TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠናቋል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው 5ኛ ዓመት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱ ታሽጎ ተልኳል። ካለው የተማሪ ቁጥር አንፃር  ማድረግ የቻልነው እጅግ ጥቂት ቢሆንም በቀጣይ ወራት ተጨማሪ ዘመቻ በማድረግ ከቤተሰባችን አባላት ቤት መፅሀፍ በመውሰድ ተጨማሪ ለመላክ ጥረት እናድረጋለን። በዚህ ስራ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያለማንም…
#እናመሰግናለን

በኮቪድ ወረርሽኝ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍትን ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናቆ መፅሀፍቱን ለት/ቤቶች አድርሰናል።

በአጠቃላይ የተሰበሰበው መፅሀፍ እንዲከፋፈል ያደረግነው ፦

- መርሳ 2ኛ ደረጃና ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ፣ ውርጌሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሲሪንቃ ሁለተኛ ደረጃ እና ሙሉ ሳይክል ት/ቤት እነዚህ በአማራ ክልል በጦርነት ቀጠና የነበሩ ት/ቤቶች ሲሆን የመማሪያ መፅሀፍት እጥረት እንዳለባቸው ከአካባቢው ቤተሰቦቻችን በደረሰን መረጃ ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ አከፋፍለናል። ለእነዚህ ት/ቤቶች በቀጣይም ተጨማሪ ለመላክ ታቅዷል።

- ዶሮ ግብርና ወደዪ ሜዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አጋዥ እና በቀድሞው ካሪኩለም የታተሙ መፅሀፍትን የላክን ሲሆን በአዲሱ ካሪኩለም የታተሙትን ኮፒ ለመላክ እየተዘጋጀን ነው። በተላኩት መፅሀፍት ውስጥ የልጆች መማሪያ የሚሆኑ የተረት መፅሀፍት አሉበት።

- ማላካ ፣ ኢርባኖ ፣ ህዳሴ የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ት/ቤቶቹ የሚገኙት በደቡብ ክልል ከጅንካ ከተማ በ50 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ሲሆን በስፍራው ያሉ ቤተሰቦቻችን በመማሪያ መፅሀፍ ግብዓት እጥረት ሳቢያ በት/ቤቶቹ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የሚፈለገውን ያህል ውጤት አይመዘገብም ብለውናል። በዚህም ለሶስቱም ከተሰበሰበው መፅሀፍ በማካፈል ልከናል። ካለው ተማሪ ብዛት በቀጣይ ዙርም ተጨማሪ ለመላክ አቅደናል።

- ቤተሰብ የህዝብ ቤተመፅሀፍ አ/አ ከተማ መካኒሳ አካባቢ የተከፈተ አዲስ ቤተመፅሀፍ ሲሆን መፅሀፍ እንደሚያስፈልጋቸው በገለፁልን መሰረት ተመልክተን ከተሰበሰበው መፅሀፍ አካፍለናል ፤ በተጨማሪ 10 ሺህ ብር ሰጥተናል። በቀጣይ ተጨማሪ መፀሀፍ ለመስጠት ታቅዷል።

- ፈንታው ድንቁ መታሰቢያ አፀደ ህፃናት እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #ቆቦ የሚገኝ ሲሆን በጦርነት ወቅት ለህትመት የሚገለገሉበት ኮምፒዩተር በመሰረቁ 2 ኮምፒዪተርና መፅሀፍትን ልከናል።

(መፅሀፍቱ የተበረከተው ከአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ነው፤ መፅሀፍ ያበረከቱ ቤተሰቦቻችን ስም ዝርዝራቸው በ @tikvahuniversity ላይ ይገኛል ፤ በዚህ ዙር በየቤቱ እየተኬደ ከተሰበሰበው መፅሀፍ በተጨማሪ ከመቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መፅሀፍት በቤተሰቡ ስም ተገዝተው ተጨምረዋል)

ያጋጠሙ ችግሮች ፦ በዚህ ዙር #በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ እንዲሁም መፅሀፉን ለመላክ ከገጠመ የትራንስፖርት ችግር ውጭ ሁሉንም በቤተሰቡ አቅም ለማድረግ ተሞክሯል።

በቀጣይ ፦ አሁን የጎደሉትን መሙላት እና ተጨማሪ መላክ እንዱሁም በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለመድረስ ታስቧል።

ከአንድ ወር በኃላ በድጋሚ ሌላ ዙር በየቤቱ መፅሀፍ ለማሰባሰብ የሚሰራ ሲሆን በዚህ ዙር በቲክቫህ ላይ ማስታወቂያ የሚያሰሩ / መልዕክት የሚያስናግሩ ሁሉም ድርጅቶች የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው የማስታወቂያ / መልዕክት ለቤተሰቡ መላኪያ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል።

ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ ፦

👉 #ንፁህ_ወረቀቶችን (ኮፒ ለማድረግ) ፣ 
👉 ያገለገሉ በየቤቱ ያሉ ኮምፒዩተሮችን ፣ ታብሌቶችን
👉 ከከተማ ለወጡት ትምህርት ቤቶች ከመማሪያ መፅሀፍ በተጨማሪ አስተማሪ እና ጥላቻ የማይዘሩ የልብ ወለድና ሌሎች መፅሀፍትን የምናሰባስብ ይሆናል።

(ከዚህ ቀደም በነበሩ 4 ዓመታት በየዓመቱ የነበረውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለው ችግር በየአንድ እና ሁለት ወር ለማድረግ ይሰራል)

እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የምናድረገው እጅግ በጣም ጥቂት ቢሆንም ይህን ለማስፋት እንሰራለን ፤ ሁሉም በያለበት #የራሱን ጥቂት አስተዋፆ ማድረግ ከቻለ ብዙሃንን መድረስ ይቻላል። ለማድረግ አቅም ቢያንሰን እንኳን ለወገናችን በጎ በማሰብ ችግሩን እንካፈለው።

#TikvahFamily❤️
0919743630
0703313630

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT