እከሌ ሪዞርት ከፈተ የሚለው ምንም ፋይዳ የለውም። ማነው የሚተባበረው ? ማነው አብሮት ያለው? ከአዲስ አበባ ከ300 ኪሎ ሜትር ሲመጣ ሴፍ ነው ወይ? የሚሉት ምላሽ የሚፈልጉ ናቸው ” ሲሉም አስገንዝበዋል።

በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂዎች እየተካሄደ ያለውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በጎንደር ከተማ ያለው ሆቴላቸው ገቢው እየተቀዛቀዘ መሆኑንም ከዚህ ቀደም መግለጻቸው ይታወሳል።

የጎንደሩ ሆቴል ገቢው በምን ያህል ቀንሷል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ላቀረበላቸው ጥያቄ ሻለቃ ኃይሌ፣ “ አለ እንዴ ለመሆኑ ቢዝነሱ? 56፣ 57 ሩም ተይዞ 5 ሰዎች ስላሳደርክ ምንድን ነው ገቢው? ” የሚል ጥያቄ አዘል ምላሽ ሰጥተውም ነበር።

አሁንስ የጎንደሩ ሆቴል ገቢ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? በሚል ዛሬ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ደግሞ፣ “ በጎንደሩ ሆቴል የሚፈለገውን ያህል እየተሰራ አይደለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የቀጣይ የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርቶች መዳረሻ የት እንደሚሆን በዛሬ የጅማ ሪዞርት ምረቃ መርሀ ግብር ላይ ማብራሪያ የሰጡት ሻለቃ ኃይሌ፣ የሻሸመኔውንና የደብረ ብርሃኑን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ “ ድሬዳዋና ሀረርም ቀጣይ መዳረሻችን ይሆናል” ሲሉ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

⚫️ " ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነው ያለብን መኖር አልቻልንም በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን መብራት የለንም " - ቅሬታ አቅራቢ

🔴 " ከክረምት በፊት ችግሩ ይቀረፋል ታገሱ " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ፍርድ ቤት፣ ሰሚት ሳፋሪ፣ ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ ፣ ፍየል ቤት ፣ ወጂ ሰፈር፣ ሰንራይዝ ሪል ስቴት፣ ፊሊንት ስቶን ሆምስ እና ጎሮ ሚካኤል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የሃይል መቆራረጥ ከፍተኛ የሆነ ምሬት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚገኙ በተለይም የፍሊንት ስቶን ትዊን የጋራ መኖሪያ መንደር ነዋሪዎች " ከህዳር 02/03/17 ዓ/ም ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ቀንም ለሊትም ሳናገኝ በችግር ላይ እንገኛለን " ሲሉ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በደብዳቤ ጭምር ቢያሳውቁም " መፍትሄ የሚሰጠን አጥተናል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ በአካባቢው ለሃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆነው በመሬት ውስጥ በሚቀበሩ የሃይል መስመሮች ላይ የሚያጋጥም የመሰረት ልማት ጉዳት እና ስርቆት ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ደንበኞቹ የሃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የሚጠይቅ ጽሁፍ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል።

ነዋሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ?

" ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነው ያለብን መኖር አልቻልንም በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን መብራት የለንም መብራት አይመጣም ከመጣም ለሊት ነው ከዛ ተመልሶ ይጠፋል መኖር ከብዶናል።

ህመምተኞች አሉ ፤ ፍሪጅ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ ከዚህም በላይ በዚህ ኑሮ ውድነት ምግብ ለመድፋት ተገደናል።

ከህዳር 18 እስከ ታህሳስ 9 ባለው ጊዜ አምስት ጊዜ በተደጋጋሚ በመንገድ ስራ ምክንያት በመሬት ውስጥ ያለ መስመር በኤክስካቫተር እየተመታ ሃይል ተቋርጧል።

መፈጠር አልነበረበትም ቅድመ መከላከል ስራዎች ሊሰሩ ይገባ ነበር ከሆነ በኋላ ግን በተደጋጋሚ መፈጠር አልነበረበትም ተጠያቂነትም ሊኖር ይገባ ነበር።

ከታህሳስ 10 በኋላ ግን አንድ ጊዜ ሲመታ ከ18 ሰዓት እስከ 3 ቀን መብራት ይጠፋ ጀምሯል ከዛ በኋላ መቆራረጡ በከፍተኛ ሁኔታ ባሰ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ለ25 ደቂቃ ብቻ ሃይል የምናገኝበት ጊዜ ሁሉ አለ።

ትልቁ ቆየ ከተባለ 4 ሰዓት ነው ይህም ከእኩለ ለሊት እስከ ንጋት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ሰው ከተኛ በኋላ ለምንም አገልግሎት መዋል በማይችልበት ሰዓት ነው ከሚመጣው።

የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናወን በሚል በወጣው ዝርዝር ውስጥ አካባቢያችን የሃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የሚገልጸው ከ 3 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ቢሆንም እኛ ከንጋት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መብራት አናገኝም።

ችግሩን ማስቆም ሲችሉ ማህበረሰቡ በመሃል እየተቀጣ ነው ልጆች ከትምህርት ቤት መጥተው ማጥናት አልቻሉም ፣በተደጋጋሚ በመጥፋቱም ምክንያት ነዋሪው ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እየተዳረገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ሺፈራው ተሊላ ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ቀን ቀን የፕሮጀክት ስራ አለ በስራው ምክንያት ይቋረጣል ማታ ማታ ይለቁላቸዋል ሙሉ ቀን የማይበራላቸው ብልሽት ሲኖር ነው እንደዛ የሚሆነው ሁሌ አይደለም።

ከሰሚት ጀምሮ እስከ ወረገኑ ድረስ እዛ መስመር ላይ መሰረተ ልማት ስራ እየተሰራ ነው ስራዎች በቅንጅት ነው የሚሰሩት አንዳንዴ ብዙ ስራ ስለሆነ እየተሰራ ያለው ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ችግሮች ይከሰታሉ።

ለዘለቄታው ለመገልገያ (Utility) የሚሆን ኮሪደር አብሮ እየተሰራ ነው ለተወሰነ ጊዜ ነው የተጠቀሰው አይነት ችግር የሚኖረው በቀጣይ በጣም አስተማማኝ የሆነ መሰረተ ልማት እየተሰራ ነው።

መንገድ በሚሰራበት ጊዜ ከእግረኛና ከአስፋልት መንገድ ጎን የውሃ ፣ የቴሌኮም እና የኤሌክትሪክ መስመር (Utility Corridor) አብሮ እየተገነባ ነው።

ቀደም ሲል የነበረው አካሄድ ብልሽት በሚኖርበት ጊዜ አስባልት ተቆፍሮ ነበር የሚሰራው በአሁኑ አሰራር ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ብልሽት ሲኖር መቆፈር እና ማፍረስ ሳያስፈልግ ገብቶ ለመስራት ያስችላል ፣ የመቀየር እና የማሻሻል ስራ ሲያስፈልግ ማሟላት የሚችል የአቅም ማሳደግ ስራ እየተሰራ ነው።

ይህ አይነት ቅንጅት ባለመኖሩ ብዙ ችግሮች ሲከሰቱ ነበር አሁንም የምናየው ችግር የተከሰተው ቀደም ሲል ይህ አይነት ቅንጅት እና የUtility corridor ባለመኖሩ ምክንያት የተከሰተ ነው ።

ይሄንን ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ችግሩን ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራን ነው።

የተወሰነ ጊዜ መታገስ ነው ለዘመናት የሚያገለግል ስራ ነው የሚሰራው ስራው እስከ 6 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው ከክረምቱ በፊት ያልቃል" ብለዋል።

እስከዛ አሁን ባሉበት አይነት የመብራት ችግር ውስጥ ይቆያሉ ወይ ? ስንል ለዋና ስራ አስፈጻሚው ጥያቄ አንስተናል።

ኢ/ር ሺፈራው ተሊላ

" ሲሪየስ በሆነ ነገር ውስጥ ላይቆዩ ይችላሉ ብዙ ነገር እየተሻሻለ ነው የሚሄደው ብዙ ቁፋሮ አለ ቁፋሮ ካለቀም በኋላ መሰረተ ልማቱ ቦታውን ይይዛል ለስራ ሲባል ሃይል መቆራረጥ ይኖራል ነገር ግን እየተሻሻለ ይሄዳል።

ከመገናኛ ሰሚትም ሲሰራ እንደዚህ አይነት ችግሮች ነበሩ አሁን CMC አካባቢ እንደዚህ አይነት ችግር የለም ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ችግሮች አይኖሩም የሁሉም ስራ ያልቃል ከክረምት በፊት ችግሩ ይቀረፋል ታገሱ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ችግሩን በማቃለል እስከዛ በተሻለ መንገድ ሃይል የሚያገኙበት እድል ይኖራል ወይ ? የሚል ጥያቄም ያነሳንላቸው ሲሆን በምላሻቸውም " እንደዛ እናደርጋለን ከባድ ችግር ስለነበር አንድ ጊዜ ነው እስካሁን ለቀናት በሚባል ደረጃ የተቋረጠው ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይኖር ጥረት እናደርጋለን " ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ ፦ በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ። ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡ ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ተናግረዋል። በዚሁ መሠረት " በተቀናጀ…
" እዛ አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል " -የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰቱ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው ተብሏል።

ሁኔታውን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሊ ሷሊህ ፥ " ቅድሚያ ህይወት የማዳን ስራዎች እና ነዋሪዎችን አደጋው ከተፈጠረበት አካባቢ የማሸሽ ሥራ ከክልሉ መንግስት ጋር እየተሰራ ነው " ብለዋል።

" ማህበረሰቡ ደህንነቱ ወደ ተረጋገጠ አካባቢ ከመጣ በኋላ የችግሩን ስፋት እና መጠን የሚገመግም እና ምን ያህል ማህበረሰብ እርዳታ ይፈልጋል የሚለውን ለመለየት የሚያስችል ቡድን አዋቅረን ዛሬ ጠዋት ወደ አካባቢው ልከናል " ብለዋል።

" ጉዳዩ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ምን ያህል መጠለያ ጣቢያ ያስፈልጋል የሚለው በውል አልታወቀም "  ያሉት ሃላፊው " ዱለቻ አካባቢ ከሁለት ቀበሌዎች እንዲሁም አዋሽ ፈንታሌ ሳቡሬ አካባቢ በርካታ ሰዎች እየወጡ ነው ሦስት መጠለያ ጣቢያዎች ያስፈልጋሉ ብዬ አስባለሁ ትክክለኛ ቁጥሩን የምናውቀው የላክነው ቡድን መረጃውን ይዞ ሲመጣ ነው " ብለዋል።

አክለውም ፥ " ችግሩ ሊቀጥል እና ሊሰፋ ይችላል በሂደት ላይ ያለ ነገር ስለሆነ ተጨማሪ ቀበሌዎች ይፈናቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል እዛ አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል " ነው ያሉት።

አቶ አሊ ዛሬ ወደ ስፍራው ያቀናው ቡድን መረጃዎችን ሰብስቦ ይመለሳል ያሉ ሲሆን ውጤቱ እንደቀረበ በ 72 ሰዓት ውስጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ : " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " ሰኞ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል። ይህንን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ ከላይ ተያይዟል። የዘንድሮው የእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) ፤ በድሬዳዋ ደግሞ ለገሀር አደባባይ ብቻ ነው የሚካሄደው። (መግለጫውን ያንብቡ)…
#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads

“ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” - የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ (ኢጃት)

ታኅሳስ 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ ያዘጋጀው “ልደትን በባለ ልደቱ ቤት” የተሰኘውን የአእላፍ ዝማሬ በተመለከተ አዘጋጆቹ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።

የዝማሬ ጉባዔው በአዲስ አበባ በድሬዳዋ እንደሚከናወን የገለጹት አዘጋጆች፣ “ ላለፉት ስምንት ወራት ለዚህ ታላቅ የዝማሬ ጉባዔ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ” ብለዋል።

የጉባዔው ዋነኛ ዓላማ በአልባሌ ቦታ የሚውሉ ወገኖች በዓሉን በቤተክርስቲያን የመላክትን ዝማሬ በመዘመር እንዲያሳልፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያው ጃንረባ ትውልድ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቢንያም አሕመድ ፤  “ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” ብለዋል።

“ በሌሎች አካባቢዎች ላይ የተዘጋጁ ዝግጅቶች ካሉም በእዛው በመገኘት እንድታሳልፉ የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ ጥሪ ያቀርባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

በመርሃ ግብሩ በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ምንም አይነት ሽያጭ እንደማይከናውን አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል፣ “ አእላፋት ዝማሬ ነጭ ልብስ ልበሱ ” ተብሏል በሚል ነጭ ልብስ በተጋነነ ዋጋ የሚቸበችቡ ሁነቱን የተከተሉ ነጋዴዎች ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ነጭ ልብስ በውድ ወጋ እየተቸበቸበ ነው የሚል አስተያዬት እየተሰጠ ተስተውሏል፣ ለመርሀ ግብሩ ነጭ ልብስ ብቻ ለብሶ መምጣት ግዴታ ነው ? ሲል ለአዘጋጆቹ ጥያቄ አቅርቧል።

የኢትዮጵያው ጃንረባ ትውልድ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ብንያም አሕመድ በሰጡት ምላሽም፣ “ ነጭ ልብስ የሌለን ያለንን ልብስ ንጹህ አድርገን እንምጣ። ዓላማችን ልብሱ ለመቁረቢያ እንዲሆን ነው ” ብለዋል።

“ ኦርቶዶክሳዊ ኢኮኖሚ እንዲፈጠር ይፈለጋል ግልጽ ነው። በዚህ ምክንያት ወደ ስራ የሚገቡ፣ ሥራቸውን የሚያስፋፉ፣ የሚለወጡ ኦርቶዶክሳዊያን ቢኖሩ ይሄ የማኀበራችን አንዱ ዓላማ ነው ” ሲሉ ነው የተናገሩት።

“ ስለዚህ ይህን በቀና ዓይን ነው የምናየው ” ያሉት አቶ ብንያም፣ “ በእርግጥ በዚሁ ምክንያት ደግሞ አጋጣሚውን የሚጠቀሙ፣ Accidental Entrprenuers የምንላቸው መጥተው ባለሃብት ለመሆን የሚጥሩ ይኖራሉ ” ሲሉም አክለዋል።

“ ልደቱ የሰዎች የመላክት ዝማሬ ነው። ስለዚህ ይህንን በማሰብ ነጭ ለብሰን እንመጣለን ” ብለው፣ “ ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንሄድ የምናደርገው ነው፣ የተለዬ ነገር የለውም ” ነው ያሉት።

ሆኖም ነጭ ልብስ የሌላቸው ያላቸውን ልብስ በአግባቡ ለብሰው በዝማሬ መርሀ ግብሩ መገኘታቸው እንዳይዘነጋ መልዕክት ተላልፏል። 

ዝማሬው ዘማሪያን እየዘመሩ ምዕመናን የሚቀበሉበት ሂደት ሳይሆን ልደቱን በሚያወሱ ዝማሬዎች ሁሉም በጋራ ምስጋና እንዲያቀርብ መሆኑ ተሰምሮበታል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia