TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ህዝቡ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መታገል አለበት"– የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት
.
.
የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮችን ሌላ መልክ በመስጠት አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳና እርስ በእርሱ እንዲጋጭ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መላው ህዝብ እንዲታገል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ ጥሪ አቀረቡ።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ጥሪውን ያቀረቡት በአዳማ ከተማ ዛሬ በተጀመረው 9ኛው የጨፌው ጉባኤ ላይ ከጨፌው አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

አባላቱ በክልሉ ሰላም፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ክልሉ በአዲስ አበባ ላይ ካለው ጥቅም ጋር የተያያዘ እና ሌሎች በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ በዚሁ ወቅት ህዝቡ ጠረፍ አካባቢ ይፈፀም የነበረውን የፖለቲካ #ሴራ ወደመሃል አገር ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት ሊገታ ይገባል ብለዋል።

ህገ-ወጥነትን ለመከላከል የሚወሰደውን እርምጃ እንደአብነት ያነሱት አቶ ለማ የህዝቡን ጥቅም ማእከል አድርጎ የሚሰራ አመራር እና ህዝቡ ሌሎች በሚቀርፁለት አጀንዳ መመራት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

እንዲያም ሆኖ “ህገ-ወጥ ቤቶች ሲገነቡ ቁጭ ብሎ የሚመለከት አመራር እያለ ቤት እንዲፈርስ መደረጉ በራሱ #ጥፋት ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

የቀበሌና የጎጥ አመራር እንዲሁም የከተሞቹ ካቢኔዎች ቤቶቹ ሲገነቡ ያለእነርሱ እውቅና መገንባታቸው፤ ከዚህም አልፎ ግንባታዎቹን በእጅ አዙር ህጋዊ ሲያስደርጉ በመቆየታቸው ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላቸውን ጥቅም አስመልክቶ በተነሳው ጥያቄ ላይ ማብራሪያ ሲሰጡም ለውጡን ለመቀልበስ በዳራ አገር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች አሁን በአዲስ አበባ ጉዳይ አንዱን በሌላው በማስነሳት እርስ በእርስ ለማበላላት የሚፈፅሙት ተግባር ስለሆነ ህዝቡ ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ጉዳይ በታሪክና በህገ-መንግስቱ መሰረት በምክክርና ህግን በተከተለ ሁኔታ ብቻ የሚፈታ እንደሚሆነም ነው አቶ ለማ ያብራሩት።

የልማት ፕሮጀክቶች መጓተት ዋነኛው ምከንያቶች የፋይናንሰ ችግር፣ የተቋራጮች አቅም ማነስ እንደሆነም አነሰተዋል።

የእነዚህ ሁለት ችግሮች ውጤት ተደማምሮ በልማት ፕሮጀክቶቹ ላይ ጫና ማሳደሩን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ ተናግረዋል።

ከዚሀም በተጨማሪ የክልሉ መንግስት በሰላም ማስከበርና በተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ መጠመዱ የልማት ፕሮጀክቶቹ ቁጥጥር እንዲላላ ማድረጉንም አንስተዋል።

በሰላም ማስፈን ተግባር ላይ የክልሉ መንግስት ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ሰላም ለማውረድ በትእግስት ያከናወነውን ተግባር እንደ ድል መቁጠር ይገባል ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

አስከ ነገ የሚቆየው ጉባኤው በአስፈጻሚ አካላት የተከናወኑ ስራዎችን ይገመገማሉ፣ አዋጆችን ይጸድቃል፤ ልዩ ልዩ ሹመቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia