TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ

ካለፋት 2 ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አሳውቋል።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ይህንን ያሳወቀው ለከተማው ትምህርት ቢሮ በላከው ደብዳቤ ነው።

" ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ የመጅሊስ መዋቅሮቻችን አመራር አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጥረት ተደርጓል " ብሏል።

" በዚህም መሰረት ከተወሰኑ ት/ት ቤቶች ጋር በተደረገ ስምምነት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ከውይይቱ ስምምነት በመውጣት ተማሪዎችን ማስክ እንኳ ቢሆን እድርገው እንዳይገቡ ተከልክለዋል " ሲል ም/ቤቱ ገልጿል።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች እነማን እንደሆኑ ግን በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

በጉዳዩ ላይ ሰሞኑን ከከተማው ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲያደርግ እንደነበርም ምክር ቤቱ አስታውሷል።

" የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባወጣው የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ ስለመሆኑ ባደረግነው ውይይት ተማምነናል " ብሏል።

" ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ኃላፊነት በጎደላቸው አመራሮች ምክንያት ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ያላግባብ እንዲታገዱ መደረጉና የስነ-ልቦና ጫና መፈጠሩ የየትኛውም ህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት የሚደረግ ጥረት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል " ሲል አክሏል።

" ስለሆነም በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ተማሪዎቹም መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት #እንዲካካስላቸው " ሲል አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል።

ሰሞኑን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ምክንያት ችግሮች መከሰታቸው ፤ በዚህም ተማሪዎቹ ለ3 ሳምንታት ያህል ከትምህርት ገበታቸው እንደተስተጓጎሉ ተገልጿል።

እነዚህን ተማሪዎችን የሚወክሉ ከአዲስ ከተማ ት/ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳተፉበት በዛሬው ውይይት ላይ ፦

🟢 ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

🟢 በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችንና አለባበሳቸውን መነሻ በማድረግ እየተስተዋለ ያለው አግላይነትና ከትምህርት የማራቅ ተግባር ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

🟢 ዛሬ ከአለባበስ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ ነገ ወደ ሌላ የእምነቱ የስርዓተ አምልኮ ላይ ተሸጋግሮ ችግር ይፈጥራል የሚል ስጋት ገብቶናል ያሉ ተማሪዎቹ የተነሳውን ችግር ከወዲሁ እንዲፈታ አሳስበዋል።

የምክር ቤት አመራሮቹ ምን አሉ ?

➡️  ምክር ቤቱ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

➡️ ሙስሊሙ በሚታወቅበት ሰላም ፈላጊነቱ ምክንያት እስካሁን የነበሩ ጉዳዮችን በሕግ አግባብ ማሳለፍ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተከሰተውን ችግር በተለመደው የሕግ አግባብ እልባት ለማስገኘት እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

➡️ ሰሞኑንም ሆነ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ ችግሮች መፍትሔ ያገኙ ዘንድ መላው ሙስሊም፣ ተማሪዎችና መሪው ተቋም መጅሊስ የተለመደ ሕጋዊ አካሄዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ከተማሪዎቹ ጋር በነበረው ውይይት የም/ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል ፤ የትምህርትና ስልጠና መመሪያ ዳይሬክተር ኡስታዝ ሀሰን አሕመድ እና የመምሪያው ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ በድር ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopia