TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.2K photos
1.58K videos
216 files
4.32K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Bitcoin

" በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " - ትራምፕ (በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት)

የዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆኖ መመረጥ ለክሪፕቶ ማህበረሰቡ ትልቅ ብስራት ነው የሆነው።

ትራምፕ መመረጣቸው ከተሰማ በኃላ ቢትኮይን ታይቶ ባይታወቅ እና በማይታመን ሁኔታ ጨምሯል።

ዛሬ ላይ አንድ ቢትኮይን ከ91,000 ዶላር በላይ ገብቷል።

ልክ ትራምፕ ሲመረጡ በክሪፕቶ ማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ደስታ የተፈጠረ ሲሆን " የመጀመሪያው የክሪፕቶ ፕሬዝዳንት ተመረጠ " ነው የተባለው።

ትራምፕ የመጀመሪያው በይፋ ቢትኮይን እና ክሪፕቶከረንሲ የሚደግፉ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ተመራጩ ፕሬዝደንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት " አሜሪካን የፕላኔታችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ለዲጂታል መገበያያዎች የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል። ይህን ተከትሎ በክሪፕቶ ኢንዱስትሪ ላይ የተጣለው ቁጥጥር ይላላል የሚል እምነት አለ።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " በፍጹም ቢትኮይናችሁን አንዳትሸጡ " ሲሉ ተናግረው ነበር።

የዓለማችን ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይት ከትራምፕ መመረጥ በኃላ በማይታመን ሁኔታ ጨምሮ ዛሬ ላይ ከ91,000 (ዘጠና አንድ ሺህ) ዶላር በላይ ሆኗል።

ሌሎች እንደ ዶጅኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችም ዋጋቸው ከፍ እያለ ነው። የዶናልድ ትራምፕ ቀኝ እጅ የሆነው ኢላን መስክ ዶጅኮይን በስፋት ያስተዋውቃል።

ክሪፕቶከረንሲ ምንድን ነው ?

ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን " የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ " ይለዋል።

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ።

በስፋት ከሚታወቁት መካከል ፦
- ቢትኮይን፣
- ኤቴሪያም፣
- ሪፕል እና ቢትኮይን ካሽ የሚባሉት ከበርካታ ክሪፕቶካረንሲዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል + ገንዘብ + መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል።

ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የወረቀት ገንዘብ ወይም ሳንቲም ሳይሆን በበይነ መረብ ላይ የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው።

ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው።

ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች አማካኝነት ቁጥጥር ይደረግበታል።

ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጠ/ጡ ይታመናል።

የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን ከ17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል ተብሎ ይታመናል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

#USA #Bitcoin #BBC #Mario #Crypto

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ የቢትኮይን ኩባንያዎችን ትኩረት ለምን ሳበች ?  በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ፣ ዋነኛው የቢትኮይን ኩባንያዎች መዳረሻ ሆኗል፡፡ ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ 10 ኩባንያዎች በዚሁ ፓርክ ውስጥ መሰረተልማት ገንብተው እየሰሩ መሆናቸውን፣ የአይቲ ፓርኩ ሐላፊ አቶ ሔኖክ አሕመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም በዚሁ ስራ ላይ የተሰማሩ አለምአቀፍ…
#Crypto #Ethiopia

ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሀይል ፍላጎት ማሟላት ትችላለች ?

" አሁን ያሉትን የክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሀይል ፍላጎት ለማሟላት ጥረት እናደርጋለን፡፡ አዳዲስ ካምፓኒዎች መቀበል ግን አቁመናል " - አቶ ሞገስ መኮነን

➡️ " ሁሌም ቅድሚያ የምንሰጠው ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ነው፡፡ በሀገር ውስጥ የሀይል እጥረት ሲያጋጥም፣ ለክሪፕቶ ከረንሲ ካምፓኒዎች የሚቀርበው ሀይል ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ እንደሚችል አስገዳጅ ስምምነት አለ !
"

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ ከዚህ በኋላ አዳዲስ የክሪፕቶከረንሲ ካምፓኒዎችን ላለመቀበል መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮነን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ " የክሪፕቶ ካምፓኒዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ፣ ያሉትን ካምፓኒዎች ፍላጎት ማሟላት እንጂ፣ ከእንግዲህ አዳዲስ ካምፓኒዎችን አንቀበልም " ብለዋል፡፡

በተቋሙ የሀይል አቅርቦት ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ቅድሚያ እንደሚሰጥም ገልፀዋል፡፡

አቶ ሞገስ መኮነን በዝርዝር ምን አሉ ?

" በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የክሪፕቶ ከረንሲ ካምፓኒዎች እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ነው፡፡ ይህ ኢንቨስትመንት ሁለት አመት ሆኖታል፡፡

ኢትዮጵያ ላይ ትኩረት ያደረጉበት ምክንያት፣ እኛ ጋር የኤሌክትሪክ ሀይል ዋጋ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋራ ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ ነው፡፡ በዛ ላይ ከታዳሽ የሀይል ምንጭ የሚገኝ መሆኑ ነው፡፡

አሁን በአጠቃላይ 36 የክሪፕቶከረንሲ ካምፓኒዎች አሉ፡፡ ስራ የጀመሩና ስራ ለመጀመር በሒደት ላይ የሚገኙ፡፡ እነዚህ ካምፓኒዎች ከፍተኛ የሀይል መጠን እንደሚፈልጉ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን እኛ ቅድሚያ የምንሰጠው ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ማሟላት ነው፡፡

የህዝቡና የአምራቹ ዘርፍ የሀይል ፍላጎት ሳይሟላ፣ ለክሪፕቶ ካምፓኒዎችም ይሁን ለውጭ ሀገራት የሚቀርብ ሀይል የለም፡፡ ሁሌም ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሀገር ውስጥ ፍላጎት መሟላት ነው፡፡ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪውም ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ከፍተኛ የሰው ሀይል የሚቀጥር ስለሆነ በሀይል አቅርቦት በኩል ቅድሚያ ያገኛል፡፡ በዚህም በማኑፋክቸሪን ዘርፉ ያሉ ባለሀብቶች ደስተኞች እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ለሀገር ውስጥ ፍላጎት ቅድሚያ ስለሚሰጥ ነው እንደዛ የሆነው፡፡

የሀገር ውስጥ ፍላጎት በሚጨምርበት ጊዜ ለጎረቤት ሀገራት የሚላከው ሀይል ይቋረጣል፡፡ ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሚቀርበውም ሀይል እንደዚሁ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

አሁን ላይ የሀይል እጥረት ችግር የለብንም እንጂ እንዲህ አይነት ችግር ቢያጋጥመን፣ ለነሱ የምናቀርበውን ሀይል እስከማቋረጥ የሚያደርስ ውል አለን፡፡ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎታችንንና የሀገር ውስጥ የሀይል ፍላጎትን በዚህ መልኩ ነው የምናጣጥመው፡፡ ከክሪፕቶ ካምፓኒዎች ዶላር ለማግኘት ተብሎ የሀገር ውስጥ የሀይል ፍላጎት አይጎዳም፡፡

የክሪፕቶ ካምፓኒዎቹ የሀይል ፍላጎት ከ 100 እስከ 400 ሜጋዋት ይደርሳል፡፡ እኛ የምንሰጣቸው ግን ከ20 እስከ 30 ሜጋዋት ብቻ ነው፡፡ አሁን ያሉት የክሪፕቶ ካምፓኒዎች እየቆዩ ያሉት የሚፈልጉትን የሀይል መጠን ስለሚያገኙ ሳይሆን ወደፊት እናገኛለን ብለው ተስፋ ስለሚያደርጉ ነው፡፡ እያደገ ከሚሔደው የሀይል ልማት መጠቀም ይፈልጋሉ፡፡

በርግጥ አሁን እየተሰሩ ያሉት ስራዎች የማመንጨት አቅማችንን እያሳደጉት ነው ያሉት፡፡ ሀይል የማመንጨት አቅማችን ሲያድግ የክሪፕቶ ካምፓኒዎችንም ፍላጎት ማሟላት እንችል ይሆናል፡፡ አሁን ባለው ኹኔታ ግን ከሀገር ውስጥ ፍጆታ የተረፈንን ነው የምናቀርብላቸው፡፡

አሁን ላይ የማመንጨት አቅማችን ወደ 6ሺህ ሜጋዋት ቢደርስም መሰረተልማቶቻችን ተቀብለው ማሰራጨት የሚችሉት 4ሺህ ሜጋዋት ያህሉን ብቻ ነው፡፡ አሁን ባለን መሰረተልማት ማቅረብ የምንችለው ይህን ነው፡፡ የ2 ሺህ ሜጋዋት ትርፍ አለን፡፡ ይህንን ትርፍ የማመንጨት አቅም ለተጠቃሚው ለማድረስ ግን በየአመቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ ህብረተሰቡ ጋር ካልደረሰ የእኛ ማመንጨት ብቻውን ትርጉም የለውም፡፡ 

የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር፣ የገጠር ኤሌክትሪክ ማስፋፋት ስራም እንደቀጠለ ነው፡፡ ይህን የምናደርገው ከዋናው ብሔራዊ የሀይል ቋት/ግሪድ ጋር በማገናኘትና ከመስመር ውጪ ባሉ አካባቢዎች በሚሰሩ ስራዎች አማካኝነት ነው፡፡ ህብረተሰቡ ተጠጋግቶ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ከዋናው መስመር ሀይል እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡

በገጠሩ አካባቢና በሀገሪቱ ዳርቻ የሚገኙ አካባቢዎች ደግሞ አኗኗኗቸው የተራራቀ ስለሆነ ከግሪድ ውጪ ካሉ አማራጮች ለምሳሌ ከፀሀይ ሀይል እና ከሌሎችም ምንጮች የሀይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትን ለማስፋፋት የፋይናንስ እጥረት አለብን፡፡ 85 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ መሰረተልማት ከውጪ ነው የምናስገባው፡፡ ይህን ለማድረግ የሚያስፈልገን የገንዘብ አቅም ከአለምአቀፍ አበዳሪዎችና ለጋሾች ነው የምናገኘው፡፡ የፋይናንስ እጥረቱን ከተለያዩ ምንጮች ነው የምናሟላው፡፡ ነገር ግን ያለብንን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ ሲባል ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች ቅድሚያ ሰጥተን የሀገር ውስጥ ፍላጎትን አንጎዳም፡፡

በሌላ በኩል፣ ተቋማችን ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች ሀይል በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱ መጀመሩ የውጭ ምንዛሪ ምንጩን እንዲያሰፋ ረድቶታል፡፡ በሌላ አባባል ከክሪፕቶ ካምፓኒዎች የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ መሰረተልማትን ለማስፋፋት አስተዋፅኦ እያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ለክሪፕቶ ካምፓኒዎች ከምናቀርበው ሀይል የሚገኘው ገቢ የኤሌክትሪክ ሀይልን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ እያገዘን ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ የሚፈልጉ እቃዎች እንገዛበታለን ከዚህ በፊት ያሉብንን አዳዎች እንከፍልበታለን፡፡

ከዚህ በኋላ ግን የክሪፕቶ ካምፓኒዎችን ተቀብለን አናስተናግድም፡፡ አሁን ያሉትን ካምፓኒዎች የሀይል ፍላጎታቸውን ለማሟላት ጥረት እናደርጋለን፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia