TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቤኒሻንጉል_ጉምዝ

ለኢንቨስትመንት መሬት ከወሰዱና ከአላለሙ ባለሃብቶች በመንጠቅ ለአልሚ ባለሀብቶችና ለወጣቶች እንደሚሰጥ የቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ በጀመረው የ5ኛ 5 ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 9ኛ ጉባኤም የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ሲገመግም እንደገለጸው፣ በተለይ የግብርናውንና የማዕድን ዘርፍ ስራዎችን ለመስራት መሬት ወስደው ያላለሙት ይነጠቃሉ፤ ለወጣቶችና ለአልሚ ባለሃብቶችም ይሰጣል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ታደሰ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ክልሉ የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት እንደሆነ ጠቅሰው፤ በተለያዩ ዘርፎች ማልማት የሚፈልጉ ባለሃብቶች መሬት ተረክበው መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

Via አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነገ ነሃሴ 20 እስከ መስከረም 30 በመላው ሀገሪቱ ይካሄዳል!!

ላለፉት አመታት በአብዛኛውን በከተሞች አካባቢ የሰራነውን ስራ #በማጠናከር ዘንድሮ ደግሞ ከከተማ ውጭ ወደሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረታችንን እናደርጋለን።

ምን አይነት መፅሃፍት ነው ከቤተሰባችን አባላት የምናሰባስበው?

•ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ መፅሃፍትን/Text Book/ እንዲሁም አጋዥ መፅሃፍት ብቻ

•በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትውልዱን ይጠቅማል፤ እውቀት ያስጨብጣል የምንላቸው መፅሃፍት።

•ትንሹ መስጠት የሚቻለው መፅሃፍ 1

•መፅሃፍቱ የሚገቡት ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ እና በአካል ሄደን ለምንለያቸው ቤተ መፅሃፍት

#እርሶ ምን ማድረግ ይችላሉ??

√ቢያንስ አንድ የመማሪያ መፅሃፍ ለሚወዷት ለኢትዮጵያ መለገስ ይችላሉ። እንዲሁም ከፍተኛ የመፅሃፍት ችግር ያሉባቸው ቦታዎችን በመለየት የማስተባበር ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

•TIKVAH-ETH በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ይህን ሀገራዊ ስራ እንድታግዙ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።

•የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከተማራቹባቸው እና ስትጠቀሟቸው ከነበሩት መፅሃፍ መካከል ቢያንስ አንዱን ለመጪው ትውልድ በስጦታ አበርክቱ።

•በStopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የነበራችሁ የቤተሰባችን አባላት ይህን ለሀገርና ለትውልድ የሚሰራን ስራ በሙሉ አቅማችሁ እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

•በውጭ ሀገር የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቃሚ ናቸው የምትሏቸው መፅሃፍት በመላክ አልያም እዚህ ሀገር ባላችሁ ወዳጅና ዘመድ መፅሃፍት እንዲገዛ በማድረግ ይህን

#ኦሮሚያ
#አማራ
#ትግራይ
#ደቡብ
#ሱማሌ
#አፋር
#ሀረሪ
#ጋምቤላ
#ቤኒሻንጉል
#አ/አ ከተማ አስተዳደር
#ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

🏷በማኛውም አይነት ቋንቋ የተዘጋጀ የመማሪያ መፅሃፍ መለገስ ይቻላል!!
-------------------------------------------------------
በአሁን ሰዓት ልየታ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል፦

#ራያ_ቆቦ በራያ ቆቦና ዙሪያዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መፅሃፍት ለመለገስ እና ይህን ስራ ለማስተባበር ከቤተሰባችን አባል #ሉላይ ጋር ይገናኙ፦ +251949256094

#ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ደግሞ ከቤተሰባችን አባል መሃሪ 0915034762/መሃሪ/ ጋር መገናኘት መፅሃፍ መለገስ ትችላላችሁ።

ሌሎች አካባቢዎች ላይ እኛም ለሀገራችን መስራት እንፈልጋለን የምትሉ እውቅና ያላችሁ ማህበራት ካላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ

" በጸጥታ ችግር በሙሉና በከፊል የወደሙ 287 ትምህርት ቤቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ጥገና ያስፈልጋቸዋል" ሲል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዘነበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "በጸጥታ ችግር በሙሉና በከፊል የወደሙ 287 ትምህርት ቤቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ጥገና ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል።

"እንደሚታወቀው ክልሉ ከዚህ በፊት መተከልና ከማሽ ዞኖች አካባቢ የነበረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በሙሉና በከፊል የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሉ" ያሉት አቶ ምትኩ፣ "እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ የመገንባት አሁን ማኅበረሰቡ የጀመረው ሥራ አለ። መንግሥትም ደግሞ ራሱን አስችሎ ከባለ ሃብቶች፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ ትምህርት ቤቶችን የመጠገን ሁኔታ አለ" ሲሉ ተናግረዋል።

ወደሙ የተባሉት ተቋማት የት አካባቢ እንደሆነ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም፣ በከማሽ፣ መተከል ዞኖች እዲሁም በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ መሆኑን ገልጸው፣ የወደሙት ትምህርት ቤቶች ብላክ ብርድ፣ ወንበር፣ ቤተ መጻሕፍት፣ አጋዥ መጻሕፍት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ውድመቱን ተከትሎ ምን ያህል ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ እንዲገልጹ ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ምትኩ፣ "ወደ 50ሺሕ ገደማ ሕፃናት ናቸው በዚህ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑት" ብለዋል።
50 ሺሕ ገደማ ሕፃናት ሲባል በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ ቤተሰቦቻቸው በኢኮኖሚ ችግር ላይ በመሆናቸውና አብዛኛዎቹ ግን በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ደረሰ ከተባለው የትምህርት ቤቶች ውድመት በተጨማሪ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው 2.4 ሚሊዮን ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን፣ 1,218 ትምህርት ቤቶች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ቢከፈቱም 722ቱ እንዳልተከፈቱ መረጃዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ወቅቶች ሲገልጽ ተስተውሏል።

በአፋር ክልል ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 65 ትምህርት ቤቶች አምስቱ መልሶ ግንባታ እንደተደረገላቸው፣ በከፊል ከወደሙት 694 ትምህርት ቤቶች መካከል 34ቱ እንደተጠገኑ እንዲሁም በ2016 የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 245 ሺሕ ተማሪዎች እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የተመዘገቡት 126 ሺሕ ተማሪዎች መሆናቸው ተመላክቶ ነበር።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-09

@tikvahethiopia