TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረቂቅአዋጅ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ረቂቁ ምን ይዟል ? 🔵 የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነትና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ። 🔵 የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት…
" የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ሳናሻሽል እንዴት አድርገን ነው የትምህርት ጥራትን የምናሳካው ? " - የፓርላማ አባል

አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ በትላንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ቀርቦ በምክር ቤት አባላት አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ለሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትኛ ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

በዋነኛነት በረቂቅ አዋጁ ላይ የምክር ቤት አባላት ምን አነሱ ?

አንዱ የተነሳው ከትምህርት ጥራት እንዲሁም ከመምህራን ጋር የተነሳ ነው።

ከሦስት በላይ የምክር ቤት አባላት የትምህርት ጥራት በቀጥታ ከመምህራን ጥራት ጋር አገናኝተው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በመምህራን የሚቀርቡ ጥያቄዎችንም አዋጁ የሚያስተናግድበት መንገድ እንዲፈጠር ነው የጠየቁት።

የምክር ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ሳናሻሽል እንዴት አድርገን ነው የትምህርት ጥራትን የምናሳካው ? ስለሚበላው ነገር የሚያስብ ፤ የት እንደሚያድር የሚያስብ መምህራንን ይዘን እንዴት ነው የምናሳካው ?

አሁንማ በሚገርም ሁኔታ ወሩን ጠብቆ ደሞዝ ስላልመጣ ሲያምጽ፣ ተቃውሞ ሲያሰማ የሚታሰርባቸው ክልሎች መኖሩን በተለያዩ ሜንስትሪም ሚዲያዎች የምንሰማበት ነውና የመምህራንን የትምህርት ጥራት ሳናሻሽል የትምህርት ጥራትን ማሳካት አንችልም።

ግብዓቶችን በጥቂቱ ሳናሟላ ውጤት መጠበቁ እንደማያዋጣ አያዋጣም።

ለትምህርት ጥራቱ ብዙ ነገሮች መታየት አለባቸው።

የሀገሪቷ የሥራ እድል ሁኔታ ምን ይመስላል ? ተማሪዎች ምንን አይተው ነው ተነቃቅተው የሚማሩት ወንድሞቻቸው እህቶቻቸው የት ደረጃ የተሻለ ኑሮ የሚኖሩትን አይተው ነው የሚማሩት ?

የሀገሪቷ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ፣ እንደዚህ አይነት በጣም ዘግናኝ የሆኑ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን እያዩስ በምን አይነት ተነሳሽነት አይተው ነው ተማሪዎች የሚማሩት ? እነዚህ ሁሉ ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው "
ብለዋል።

ሌላው በምክር ቤት አባላት የተነሳው ሀሳብ ቋንቋን በተመለከተ ነው።

በዚህ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት የምክር ቤቱ አባል ወ/ሮ አቡኔ ዓለም በተለይ ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ጋር በተያያዘ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና ማብቂያውን በክልሎች እንዲወሰን በረቂቅ አዋጁ መቀመጡ የብሔረሰብ አስተዳደሮችን መብት የሚጋፋ እንደሆነ አስረድተዋል።

ሌላኛዋ የምክር ቤት አባል ወ/ሮ ሲቲ ሬዲዋን ፥ የአፍ መፍቻ ቋንቋ በክልሎች መወሰኑ " የዚያ አከባቢ ሰው ከሌለ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሉ " ሲሉ ለክልሎች ኃላፊነቱ መሰጠቱን ተቃውመዋል።

" የወለኔ ህዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው የመማር እድል አላገኘም " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ ከአፍ ቋንቋቸው ውጪ " ከፌደራል የሥራ ቋንቋ አንድ መርጠው እንዲሰጡ " የሚለው አገላለጽ ህገመንግስታዊ መሰረት የሌለው ነው ተብሏል።

ይህንን ኃሳብ ያነሱት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ናቸው።

ምን አሉ ?

" ህገመንግስቱ ይሻሻል ችግር የለውም ዜጎች በቋንቋቸው የመማር መብታቸው ይከበር። በጣም የሚበረታታ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ህገ መንግስቱን ሳናሻሽል 5 የሥራ ቋንቋዎች ውስጥ ምረጡ ማለት አስቸጋሪ ነው። " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#መገናኛ

" የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ

ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ነው " መገናኛ " አካባቢ።

በዚህ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መሰራት ጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ባለው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ምን አሉ ?

" መገናኛ በጣም ብዙ ሰዎች ተሽከርካሪዎችም የሚገናኙበት በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ቀድም ብሎ የቀለበት መንገድ የሚባለው ስለነበር መንገዱ ለእግረኞች ማቋረጫ በቂ አልነበረም። በዚህም ህብረተሰቡ በርካታ ችግር እንዲያሳልፍ ሆኗል።

ይሄ ትልቅ ጎዳና እንደመሆኑ የሚሰራው እግረኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይቸገሩ በመሬት ውስጥ መሻገር የሚችሉበት ነው።

የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናልም ይገነባል በማዶ በኩል። በሙልጌታ ህንጻ ስርም ሁለት ወለል ያለው ተርሚናል ይገነባል።

እግረኞች ከአንዱ ተርሚናል ወደሌላኛው ተርሚናል የሚገናኙት በመሬት ውስጥ ይሆናል።

ከላይ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ በማይኖርበት ወይም በኒቀንስበት ሁኔታ ነው እየሰራን ያለነው።

ገንቢው ተቋራጭ ይህንን ስራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው ጊዜ 45 ቀን ነው።

ትንሽ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ለ45 ቀናት መንገዱን ስንዘጋው የነዋሪዎች እና የመኪና እንቅስቃሴ በተለይ መገናኛ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እንደመሆኑ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።

ዛሬ የምንወስነው ውሳኔ ምናልባት ለወደፊቱ ለበርከታ ረጅም አመታት ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል።

ለ45 ቀናት በ3 ሺፍት ነው የምንሰራው። ከዛም ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ከሚሰሩት ኮንትራክተሮች ጋር ተግባብተናል " ብለዋል።


የግንባታ ስራውን የሚያማክረው ማነው ? ስራውን የሚያማክረው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።

ኮርፖሬሽኑ " የመገናኛ እግረኛ መተለለፊያ ስራ በአይነቱ የተለየ እና ዘመናዊ ነው " ብሎታል።

ሱቆችን ጨምሮ የተለያዩ የፅዳት ቦታዎችም ይሰራሉ ብሏል።

" ፕሮጀክቱን በተባለው በ45 ቀናት እንደሚያልቅ እርግጠኞች ነን ፤ 24 ሰዓት ነው የሚሰራው  ፣ በቂ ማሽነሪ አለ፣ በተጓዳኝ ብረትና ሌሎች ዥግጅቶች እየተደረጉ ነው " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤኤምኤን ቲቪ መውሰዱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🙌🏼 ከሳፋሪኮም ወደ ቴሌ መደወል በደንብ ይቻላል ! እነዚህን የድምፅ ጥቅሎች እየተጠቀምን ከ07 ➡️ 09 መስመር እንደዋወል! ከአስተማማኙ ኔትወርክ ጋር አንድ ወደፊት⚡️
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ

ካለፋት 2 ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አሳውቋል።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ይህንን ያሳወቀው ለከተማው ትምህርት ቢሮ በላከው ደብዳቤ ነው።

" ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ የመጅሊስ መዋቅሮቻችን አመራር አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጥረት ተደርጓል " ብሏል።

" በዚህም መሰረት ከተወሰኑ ት/ት ቤቶች ጋር በተደረገ ስምምነት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ከውይይቱ ስምምነት በመውጣት ተማሪዎችን ማስክ እንኳ ቢሆን እድርገው እንዳይገቡ ተከልክለዋል " ሲል ም/ቤቱ ገልጿል።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች እነማን እንደሆኑ ግን በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

በጉዳዩ ላይ ሰሞኑን ከከተማው ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ እንደነበርም ምክር ቤቱ አስታውሷል።

" የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባወጣው የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ ስለመሆኑ ባደረግነው ውይይት ተማምነናል " ብሏል።

" ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ኃላፊነት በጎደላቸው አመራሮች ምክንያት ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ያላግባብ እንዲታገዱ መደረጉና የስነ-ልቦና ጫና መፈጠሩ የየትኛውም ህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት የሚደረግ ጥረት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል " ሲል አክሏል።

" ስለሆነም በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ተማሪዎቹም መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት #እንዲካካስላቸው " ሲል አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል።

ሰሞኑን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ምክንያት ችግሮች መከሰታቸው ፤ በዚህም ተማሪዎቹ ለ3 ሳምንታት ያህል ከትምህርት ገበታቸው እንደተስተጓጎሉ ተገልጿል።

እነዚህን ተማሪዎችን የሚወክሉ ከአዲስ ከተማ ት/ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳተፉበት በዛሬው ውይይት ላይ ፦

🟢 ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

🟢 በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችንና አለባበሳቸውን መነሻ በማድረግ እየተስተዋለ ያለው አግላይነትና ከትምህርት የማራቅ ተግባር ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

🟢 ዛሬ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ነገ ወደ ሌላ የእምነቱ የስርዓተ አምልኮ ላይ ተሸጋግሮ ችግር ይፈጥራል የሚል ስጋት ገብቶናል ያሉ ተማሪዎቹ የተነሳውን ችግር ከወዲሁ እንዲፈታ አሳስበዋል።

የምክር ቤት አመራሮቹ ምን አሉ ?

➡️  ምክር ቤቱ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

➡️ ሙስሊሙ በሚታወቅበት ሰላም ፈላጊነቱ ምክንያት እስካሁን የነበሩ ጉዳዮችን በሕግ አግባብ ማሳለፍ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተከሰተውን ችግር በተለመደው የሕግ አግባብ እልባት ለማስገኘት እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

➡️ ሰሞኑንም ሆነ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ ችግሮች መፍትሔ ያገኙ ዘንድ መላው ሙስሊም፣ ተማሪዎችና መሪው ተቋም መጅሊስ የተለመደ ሕጋዊ አካሄዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ከተማሪዎቹ ጋር በነበረው ውይይት የም/ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል ፤ የትምህርትና ስልጠና መመሪያ ዳይሬክተር ኡስታዝ ሀሰን አሕመድ እና የመምሪያው ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ በድር ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “ Best Overall in Africa award ” ሽልማት ማሸነፉን አሳውቋል።

አየር መንገዱ ፦
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣
🛫 በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት
🛫 በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

ይህ በ “ Airline Passenger Experience Association ” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

በአቪዬሽን ኢንደስትሪውም ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ እንደሆነ አየር መንገዱ ገልጿል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
🔈 #የሠራተኞችድምጽ

" 3 ወር ደሞዝ አልተከፈለንም " ያሉ የፐርፐዝ ብላክ ሠራተኞች የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ያሉበት የከፋ ችግር ታይቶ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ሠራተኞቹ ምን አሉ ?

" እኛ በፐርፐዝ ብላክ ኢታኤች የምንሰራ ሠረተኞች ደሞዝ ስላልተከፈለን ለከፋ ችግር ተዳርገናል።

በፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች የምንሰራ ሰራተኞች ደሞዝ ለ3 ወር ባለመከፈሉ ምክንያት ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተደማምሮ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀናል።

ከዛሬ ነገ ይከፈለናል በሚል ተስፋ የቆየን ቢሆንም እስካሁን በህግ ተይዟል ከሚል ጥቅል ምላሽ ውጪ  ይህ ነው የሚባል መረጃ እንኳን ማግኘት አልቻልንም።

ከእለት ወደእለት ወዳለመኖር እየተሸጋገርን ነው ፤ አልፎ ለከፍተኛ ማሕበራዊ ቀውሶች እየተዳረግን ነው።

አብዛኛው ሠራተኛ ቤት ተከራይቶ ስለሆነ የሚኖረው  የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶታል ቤተሰብ እየተበተነ ነው፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ አልቻሉም።

እነዚ የጠቀስናቸው ችግሮች ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው የሚመለከተው አካል ያለንበትን ችግር አይቶ አፋጣኝ ምላሽ ቢሰጠን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል። ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል። " የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ  ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ…
List of Names.pdf
4.8 MB
" የተሰጠው ማብራሪያ ከእውነት የራቀ ነው " - የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች

ሰሞኑን ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ዝርዝር ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ማብራሪያው ፥ " ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች  በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ነበር ያለው።

ዝርዝር ማብራሪያው በዚህም ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/91710?single

ማብራሪያውን የተመለከቱ ቆጣቢዎች ግን ማብራሪያ " ከእውነት የራቀ ነው " ሲሉ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

" እኛ የ1997 ነባር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት አክቲቭ ተመዝጋቢዎች ሰሞኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሰጠው መግለጫ ከእውነታ የራቀ ነው ስንል አንገልፃለን " ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት።

" እኛ የ1997 አክቲቭ ቆጣቢዎች የሆንን በ14ኛው ዙር 25 ሺህ ለእጣው አክቲቭ ናቸው ተብለን ለ18,650  ቤቶች ተወዳድረን እጣው ያልወጣልን ወደ 8,000 የምንሆን የተረፍን አክቲቭ ቆጣቢዎች መሆናችን ቢሮው በደንብ ያውቃል ሰነዳችንም በግልፅ በቤቶች ኤጀንሲም ሆነ በንግድ ባንክ አለ " ብለዋል።

" ቢሮው ' ብቁ እና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል ' ማለቱ እጅግ ግራ የሚያጋባ ነው የሆነብን " ሲሉም አክለዋል።

አሉን ያሏቸውን ዶክመንቶችንም የላኩ ሲሆን ከላይ ተያይዟል።

ጉዳያቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም እንደያዘው አስታውሰው ተቋሙ መፍትሄ እስኪያገኙ ድረስ እንዲገፋበት ጥሪ አቅርበዋል።

ዜጎቹ " አሁንም ድምፃችን ይሰማ ፤ መፍትሄ ይሰጠን " ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መገናኛ " የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት…
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለው የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም በተለይ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ ፤ ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን ተገልጿል።

እግረኞች በሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ በኩል ማለፍ ስለማይቻል በቦሌ ክ/ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ ተጠይቋል።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

#የአዲስአበባትራፊክማኔጅመንትባለስልጣን

@tikvahethiopia
#HopR

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል።

አሁን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄዎቹ ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

@tikvahethiopia