TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WKU

" አንድ ተመራቂ ተማሪ እና አንድ  መምህር ጉዳት ካስተናገዱ በኋላ ሁኔታዉ በቁጥጥር ስር ውሏል " - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራር

ከሰሞኑ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት እና አንድ መምህር ተጎድተዋል።

የግቢዉ ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በወቅቱ የተፈጠረው የተኩስ ድምጽ እና ሁኔታ እጅግ ረብሿቸው ነበር።

ይሁንና " ታጥቆ ወደ ግቢው የገባው አካል በቁጥጥር ስር መዋሉና ሰላም መሆኑ " ተነግሯቸው ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል።

ሁኔታውን በተመለከተ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊ " ጉዳዩ ድንገት በመፈጠሩ ለጥቂት ሰአታት ግርግር ቢፈጥርም በግቢዉ የጸጥታ ሀይል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል " ብለዋል።

በወቅቱ " የመመረቂያ ጽሁፍን በዲስፕሊን ምክኒያት እንዳያቀርብ የተከለከለ የነርሲንግ ተማሪ  ሽጉጥ ታጥቆ በመምጣት ጉዳት አድርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የመመረቂያ ወረቀቷን ታቀርብ የነበረዉንና ጓደኛዬ የሚላትን ' እኔ ካላቀረብኩ አንችም አታቀርቢም ' በማለት ሽጉጥ ተኩሶ በማቁሰል በዛ የነበሩትን መምህራን አባሯል " ሲሉ አስረድቷል።

ከዚህ በኋላ ሰዎችን ባይጎዳም ደጋግሞ መተኮሱ በግቢው ውስጥ ችግር መፍጠሩን የሚገልጹት ሀላፊዉ ይህም ተማሪዎችን መረበሹን ገልጸዋል።

በዚህ ወቅት የተሰማዉን የተኩስ ድምጽ የሰማዉ የግቢዉ የጸጥታ ሀይል ወጣቱን በፍጥነት በመቆጣጠር ሁለቱን ተጎጅዎች ወደህክምና ሊወስዳቸዉ እንደቻለና ገልጸዋል።

በወቅቱ ከተከሰተዉ ችግር ለመሸሽ መምህራኑ ባደረጉት ጥረት አንዱ በመስኮት ሲዘል ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበትና የሁለት እግሮቹ አጥንቶች ተሰብረዉ ከፍተኛ የአጥንት ህክምና በማስፈለጉ የግቢዉ ማህበረሰብ ገንዘብ እያወጣለት መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ ችሏል።

አንድ ጉዳዩን የምታውቅ ተማሪ ፤ " 1 ወር ከ15 ቀን ልጅ በፊት ደብድቧት ሆስፒታል ገብታ ፤  እሱም 2 ዓመት ተቀጥቶ ነበር። ከዛም በፊት መትቷት ያቃል። ባለፈው ደግሞ ዲፌንስ አቀርባለው ብሎ ሲከለከል ሽጉጥ ይዞ መተኮስ ጀመረ ልጅቷን ተኩሶ ስቷቷል ፤ ከዛ ይዞ ደብድቧታል። ጭንቅላቷ ተፈንክቷል። አንድ መምህርም ከፎቅ ዘሎ ተሰብሯል። አንድ ተማሪም ወድቃ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም ፈሶ ሰርጀሪ ተሰርቶላታል " ብላለች።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#ስራ #ደመወዝ

° " ያለስራና ደመወዝ በመቆየታችን ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀናል " - የመንግስት ሰራተኞች

° " ጉዳዩን እናውቀዋለን እየተወያየንበት ነው ፥ በአጭር ቀናት መፍትሄ ይሰጣቸዋል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለስልጣን

የደቡብ ክልል መበተኑን ተከትሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ የ " ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ሰራተኞች " ከስራ እና ከደመወዝ ውጭ ሆነው ወራት እንደተቆጠሩ ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባቀረቡት ቅሬታ ፥ ክልሉ ከፈረሰ በኋላ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢመደቡም እስካሁን ስራ አለመጀመራቸውን በዚህም ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል።

ከ2 ወር በፊት ዘግይቶ በተሰጣቸው ደብዳቤ ሆሳዕና ከተማ መመደባቸው እንደተነገራቸው ጠቁመዋል።

ቦታው ላይ ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም እንደሚሰጣቸውም ተገልጾላቸው ነበር።

በዚህም ግማሽ ሰራተኞች እቃቸውን በገንዘብ እጥረት ሽጠው እንዲሁም ቀሪውን በሌለ ገንዘብ ትራንስፖርት ከፍለው ቦታው ቢደርሱም አንድም የሚያስተናግዳቸው ሆነ የሚቀበላቸዉ አካል ማጣታቸውን አስረድተዋል።

በመሆኑም ያለደሞዝና ስራ በተመደቡበት ከተማ ለ2 ወራት መቆየታቸው ህይወትን ከባድ እንዳደረገባቸዉ ገልጸዋል።

በገንዘብ እጦት የምግብ መግዣ እንኳ እንስከማጣት መድረሳቸውን ከዚህም በላይ በቤት ኪራይ ችግር አብዛኛዉ ሰራተኛ ጎዳና ለመውጣት ጫፍ መድረሱን ተናግረዋል።

" ሆሳዕና የሚገኘው አዲሱ ቢሮ ስንሄድ #ጸሀፊ_ብቻ ነው የምናገኘው " የሚሉት ሰራተኞቹ " የሚመለከተው አካል ሌላዉ ቢቀር ጥያቄያችን ሊያደምጥ ይገባል " ሲሉ ቅሬታቸው ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞቹን ጥያቄ ይዞ ያናገራቸዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አማካሪ እና ልዩ ረዳት የሆኑትን አቶ ንጉሴ አስረስ ፥ ጉዳዩን እንደሚያውቁት በመግለጽ ችግሩ በቅርብ እንደሚፈታ ተናግረዋል።

ከሰሞኑ ሰራተኞችን በአካል አግኝተዋቸው ለማነጋገር እቅድ እንዳላቸውም የገለጹት አቶ ዘሪሁን " ለሁለት መቶ አስር ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል ለክልሉ ቀላል ነው " ብለዋል።

በቅርቡ ችግሩ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም ሌሎችም ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሊያነጋግራቸው እንደሚችል ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
#CentralEthiopiaRegion

@tikvahethiopia
#አፊኒ #ሲዳማ

በሲዳማ በህዝብ ዘንድ ቁጣ ፈጥሯል የተባለው መፅሀፍ ጉዳይ ምንድነው ?

ከሰሞኑ በዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የተጻፈ " አፊኒ " የተሰኘ መጽሀፍ በአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን ተመዝግቦ የባለቤትነት ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ በሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኩል ጥያቄ ተነስቷል።

ቢሮው ለአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በላከው የቅሬታ ደብዳቤ " ለዶክተር አራርሶ ገረመዉ ' አፊኒ ' በሚል ስያሜ የተሰጠው የባለቤትነት እዉቅና በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል " በማለት ገልጿል።

የተሰጠዉ እውቅና " የባለቤት " የሚል ሀሳብ የያዘ ሲሆን ይህም የድርሰት ስራ በመሆኑ የቅጅና ተዛማጅ መሆን እንደሚገባዉና " የፈጠራው ባለቤት " የሚለው ቃልም አግባብ አይደለም በማለት ገልጿል።

በመሆኑም ' አፊኒ ' የመላዉ የሲዳማ ህዝብ እንጅ የደራሲዉ የዶ/ር አራርሶ ገረመዉ የፈጠራ ንብረት አለመሆኑ ታዉቆ ማስተካከያ እንዲደረግ በማለት ማብራሪያና ማስተካከያ ጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩን ሰምቶ የመጽሀፉን ደራሲ አነጋግሯል።

ዶ/ር አራርሶ ገረመው ፤ የተፈጠረዉ ሁኔታ ከርሳቸዉ ቀድሞ ሶሻል ሚዲያዉን ማጥለቅለቁን ገልጸዋል ፤ " በዚህም አዝኛለሁ " ብለዋል።

ሁኔታውን በንግግር እንደፈቱት ገልጸው ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመመለስና ማህበረሰቡን ለማስቀደም በማሰብ ' አፊኒ ' የሚለዉ ርእስ እንዲስተካከል በመወሰን ስራ መጀመራቸውን አስረድተዋል።

' አፊኒ ' የሚለው ርዕስ ተቆርጦ የወጣ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አራርሶ ፥ አሁን ላይ መጽሀፉ ላይ ያለው ሙሉ አርእስት ' አፊኒ የሲዳማ ድንቅ ባህል ታላቅ ተቋም አስደማሚ የሰላም እሴት ' በሚል ለማስተካከል በደብዳቤ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንን መጠየቃቸውን ባለስልጣኑም እንደተቀበላቸውና ማስተካከያ እንደተደረገበት ገልጸዋል።

" ይህንን መጽሐፍ የጻፍኩት #የህዝቤን_ታሪክ ለማስተዋወቅ እና ለማጉላት መሆኑን በውስጡ ያሰፈርኩት አሳብ ይመሰክራል " ያሉት ደራሲው " በርዕሱ ምክኒያት የተፈጠረውን ቅራኔ በቀላሉ ከፈቃድ ሰጪው ጋር ተነጋግሮ መፍታት የሚቻል ቢሆንም በማህበራዊ ሚድያ የጥቂቶች ሀሳብ በዚህ ደረጃ መንጸባረቁ አስገርሞኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2 ዓመት ?

የህጻን ልጅ ፊት በጋለ ብረት ያበላሸው ወንጀለኛ ላይ የተወሰነው የ2 አመት ፍርድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነሳ።

አንድ ግለሰብ በጌዴኦ ዞን ፤ በይርጋጨፌ ከተማ የሚያሳድጋትን ልጅ " ጥፋት አጠፋሽ " በሚል በጋለ ብረት ፊቷን እጇንና እግሯን በማቃጠል ጉዳት አድርሶባታል።

በወቅቱ የህጻኗን ጉዳት የተመለከተውን መረጃ በአካባቢው ከነበሩ ነዋሪዎች የደረሰው ፖሊስ ህጻኗን ወደ ህክምና በመዉሰድ የተበላሸ ፊትና ሰውነቷ እርዳታ እንዲያገኝ በማድረግ ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ጉዳዩን የያዘዉ  የይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የሰውና የህክምና ማስረጃ ከተመለከተ በኋላ ግለሰቡ በ2 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ሰጥቷል።

ይሁንና በህጻኗ ላይ ከደረሰዉ አሰቃቂ ጥቃት አንጻር የተሰጠው ፍርድ አግባብ አይደለም ያሉ አካላት በተለይ ዜናውን የሰሙ ግለሰቦች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጌዴኦ ዞን ፍትህ መምሪያን አነጋግሯል።

የመምሪያው ሀላፊ የሆኑት አቶ ብዙአየሁ  ዘዉዴ ፥ የይርጋጨፌ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩን  መርምሮ 2 ዓመት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም በውሣኔ ላይ ዐቃቤ ህግ ቅሬታ ያለው በመሆኑ ይግባኝ ለጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ውሣኔውን ለሰጠዉ ፍ/ቤት መዝገብ ተገልብጦ እንዲሰጥ መጠየቁን ገልጸዋል።

ጉዳዩ  በሂደት ላይ መሆኑን የገለጹት ሀላፊው ቅሬታዉ ህጋዊ መሰረት መያዙን ገልጸዉ ወደፊት ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጡን ቃል ገብተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቀጣይ የሚኖረዉን የፍትህ ሂደት ተከታትሎ የሚዘግብ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#Hawassa

በሀዋሳ እንደ አዲስ አበባው አይነት የመንገድ ማስፋትና የማስዋብ ስራ / የኮሪደር ልማት / መታሰቡን ተከትሎ " የሚፈርሱ ይዞታዎቻችን ግምት ባልታወቀበት እና በቂ የሆነ የዝግጅት ጊዜ ባልተሰጠበት ይዞታችሁን አፍርሱ " ተብለናል ያሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ስራው ወደተግባር ከመግባቱ በፊት ካንዴም ሁለቴ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

በቅርቡ በነበረ መድረክ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ ፤ 10 መንገዶች መለየታቸውን እና እነዚህን ውብና ዘመናዊ አድርጎ በመስራት ለትዉልድ የሚተላለፍ አሻራ የመጣል እቅድ መያዙን ገልጸው ነበር።

በመድረኩ ተገኝተው የነበሩ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚደግፉ የካሳ እና የዝግጅት ጊዜ ግን እንዲሰጣቸዉ ጠይቀው ነበር።

ይህን ተከትሎ የንብረት ግምትን በተመለከተ ተመጣጣኝ ካሳ እንደሚኖርና የቦታ ሽግሽጎችም እንደሚደረጉ በመግለጽ ከንቲባዉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ይሁንና የከተማ መስተዳድሩ ከመረጣቸዉ 10 ቦታዎች መካከል 3ቱን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ማሰቡን ተከትሎ በተለይ ከስሙዳ በሳዉዝ ስታር ሆቴል ወደ ኢንዱስትሪ መንገድ የሚሄደው እና ከሻፌታ አደባባይ አስከሳዉዝ ስፕሪንግ ያለው መስመር ያሉ ነዋሪዎች ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በዚህ በኩል በርካታ የመኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የሚነኩ መሆኑን ተከትሎ ነዋሪዎች ድንጋጤ ውስጥ መግባታቸዉን ተናግረዋል።

በከተማ መስተዳድሩ በእቅድ የተያዘዉ  የከተማ ልማት የምንደግፈዉ ቢሆንም የካሳና የቦታ ሽግሽግ ጉዳይ ባልተወሰነበትና ሰዉ ዝግጅት ባላጠናቀቀበት " በቅርቡ ፈረሳ ይጀምራል " መባሉ አሳስቦናል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ በተሰጣቸው ደብዳቤ በ2 ቀን ውስጥ አፍርሰው ማስተካከያ እንዲያደርጉ መባላቸውን ጠቁመዋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚፈርሱ ድርጅቶች መኖሪያ ቤቶችና አጥሮች ምልክት በመደረጉና ስራውበፍጥነት ይጀመራል መባሉን ተከትሎ ፦
➡️ የካሳና የቦታ ለዉጥ ወይም ሽግሽግ ጉዳይ ምን ይመስላል ?
➡️ በትክክል ስራዉስ መች ይጀምራል ? በማለት ጥያቄ ይዘን የሚመለከተዉን አካል ለማናገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ይዞ በቅርቡ ለመምጣት ይሞክራል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ የስፓርት ውርርድ ( #ቤቲንግ ) ቤቶች እየታሸጉ / እየተዘጉ ይገኛሉ። ይህ ተከትሎ የስፖርት ውርርድ ቤት ባለቤቶች " እንዴት የንግድ ፈቃድ እያለን ይዘጋብናል ? " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል። እነዚህ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ከወራት በፊት በተለያዩ ምክኒያቶች ተዘግተው የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ተከፍተው ነበር። አሁን ላይ ተመልሰው መዘጋት/መታሸግ መጀመራቸው…
#Update

" የስፖርት ውርርድ ቤቶችን የመዝጋትና የመክፈት አሰራር አድሎአዊነት የተንጸባረቀበት ነው " - ቅሬታ አቅራቢዎች

" የተከፈቱ ቤቶች ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ደብዳቤ ያመጡ ናቸው " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

በቅርቡ በሀዋሳ ከተማ ያሉ የስፖርት ውርርድ ቤቶች  " ህጋዊ አይደሉም ፣ በብዛት  የተከፈቱበት አካባቢም የትምህርትና የመኖሪያ ሰፈር ነው " በሚል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቢዘጉም ከቀናት ቆይታ በኋላ ግን የተወሰኑት ተከፍተዉ ስራ ጀምረዋል።

ይህንን ተከትሎ ፥
- ለምን ሁሉም በህግና ስርአት እየሰራ እና ግብርም እየከፈለ እያለ በከፊል ተከፍቶ በከፊል ይዘጋል ?
- ቤቶቹን የመዝጋትና የመክፈት ስራን የሚሰራዉ የከተማው ፖሊስ አሰራሩ አድሏዊነት የታየበት ነው፤
- ገንዘብ ሰጥተው የሚያስከፍቱ ሰዎችም እንዳሉ እየተሰማን ነው ሲሉ የስፖርት ውርርድ ቤታቸው የተዘጋባቸዉ ግለሰቦች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የከተማዉ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፥ አሁን ላይ ተከፍተዉ ወደስራ የተመለሱት ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህጋዊ ደብዳቤ ያቀረቡ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም " ለሀገር ፈጽሞ ጥቅም የማይሰጠዉ የቨርቹዋል አሰራር አሁንም እንደተከለከለ ነው። ካሁን በፊት እንደህግ ያስቀመጥነዉ የመኖሪያ ቤትና የትምህርት ቤቶች ዙሪያ የተጣለዉ ክልከላ ዛሬም ቀጥሏል " ብለዋል።

ከዚህ ውጭ አከፋፈቱን በተመለከተ የሚነዛዉ ስም ማጥፋት አግባብ አለመሆኑን ገልጸዉ ማንኛዉም አካል ህጋዊ ሆኖ ከመጣ ድርጅቱን ማስከፈት እንደሚችል ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል፣ በሥራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ።

አንድ ሹፌርም ህይወቱ አልፏል።

ዛሬ ከረፋዱ 3 ሰዓት ላይ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ የደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ሾፌርን ጨምሮ በስራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ ህይወት ቀጥፏል።

አደጋው በወረዳው ' ኤሬርቴ ወንዝ ' አጠገብ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ተነግሯል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ የሰጡት የሲዳማ ክልል ትራፊክና አደጋ መከላከል ተጠሪ ኮማንደር ከበደ ኮኔራ አደጋው ጠዋት 3:00 ሰዓት አካባቢ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር መድረሱን አረጋግጠዋል።

በወቅቱ የአካባቢውን የተሽከርካሪ ፍሰት ሲቆጣጠር የነበረው ትራፊክ ፖሊስ አንድ የሚኒባስ አሽከርካሪን አስወርዶ በመነጋገር ላይ እያለ አቅጣጫውን የሳተ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከዳራቸዉ ከነበረው ሲኖ ጋር እንዳጣበቃቸዉና ሁለቱም ወዲያዉ ህይወታቸዉ እንዳለፈ ገልጸዋል።

" በአካባቢዉ የነበረዉ ብቸኛ የትራፊክ ፖሊስ እና መረጃ አቀባያችን በመሰዋቱ አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልቻልንም " ያሉት ኮማንደር ወደቦታዉ ያቀኑት ባልደረቦቻቸው የሚያቀብሉት መረጃ በኋላ ላይ ለህብረተሰቡ  እንደሚያጋሩን ተናግረዋል።

በአደጋዉ የሁለቱ ዜጎች ህይወት ከመጥፋቱ ባለፈ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#Sidama #Hawassa

° " በሀዋሳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነዳጅ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " - የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች

° " በእጃችን ምንም ነዳጅ ባለመኖሩ ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ ይታገሰን " - የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ


ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 በሀዋሳ ከተማ ያሉ ማደያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች መቆማቸውን በመግለጽ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" ከሰሞኑ በሰልፍና በጎን በሚገቡ ህገወጥ ቀጅዎች ስንማረር መሰንበታችን ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በየቀኑ በቴሌግራም የሚለቀቀዉ የነዳጅ ፕሮግራም ተቋርጦ በከተማው ውስጥ ያሉ ማደያዎች ሁሉ ዝግ ሆኑብን "  የሚሉት አሽከርካሪዎች በዚህም በእጅጉ ተቸግረናል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎትን አነጋግሯል።

እሳቸውም ፤ " እንደከተማ አንድ ማደያ ብቻ አገልግሎት እየሰጠ ነው " በማለት በከተማዉ ምንም አይነት ነዳጅ አለመኖሩን ገልጸውልናል።

የቴሌግራሙ ፕሮግራም አለመውጣቱም ከዚህ የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ ችግሩ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ስብሰባ መቀመጣቸውን ገልጸው "  ማህበረሰቡ እና አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው እንዲታገሱ " ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama #Hawassa ° " በሀዋሳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነዳጅ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " - የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ° " በእጃችን ምንም ነዳጅ ባለመኖሩ ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ ይታገሰን " - የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 በሀዋሳ ከተማ ያሉ ማደያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች መቆማቸውን በመግለጽ ቅሬታቸዉን…
#Sidama

በሀዋሳ ከተማ 1 ሊትር ቤንዚን በድብቅ እስከ 180 ብር እየተሸጠ ነው።

በከተማይቱ ያሉ ሁሉም ማደያዎች ውስጥ ቤንዚን የለም ተብሏል።

ይህን ተከትሎ 1 ሊትር ቤንንዚን ከ150 ብር እስከ 180 ብር በድብቅ እየተሸጠ ይገኛል።

ቀድሞውም ቢሆን በከተማዋ በድብቅ ነዳጅ ይሸጥ ነበር። ዋጋውም 100 ብር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በመላ ከተማይቱ ነዳጅ መጥፋቱን ተከትሎ እስከ 180 ብር ደርሷል።

የከተማ ውስጥ ታክሲዎች በተለይ በከተሞች ዳርቻ ዋጋቸዉን እጥፍ ከማድረግ በዘለለ ኮንትራት ካልሆነ አንጭንም እያሉ መሆኑን ሰምተናል።

አንድ የሀዋሳ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል  " ዛሬ በሀዋሳ 1 ሊትር ቤንዚል ከ170 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ነው። በየትኛውም ነዳጅ ማደያ ዛሬ ቤንዚል የለም " ብሏል።

" አንዳንድ ታክሲዎች ዝም ብለን ከምንቀመጥ ብለው 2 ሊትር ከ320 ብር ጀምሮ እየገዙ ፤ የ5 ብር መንገዶችን በ10 ብር እየጫኑ ነው ፤ ከዛ ውጭ ሌሎች በተለይ ባጃጆች በየጥሻው ቆመው ነው ያሉት " ብለዋል።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮም ሆነ የነዳጅ ጉዳይ የሚመለከተዉ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ትናንት ስብሰባ ላይ እንደነበሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

ስብሰባውን ተከትሎ እስካሁን ምንም አዲስ ነገር አልተፈጠረም።

በትላንትናው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት  የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎት " ጉዳዩ አገር አቀፍ ችግር ነው " ብለዋል።

በማደያዎች ነዳጅ አለመኖሩን እና መንገድ የጀመረ የነዳጅ ጫኝ ቦቴ እንደሌለ በመግለጽም ማህበረሰቡ እንዲታገስ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#የጤናባለሞያዎች

" የ5 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ አልተከፈለንም !  አፋጣኝ ምላሽ እንፈልጋለን " - በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ ሆስፒታል ሰራተኞች

" በጀቱ ስለተለቀቀልን ክፍያዉን በሁለት ቀን ውስጥ እናጠናቅቃለን ተረጋጉ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሀመድ ሆስፒታል ውስት የሚሰሩ ሰራተኞች 5 ወር ሙሉ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ለወራት የትርፍ ሰአት ክፍያ ስንጠይቅ ነበር " ያሉት ሰራተኞቹ ከሰሞኑ ድምጻቸዉን ለማሰማት ሰልፍ ለመውጣት መገደዳቸውን አመልክተዋል።

" የዘገየዉ ገንዘባችን ይሰጠን  !! " ሲሉም ለሚመለከተዉ አካል መልእክታቸዉን አሰምተዋል።

" የኑሮ ዉድነት ምን ያክል ፈተና እንደሆነብን እየታወቀ የትርፍ ሰአት ክፍያችን በጠየቅን ቁጥር ቀጠሮ መስጠት የማይሰለቸዉ የሆስፒታሉ አስተዳደር ትእግስታችን ተፈታትኖታል " የሚሉት ሰራተኞቹ " ከዚህ በላይ መታገስ የምንችልበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናችን ጥያቄያችን በቶሎ ይመለስ " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞቹን ጥያቄ ይዞ የሆስፒታሉን ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያኖ ሻንቆን አነጋግሯል።

" ምንም እንኳን ችግሩ የታወቀ ቢሆንም የ5 ወር መዘግየት ሰልፍ የሚያስወጣ አልነበረም " ብለዋል።

አሁን ላይ ክፍያዉን ለማጠናቀቅ ቢበዛ 2 ቀናት ብቻ እንደሚበቃቸዉ ገልጸዋል።

የገንዘብ እጥረቱ የተከሰተዉ የነበረውን የበጀት እጥረት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲው ቅድሚያ ለተማሪ በማለቱ እንደሆነ አስረድተዋል።

" አሁን ላይ በጀቱ ተለቋል " ብለዋል።

ለክፍያው የተፈቀደው ገንዘብ በጽሁፍ እንጅ በካሽ አለመለቀቁን ተከትሎ ክፍያዉ በቶሎ አለመጀመሩን የገለጹት ስራ አስኪያጁ ፥ " አሁን ገንዘቡ በመድረሱ በ2 ቀን ውስጥ ክፍያዉ ይጠናቀቃል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

🔴 " የቤንዚን አቅርቦት ባለባቸው ማደያዎች የፀጥታ መዋቅር እየተቆጣጠረ ተገቢዉ ስርጭት እየተካሄደ ነዉ " - ግብረ ኃይሉ

🔵 " ምንም እንኳን ማደያዎች አካባቢ ያለው ግብግብ ቢሻሻልም አሁንም ተሰልፎ መዋል ነው " - ነዋሪዎች

በሲዳማ ክልል፣ በሀዋሳ ከተማ የነበረዉን ሕገወጥ የቤንዚን ንግድ በተመለከተ ተደጋጋሚ መረጃዎችን መለዋወጣችን ይታወሳል።

ከሰሞኑን የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ መገለጹም የሚዘነጋ አይደለም።

ምንም እንኳን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ቢቀመጡም እርምጃዎችም እየተወሰዱ እንደሆነ ቢነገርም አሁንም ያልተቀረፉ ችግሮች መኖራቸውን መታዘቡን የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከስፍራው ያለውን ሁኔታ አድርሶናል።

በክልሉ የነዳጅ ሥርጭቱን ለመቆጣጠር ግብረ-ኃይል መቋቋሙን ተከትሎ የከተማዉ ንግድ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ፤ ሁለት ከፍተኛ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፤ ሦስት ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና በአጠቃላይ ከ8 ሺህ ሊትር በላይ በሕገወጥ መንገድ የተከማቸ ቤንዚን መያዙ ተገልጿል።

ሆኖም ግን ግብረ-ኃይሉ ከቀናት በፊት ባካሄደው ውይይት ላይ " ከዚህ ቀደም ተሽከሪካሪ ተለይቶ ይደለደል የነበረዉ አሰራር ከአሁን ጀምሮ አይኖርም " ተብሎ ቢገለጽም ይህ የተሽከሪካሪ ምደባ አሁንም መቀጠሉን ታዝበናል።

ይህ ለምን ሆነ ? ብለን ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ መምሪያ ኃላፊ ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን " ምደባዉን ማስቆማችን አይቀርም አሁን ላይ ባለዉ እጥረት ለቁጥጥር ስለሚያስቸግር ነዉ ያላቆምነዉ። ከአራት በላይ ማደያዎች አቅርቦት ሲኖር ምደባዉን እናስቆማለን " የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

በቀጣይም በባለሙያዎች እና ማደያዎች ላይ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን የተረጋጋ የቤንዚን ስርጭት እስኪፈጠር ግብረሃይሉ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

በተጨማሪም ግብረኃይሉ፦

- የቤንዚን አቅርቦት ባለባቸው ማደያዎች የፀጥታ መዋቅር እየተቆጣጠረ ተገቢዉ ስርጭት እየተካሄደ ነዉ።

- በሕገወጥ ግብይትና ተባባሪነት የተጠረጠሩ 34 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

- ለጥቁር ገበያዉ አመላላሽ የነበሩ ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።

- የፀጥታ ሃይሎችና በእንግድነት ወደ ከተማዋ የሚገቡ ሰዎች እየተጣሩ ያለ ሰልፍ እንዲቀዱ ይደረጋል ... ብሏል።

ማደያዎች ምን አሉ ? ማደያዎች ግብረኃይሉ በሚመራው አካሄድ ስርጭት እየተካሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች እና ነዋሪዎች ምን ይላሉ ?

ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች በማደያዎች አከባቢ ይስተዋሉ የነበሩ ግብግቦች መቀነሳቸውንና አሁን ላይ እየተቀዳ ያለዉ በተራ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ሆኖም ግን የባጃጅ አሽከርካሪዎች " ከሰልፉ ብዛት የተነሳ አሁንም ተሰልፎ ዉሎ አለመቅዳት ስላለ፥ አይደለም የምንሰራበት ተሰልፈን ዉለን 12:ዐዐ ሲዘጋ ወደቤት መመለሻ እያጣን ነዉ " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

አሁንም ቢሆን የቤንዚን ሰልፉ በጣም ረጃጅም መሆኑን የገለጹት አሽከርካሪዎች " የታክሲ አገልግሎት ሰጥተን ቤተሰቦቻችንን የምንመራ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

ቁጥጥሩ ወቅታዊ እንዳይሆን ስጋት ያላቸው አሽከርካሪዎቹ የዕለቱ የቤንዚን ስርጭት ከተዘጋ በኋላ በአንዳንድ ማደያዎች ያለ ተራ የመቅዳት ተግባራት እንደሚስተዋሉ ጠቁመዋል።

የሞተር ባለንበረቶችም እንደልብ ነዳጅ ማግኘትና መንቀሳቀስ አሁንም እንዳልተቻለ ፤ እርምጃዎች ተወሰዱ ከተባለ በኃላ በተጨባጭ የታየ ለውጥ መመልከት እንዳልሻሉ ጠቁመዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ ሌሎች የከተማው ነዋሪዎች " በማደያዎች አከባቢ መሻሻሎች ቢኖሩም ችግሩ አልተቀረፈም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዞች ይስተዋላሉ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia