TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#HopR የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል። አሁን ላይ ጠቅላይ…
#ፓርላማ

" እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ! " - አበባው ደሳለው (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ምንድነው ?

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" በባለፈው ዓመት መጨረሻ የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ሰኔ 28 ወቅት ያነሳናቸው በርካታ ከህዝብ ጥያቄዎች ነበሩ።

ነገር ግን እነዛ ጥያቄዎች ስላልተመለሱ ከዛ ብዙም ለየት ያለ ጥያቄ አይደለም የምንጠይቀው ምክንያቱም ችግሮቹ እየተባባሱ ስለመጡ።

በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጻሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር ፣ እገታ ፣ ጾታዊ ጥቃት ፣ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ ከኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ያኔም ነበረ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ። በተለይ በአማራ ክልል ያለው ችግር ደግሞ አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።

አሁንም ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው ፣ ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ ፣ በአማራ ክልል እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።

የኛ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ አመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው ያሉት። ፍርድ ሳያገኙ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል። ከዚህም የሚብሱ አሉ። ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ለሁለት ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።

ከፍተኛ የኑሮ ውድነቱን ስናይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አድርገናል፣ የብር የመግዛት አቅምን አዳክመን ኢኮኖሚው እንዲንሰራራ እናድረጋለን በሚል የተለያዩ ድጎማዎችን ተደርገዋል የደመወዝ ጭማሪ እስካሁን መንግስት ሰራተኛው ክሲ ውስጥ አልገባም ኑሮ ውድነቱ ግን እጅግ በጣም አሻቅቧል።

በኮሪደር ልማት ሰበብ  በብዙ ሺዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው የተለያየ አቤቱታ በተለያየ መገናኛ ብዙሃን ዜጎች እያሰሙ ነው በተለይ አዲስ አበባ ችግሩ በጣም የገዘፈ ነው።

በአጠቃላይ እነዚህን ችግሮች ስናይ ከሰላምና ፀጥታው ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።

ቅድሚያ የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ብንፈታው ሌሎች ችግሮችን አብረን እናስወግዳለን። እዛ ላይ ማተኮር አለብን።

🔵 መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው ፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም ? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው ?

🔵 ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው ?

🔵 የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር ፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው?

🔵 የኢኮሮሚ ችግሩን ለመፍታት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አለባቸው ያን ላለፉት በርካታ ዓመታት ማድረግ አልተቻለም ዜጎች በነጻነት እና በሰላም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ መንግስት የሚያስችለው መቼ ነው ? "

በተጠየቀው ጥያቄ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ምላሽ ተከታትለን እናቀርባለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
" ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት በቅርብ ማስተካከያ ይደረጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፓርላማ አባላት ለተነሱ የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው።

በዚሁ ወቅት በቅርቡ ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት ማስተካከያ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ባለፉት ጥቂት ወራት ከሪፎርሙ ጋር ተያይዞ ከወሰናቸው አብሮ ከማይሄዱ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ ፍራንኮ ቫሉታ ነው " ብለዋል።

" ያን የወሰነው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንዱ በውጭ ያለ ሃብት ከዚህ ቀደም የሸሸ ወደ ሀገር ውስጥ መምጣት የሚችል ከሆነ እድል ለመስጠት ፤ ሁለተኛ ባንኮቻችን አሁን በጀመርነው ኢኮኖሚክ ኦፕንአፕ በቂ ልምምድ እስኪያደርጉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች እንዳያንሱና የኑሮ ውድነት እንዳያባብሱ ጉዳት ቢኖረውም ከፈት እናድርግ የሚል እሳቤ ነበር " ሲሉ አስረድተዋል።

" ያየነው ውጤት ከዚህ በላይ መሸከም ተገቢ እንዳልሆነ የሚያሳይ ስለሆነ በቅርቡ ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት ማስተካከያ እንደሚደረግ ይጠበቃል " ብለዋል።

የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እየሰጡ ያሉት ማብራሪያ ያንብቡ : https://telegra.ph/PM-Office-10-31

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት በቅርብ ማስተካከያ ይደረጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፓርላማ አባላት ለተነሱ የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው። በዚሁ ወቅት በቅርቡ ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት ማስተካከያ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ባለፉት ጥቂት ወራት ከሪፎርሙ ጋር ተያይዞ ከወሰናቸው አብሮ ከማይሄዱ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ…
" ሪፎርሙ ባይሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርስ ነበር ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው።

በተለይም ከኢኮኖሚ ሪፎርሙ ጋር የተያዙ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል።

አንዱ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሚመለከት ነው።

" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ ሪፎርም በጣም ተጠቃሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ነው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፥ " በህዳሴ ምክንያት ፣ በቦንድ ምክንያት በጣም አስጊ ጉዳይ ውስጥ ከነበሩ ተቋማት አንዱ ንግድ ባንክ ነው " ብለዋል።

" ይሄ ሪፎርም ባይሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርስ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

" ባንኩ ያለበትን ዕዳ በቀላሉ ማኔጅ የሚያደርገው አልነበረም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " በዚህ ሪፎርም 900 ቢሊዮን ብር የተራዘመ ቦንድ አግኝቷል ባንኩ በከፍተኛ ደረጃ የነበረበትን ኢሚዴዬት አደጋ መከላከል የሚያስችል ሪሶርስ አግኝቶ ስራ ጀምሯል " ብለዋል።

" ንግድ ባንክ ወደቀ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ 30ውም ባንኮች ወደቁ ማለት ነው። ዋናው የኢትዮጵያ ባንክ ንግድ ባንክ ነው እሱን ማዳን የባንክ ሴክተሩን ማዳን ነው " ሲሉም አክለዋል።

" 900 ቢሊዮን ዶላር የተገኘበት መንገድ ብንነጋገር ብዙ አስደሳች ጉዳዮች ያሉበት ነው ግን አላነሳውም " ብለዋል።

ገንዘቡ የተገኘው ጠቃሚ በሆነ ድርድር እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምን አይነት ድርድር ይህ ሁሉ ገንዘብ እንደተገኘ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሪፎርሙ ባይሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርስ ነበር ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው። በተለይም ከኢኮኖሚ ሪፎርሙ ጋር የተያዙ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። አንዱ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሚመለከት ነው። " የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ ሪፎርም በጣም ተጠቃሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ነው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ…
" በባንክ ስም የሚዘርፉ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

" የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

እነዚህ አካላት " በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ብለዋል።

" ባንኮች ኮሚሽን ስለለመዱ፣ በትክክለኛው ህጋዊ መንገድ ከሚሰራው ይልቅ የትይዩ ማርኬት ውስጥ ተዋናይ መሆን ስለሚጠቅማቸው የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ ፤ እነዚህ በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ሲሉ ነው የተደመጡት።

እነዚህ ላይ ከፍተኛ ክትትል እና እርምጃም ይወሰዳል ሲሉ ተናግረዋል።

" ባንኮች ህግ እና ስርዓት አክብረው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገትን በሚያረጋግጥ መንገድ ሊሰሩ ይገባል እንጂ በባንክ ስም የአራጣ ስራ የሚሰሩ ከሆነ ችግር ነው " ብለዋል።

" ባንክ በህጋዊ መንገድ የሚወዳደሩበት እንጂ በህገወጥ መንገድ በኮሚሽን ሃብት የሚሰበስቡበት መሆን የለበትም " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በባንክ ስም የሚዘርፉ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) " የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። እነዚህ አካላት " በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ብለዋል። " ባንኮች ኮሚሽን ስለለመዱ፣ በትክክለኛው ህጋዊ መንገድ ከሚሰራው ይልቅ የትይዩ ማርኬት ውስጥ…
#ብላክማርኬት #ኤምባሲዎች

" ነገር እንዳናበላሽ ነው የታገስናቸው ስራቸው ብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በስም ያልጠቀሷቸው ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ጠቁመዋል።

" አንዳንድ ኤምባሲዎች ቀጥ ብለው የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ የሚሰሩ ኤምባሲዎች አሉ ስራቸው ይሄ የሆነ " ብለዋል።

" እነሱ ላይ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል የማይታረሙ ከሆነ እርምጃ ይወሰዳል። ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም እኛ የምንፈልገው ጤናማ ህጋዊ ስርዓት ያለውን መንገድ የሚከተል ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ያን ስራ (ብላክ ማርኬት) የሚሰሩ ነገር እንዳናበላሽ ብለን የታገስናቸው ስራቸው ግን የብላክ ማርኬት የማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " ሲሉ ተናገረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብላክ ማርኬት ላይ የተሰማሩትን ኤምባሲዎች ስማቸውን በግልጽ ከመናገር ተቆጠበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ብላክማርኬት #ኤምባሲዎች " ነገር እንዳናበላሽ ነው የታገስናቸው ስራቸው ብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በስም ያልጠቀሷቸው ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ጠቁመዋል። " አንዳንድ ኤምባሲዎች ቀጥ ብለው የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ የሚሰሩ…
#ብላክማርኬት #ፍራንኮቫሉታ

የተለያዩ ኩባንያዎች በኩባንያ ስም ፣ በፍራንኮ ቫሉታ ስም ፣ በወርቅ ንግድ ስም የኢትዮጵያን ገበያ የሚያዛቡ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

" ሹፌሮች ፣ ትናንሽ ስራ የሚሰሩ ሳይቀሩ የኢትዮጵያ ብላክ ማርኬት ዶላር ወደ አንዳንድ ሀገራት በባቡርና በቅጥቅጥ መኪና ይወጣል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከሀገር ወርቅ ይወጣል ፣ ዶላር ይወጣል ይሄን ዘረፋ መከላከል ያስፈልጋል። ህገወጥነት ፣ ኮንትሮባንድ ዘራፊዎች በውስጣችን ያሉ ሰዎች ተጨምረውበት የሚደረግ ማንኛውም ህግ ያልተከተለ ዘረፋ መከላከል አለብን " ብለዋል።

" አንዳንድ ሀገራት በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን መዝረፍ መብት እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ አሉ ኢትዮጵያ ግን ከብሔራዊ ጥቅሟ አንጻር ጥያቄ ስታነሳ እንደ ግስላ የሚሆኑ እኛን መዝረፍና የኛን ብሔራዊ ጥቅም አለማክበር ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

" ከእኛ መውሰድ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል " ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ሀገራት እነማን እንደሆኑ ግን በስም አልገለጹም።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ፍራንኮ ቫሉታ " እርማት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

" ፍራንኮ ቫሉታ አላማውን ስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሃብት ማሸሻ እየሆነ ስላለ ለሱ እርማት ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ፓርላማ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) የጠየቁት ምን ነበር ?

በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጹሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር፣እገታ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ።

በአማራ ክልል ያለው ችግር አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።

አማራ ክልል ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው፣ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች፣ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልልና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።

  ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞች፣አንቂዎች ለ2 ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።

አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ም/ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ አመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው።

መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው?

ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው?

የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው ?

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽ ምንድነው ?

🔵 ከኃይል ይልቅ ሰላም እጅግ በጣም አዋጭ ነው።

🔵 እኛ ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን።

🔵 ከልጅነት አንስቶ ክላሽ ተሸክመን ስለኖርን ጉዳቱ ይገባናል። ጦርነትን በወሬ ሳይሆን በተግባር እናውቀዋለንና አንፈልገውም። ብዙዎችን ቀጥፎብናል አንፈልገውም።

🔵 ህልም አለን በዚህ ሀገር የሚጨበጥ ለውጥ ለማምጣት ለዛ ሰላም ያስፈልጋል።

🔵 ' የሰላም አማራጭ አትመርጡም በግልጽ አታውጁም? ' ለተባለው በተደጋጋሚ ማወጃችንን እናተም ህዝቡም ያውቃል።

🔵 የሀገር ሽማግሌዎችን ልከን በእንብርክክ መመለሳቸውን እናተም እኛም እናውቃለን።

🔵 አሁንም ቢሆን በሰላም በኩል እርሶ (ዶ/ር አበባው) እኛንና የሚቃወሙትን ማቀራረብ ከቻሉ በሩ ክፍት ነው። የምንፈልገው ሰላም ነው። አነጋግረው ያምጧቸው።

🔵 በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጋር ንግግር አለ ግን ንግግር የሚያደርጉትን እና ሰላም የሚፈልጉትን ሰዎች ' እንዴት ትነጋገራለህ ከዚህ መንግስት ጋር? '  ብለው የሚወቅሱ ሰዎች አሉ። እዚህም አሉ፤ እዛም አሉ። በዚህም ምክንያት ሰላም ፈላጊዎቹ ደበቅ ይላሉ።

🔵 መጠየቅ ብቻ አይደለም ንግግርም ጀምረናል። ለቀረው እርስዎም (ዶ/ር አበባውን) ያግዙን።

🔵 የምንፈልገው ሰላም ነው። አንድ ወንድም ገለን ምን እናገኛለን ? በዚያ መንገድ ማንም እንደማያሸንፈን እናውቃለን። ምንም ! ስጋት ኖሮብን አይደለም። ግን መገዳደል ምን ፋይዳ አለው ? አይጠቅምም።

🔵 ' በ2 ወር እንቆጣጠራለን ብላችሁ ገብታችሁ ' የሚለው ምኑን እንቆጣጠራለን ክልሉን በህጋዊ መንገድ በምርጫ ያሸነፍንበት ክልል ነው። ምንድነው? ከማን ነው? የምንቆጣጠረው። በአንጻሩ ያልተሳካው " በሁለት ሳምንት ይሄን አረፋ መንግስት አባርሬ 4 ኪሎ የአባቶቼን ርዕስት እወርሳለሁ " ያለው አልተሳካለትም። እንጂ አማራ ክልል ክልላችን ነው የአማራ ህዝብ ህዝባችን ነው። ምንም የምንቆጣጠረው አብረን ነው የኖርነው አብረን ነው ያታገልነው አብረን እኖራለን። 2 ወር 3 ወር የሚል እቅድ ከኛ ሳይሆን እኛን በቀላሉ ለመገፍተር ካሰቡ ሰዎች የመጣ ነው።

🔵 የአማራ እስር፣ ጉዳት፣ ችግር  የሚለው የቁጫም ችግር ነው፣ የኦሮሞም ሲጠየቅ ችግር ነው ይሄ የሰፈሩን ብቻ የሚያስብ ኃይል ሁል ጊዜ እንደዛ ነው። የራሱን ብቻ ነው የሚያየው።

🔵 አማራን ባለፉት 6 ዓመታት የኢንዱስትሪ ማዕከል አድርገናታል። የማያምን ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ባህር ዳር፣ ቡሬ ሄዶ ይቁጠር። ጨርቃ ጨርቅ፣ ሲሚንቶ፣ ማርብል፣ ግራናይት የዘይት ፋብሪካ ብዙ ብር አግዘን አማራ ክልል አቋቁመናል።

🔵 አማራ ክልል የብልጽግና መንግስት የፈጠረውን ኢንዱስትሪ በየትኛውም መንግስት አግኝቶ አያውቅም። በወሬ ስለተደባበቅ እንዳትሸወዱ።

🔵 ሁሉም ባይሟላም በመንገድ ዘርፍ ብዙ ስራ ተሰርቷል።

🔵 ባህር ዳር እኛን ሳይመርጠን በስራ ማስመስከር ስላለብን በኢትዮጵያ ሰርተን የማናቀውን ድልድይ ሰርተናል፣ መንገድ እየሰራን ነው፣ ኮሪደር ልማት፣ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለው ባህር ዳር ነው። ህዝባችን ሰርቪሱ ይገባዋል ብለን ስለምናስብ።

🔵 ጎንደር ቢሄዱ ያን ስልጡን ህዝብና ሀገር  ከ70 እና 80 ዓመት በኃላ ዞር ብሎ የሚያየው መንግስት ያገኘው አሁን ነው። ፋሲል ቀንና ማታ እየተገነባ ነው፣ መስቀል አደባባይ የአዲስ አበባውን መስቀል አደባባይ በሚያክል መንገድ እየተገነባ ነው። ፓያሳ እያሸበረቀ ነው። መገጭን 18 ዓመት ከቆመ በኃላ 7 ቢሊዮን ብር መድበን ቀንና ማታ እየሰራን ነው።

🔵 ሃይቅን እየሰራን ነው፣ ጎርጎራን ሰርተናል።

🔵 ማዳበሪያ በከፍተኛ ሁኔታ በቀበሌው እያዳረስን ነው።

🔵 አማራ ክልል ልማት ነው እየሰራን ያለነው። እንደ ልብ እንዳንሰራ ግን የሚያደናቅፉን ሰዎች አሉ። እርሶ ያግዝኑንና ሰዎቹ ይመለሱ።

🔵 ፋሲልን የምንሰራው፣ ማዳበሪያ የምናዳርሰው በወታደራዊ እጀባ ነው። እንዴት ነው አሳሪ መንግስት የሚሆነው? ተቀናኛን የሚባለው ልማት የሚያደናቅፍ፣ ተማሪ የሚያደናቅፍ ነው።

🔵 ህዝቡ ማን እንደሚሰራ ማን እንደሚያወራ ያውቃል።

🔵 ሰላሙን እርሶም ጓደኞቾም ይሞክሩ፤ ይምጡ! ይመልሱ! ልማቱን ደግሞ ልክ እኛ ለምነን እንደምንሰራው (አዋሬ፣ ገበታ ለሀገር) እርሶም ፓርቲዎም ለምነው ተባብረን አማራን ወደ ልማት እናስገባው።

🔵 ጎርጎራን በወታደር ጠብቀን ነው የሰራነው ፣ ጎንደር ፒያሳን የምናድሰው ከኳሪ ሲሚንቶ ለማምጣት በወታደር አስጠብቀን ነው፤ ከየትኛው ወራሪ ሀገር ነው የምንጠብቀው ? ጎንደር እንዳይለማ፣ ባህር ዳር እንዳይለማ ፣ ወሎ እንዳይለማ የሚያደርገው የዚያው ሰፈር ሰው ነው።

🔵 አማራ ክልል እንዲቀየር እየሞከርን ነው።

🔵 ጋዜጠኛ አንቂ ለተባለው ጉዳይ አንድ እግር ሲኦል አንድ እግር ገነት አኑሮ መቀመጥ ሚቻል አይመስለኝም። ወይም የገነትን ፍሬ መብላት ወይም የሲኦልን እሳት መቅመስ ነው። አንዳንድ ሰዎች እዚህም ሰላም ውስጥ አሉ እዛም ጦርነት ውስጥ አሉ። የመረጃ ችግር ያለብን እንዳይመስላችሁ።

🔵 በጅምላ የፓርላማ አባላት፣ በጅምላ የፖለቲካ ሰዎችን የምናስር ከሆነ እርሶም ይታሰሩ ነበር። በጅምላ አይደለም በግብር ነው ሰው የሚታሰረው።

🔵 የግል ምርጫዬን ከጠየቁኝ እኔ ቢቀር ነው የምለው። ይቅር ተባብለን፣ ትተን፣ በደለኛ ካለ ክሰን በሰላም ሀገራችንን እናልማ። ከዚህም ይውጣ፣ ከዩኒቨርሲቲም ይውጣ ከከተማ እስር አይጠቅምም ግን መንግስት ነን፤ መኖሪያ ቤት እንገነባለን ማረሚያ ቤትም እንገነባለን።

🔵 "አሁንም ይናገሩ" ለተባለው ሁሌም በራችን ክፍት ነው። ሞከረናል የአማራ አካባቢ ሰዎችን አነጋግረናል፤ ሽማግሌ ልከናል። በአፍሪካ ህብረት፣ በኢጋድም ሙከራ ይደረጋል። እርሶም ቢያደርጉ በደስታ እንቀበላለን።

@tikvahethiopia
#RedSea

" ዓለም ዛሬ ይስማ የቀይ ባህር አክሰስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

🟢 " ወይ እኛ ወይም ልጆቻችን ይህንን ያሳኩታል "🟢

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)  ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ኢትዮጵያ የማይናወጥ ብሔራዊ ጥቅም አላት ዓለም ዛሬ ይስማ የቀይ ባህር አክሰስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል " ሲሉ በዛሬው ፓርላማ ላይ ተናግረዋል።

ይህንን ሲናገሩ የፓርላማ አባላት ዘለግ ያለ ከፍተኛ ጭብጨባ አሰምተዋል።

" በዚህ (ቀይ ባህር) ጉዳይ የምንደብቅ የሚመስለው ካለ ተሳስቷል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በጦርነት ፣ በኃይል አንፈልግም በቂ ሪሶርስ ነው በማንኛውም ህግ በማንኛውም የሀገር ልምምድ ኢትዮጵያ ይገባታል " ብለዋል።

" ብዙዎች እኮ ይላሉ 120 ሚሊዮን ህዝብ መቆለፍ ነውር ነው ይላሉ ፤ አንዳንድ የተገዙ ኢትዮጵያውያን ባይገባቸውም ወይ እኛ ወይ ልጆቻችን ያሳኩታል ፤ ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም እውነት ስለሆነና ሎጂካል ነገር ስለሆነ " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ይህንን አስታኮ ' ነገ ውጊያ ይነሳል ' ብለው የሚያስቡ ሰዎች አንዋጋም ከማንም ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ' ኢትዮጵያን ሊወሩ ይችላሉ ሀገራት ' የሚል ስጋት ያለባቸው ሰዎች አልፎ አልፎ ስለሚነሱ ኢትዮጵያን ማንም ሰው ዛሬ በኃይል መውረር አይችልም ማንም !! " ሲሉ ገልጸዋል።

" ለመመከት የሚያስችል በቂ አቅም አለን። ስንገዛ ስንሸምት የነበርናቸውን በውጊያ ክፍተት የገጠሙንን ነገሮች ማምረት ጀምረናል። እናመርታለን ፣ ሰው አለን ጀግኖች ነን ከነኩን ግን ለማንም አንመለሰም " ብለዋል።

ይህንን ሲናገሩም የፓርላማ አባላት በጭብጨባ አቋርጠዋቸው ነበር።

ኢትዮጵያ የወረራ ስጋት እንደሌለባት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በአጼ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት ብዙ አቅም ባልነበረበት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን አድዋ ላይ ሄደው አሸንፈው ነጻነት ማስከበር ከቻሉ ያኔ 5 ሚሊዮን ነበሩ ዛሬ 120 ሚሊዮን ነው የጀግንነት ደሙ እንዳለ ነው ስጋት አይግባችሁ ማንም ቢመጣ አሳፍረን እንመልሳለን እኛ ግን ማንንም አንነከም " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓም በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ ( ወመዘክር ) በተከናወነው “የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ” የአቦል አዳዲስ ተከታታይ ድራማዎች አዘጋጆች በመድረኩ ልምዳቸውንና የአቦልን አስተዋፅኦ ያጋሩ ሲሆን ይዘቶቻቸውንም አስተዋውቀዋል።

አንተህ ኃይሌ ስለ “የእሳት እራት” ቴሌኖቬላ፣ ኑር አክመል ስለ “አሻራ” ቴሌኖቬላ፣ ፌቨን ከተማ ስለ “የልቤ” ድራማ እንዲሁም ኡስማን አወል ስለ ማዲ አቦል ይዘቶች ገለፃ አድርገዋል።

የአቦል አዳዲስ ተከታታይ ድራማዎች አዘጋጆች በመድረኩ ልምዳቸውንና የአቦልን አስተዋፅኦ ያጋሩ ሲሆን ይዘቶቻቸውንም አስተዋውቀዋል።

አንተህ ኃይሌ ስለ “የእሳት እራት” ቴሌኖቬላ፣ ኑር አክመል ስለ “አሻራ” ቴሌኖቬላ፣ ፌቨን ከተማ ስለ “የልቤ” ድራማ እንዲሁም ኡስማን አወል ስለ ማዲ አቦል ይዘቶች ገለፃ አድርገዋል።

መርሃግብሩ አስተዋፅኦ ላደረጉና በአፋፍ የዝግጅት ሂደት ለተሳተፉ ባለሙያዎች የዕውቅና የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል።

#ሁሉምያለውእኛጋርነው
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ ካለፋት 2 ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር…
ዛሬም ድረስ አንዳንድ ተቋማት ኢ-ህገመንግስታዊ የሆኑ የአለባበስ (ድሬሲንግ) ኮዶችን በመጥቀስ ብዙ ሙስሊሞችን በትምህርት፣ በስራ ገበታ ላይ አስተዋፅኦ እንዳያደረጉ እንቅፋት እየሆኑ እንዳሉ የፓርላማ አባሉ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ተናግረዋል።

ይህንን ያሉት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ነው።

ዛሬ እንኳን አሉ ኡስታዝ " ዛሬ እንኳን እኛ እዚህ ቁጭ ብለን ተማሪዎች በኒቃባቸው በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ተገለው አንዳንድ አካባቢዎች እስከ ሁለት ዓመት ድረስ የሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ አይነት ድርጊት እጅግ ጎጂ መሆኑን በማንሳት መንግሥት መሰል ድርጊቶች እንዲታረሙ እንዲያደርግ የሚያስገነዝብ ሃሳብና ጥያቄ በይፋ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia