TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ📈 የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምሥራቃዊ ዩክሬን ላይ “ወታደራዊ ዘመቻ” መጀመሩን መግለጻቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቢቢሲ ዘግቧል። በዚህም ሳቢያ በ7 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። ውጥረት እና ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ከዚህም በላይ…
የሩስያ እና ዩክሬን ፍጥጫ #እንደኛ ባሉ አዳጊ ሀገራት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅእኖ ምንድነው ?

[በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የቀረበ]

- #የምግብ_ዋጋ_መናር : ኢትዮጵያ ስንዴ የምትገዛባቸው ሶስት ዋና ዋና ሀገራት ሩስያ፣ ዩክሬን እና አውስትራሊያ ናቸው። በተለይ ሩስያ እና ዩክሬን በአለም ላይ ካለው የስንዴ ገበያ አንድ አራተኛውን ይሸፍናሉ። ዩክሬን 40 % የሚሆነውን የስንዴ ምርቷን ለመካከለኛው ምስራቅ እና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አዳጊ ሀገራት በሽያጭ ታቀርባለች። ታድያ ይህ አቅርቦት በጦርነት ምክንያት ሲስተጓጎል የምርት/ምግብ አቅርቦት መስተጓጎሉ አይቀርም። ይህም በአንዳንድ ሀገራት የሚታየውን የዋጋ ግሽበት አባብሶ ህዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል።

- #የነዳጅ_ዋጋ_መጨመር : የሩስያ እና ዩክሬንን ፍጥጫ ተከትሎ አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ እንዳሻቀበ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፣ ይህ ዋጋ ከዚህም በላይ በፍጥነት ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አለ። ሩስያ በአለም ላይ የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ በማምረት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙ ሀገራት መሀል ትመደባለች። ታድያ ይህ ግጭት የአለም የነዳጅ ዋጋን እጅጉን እያናረው ይገኛል፣ ይህም በተለይ እንደ ሀገራችን ላሉ ነዳጅ ገዢ ሀገራት እጅጉን ፈታኝ ግዜ እንደሚያመጣ ግልፅ እየሆነ ነው።

- #የእርዳታ_መቀነስ : ብዙ ግዜ እንደሚታየው አንድ ቦታ ላይ ትልቅ ችግር ሲከሰት ትኩረት ወደዛ ይዞራል። ለምሳሌ በሶርያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተ ችግሮች ሲከሰቱ ከረጂ ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እዚህም፣ እዛም ይከፋፈል እና ይቀንሳል። አሁን ደግሞ ሀገራችን በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ከፍተኛ አለም አቀፍ ድጋፍ የምትሻበት ግዜ ነው፣ ነገር ግን ይህ እየተባባሰ የመጣ ፍጥጫ ትኩረት እንዳያሳጣን ስጋት አለ።

@tikvahethiopia
#የነዳጅ_ዋጋ !

አሁን በዓለም ገበያ 1 በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ 106.6 ዶላር እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት አንድ በርሜል ነዳጅ 104.3 ዶላር በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።

#OilPrice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሚያዚያ የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፥ የሚያዚያ ወር የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ላይ ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል አስታውቋል። የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ እና የቀላል ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የመጣው ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ኤፍ ቢ…
#የነዳጅ_ዋጋ_ጭማሪ

ከነገ ሚያዚያ 30 ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

በዚህም ፦

👉 ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ፣
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
👉 ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም
👉 የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 78 ብር ከ87 ሳንቲም እንዲሆን መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዝርዝሩን ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-05-07

@tikvahethiopia
#የWFP_ማጠንቀቂያ

የተመድ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ዓለም፥ የጅምላ ስደትን፣ መረጋጋት የጎደላቸውን ሀገራት እና በረኀብ የተጠቁ ሕፃናትንና አዋቂዎችን ማየት እንደሚጀምር አስጠንቅቋል።

የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቤስሊ ባለፈው ዐርብ  ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር።

ቤስሊ ምን አሉ ?

- ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ #በቢሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ በሚቀጥሉት ከ12 እስከ 18 ወራት ውስጥ ዓለም፥ የጅምላ ስደትን፣ መረጋጋት የጎደላቸውን ሀገራት እና በረሃብ የተጠቁ ሕፃናትንና አዋቂዎችን ማየት ይጀምራል።

- ባለፈው ዓመት፣ ከአሜሪካና ከጀርመን የተገኘውን ተጨማሪ ድጋፍ ይደነቃል ፤ ቻይና፣ የባሕረ ሠላጤው ሀገራት፣ ቢሊየነር ባዕለ ጸጋዎች እና ሌሎችም ሀገራት፣ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ድጋፋቸውን ሊያፋጥኑ ይገባል።

- በ49 ሀገራት ውስጥ አስቸኳይ የሆነ #የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 350 ሚሊዮን ሰዎች ለመርዳት 23 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ይህ ገንዘብ ላያገኝ ይችላል ፤ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ኹኔታ አስጨንቆኛል።

- አሜሪካ የምትሰጠውን የገንዘብ ርዳታ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 7.4 ቢሊዮን አሳድጋለች፤ በተመሳሳይ ጀርመንም ከ350 ሚሊየን ዶላር ወደ 1.7 ቢሊዮን ከፍ አድርጋለች ፤ በዓለም ሁለተኛ ትልቁ የሆነውን ኢኮኖሚ የያዘችው ቻይና ባለፈው ዓመት ለተቋሙ የሰጠችው ገንዘብ 11 ሚሊየን ዶላር ብቻ በመሆኑ ድጋፏን ልታሳድግ ይገባል።

- #የነዳጅ_ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩ ጋራ ተያይዞ የባሕረ ሠላጤው ሀገራት የበለጠ እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ። በተለይ ከምሥራቅ አፍሪካ፣ ከሰሐራ እና ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ጋራ ግንኙነት ያላቸው የሙስሊም ሀገራት የተሻለ አስተዋፅኦ ማድረግ ይችላሉ።

- ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው በአፍሪካ የሳሕል ክልል የሚገኙ ሀገራትና ምሥራቅ ሶማሊያ ፣ ሰሜናዊ ኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣  #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ይገኙባቸዋል።

- የዓለም መሪዎች፣ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋትን ሊያስከትሉ የሚችሉ የሰብአዊ ርዳታ ክፍተቶች ለአሉባቸው ሀገራት ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል።

ዴቪድ ቤስሊ በዓለም ትልቁ ሰብአዊ ርዳታ ሰጪ በሆነው ተቋም የነበራቸውን ሥልጣን በመጪው ሳምንት ለአሜሪካ አምባሳደር ሲንዲ ማኬይን ያስረክባሉ።

#VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሩስያ ሩስያ ላልተወሰነ ጊዜ ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ወደ ውጭ መላክ አቆመች ፤ ይህ ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ይኖራል ተብሎ ተሰግቷል። ሩስያ ፤ " የሀገር ውስጥ ገበያን ለማረጋጋት እንዲሁም የሀገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎትን ለማሻሻል " በሚል ከአራት የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት አባላት ውጭ ወደ #ሁሉም_ሀገራት የነዳጅ ምርቶችን ቤንዚን እና ናፍጣ መላክን ለጊዜው አግዳለች። እገዳው…
#የነዳጅ_ዋጋ !

በዓለም ገበያ 1 በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ3 ወራት በፊት 74 የአሜሪካ ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 94.8 የአሜሪካ ዶላር ገብቷል።

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ ይገኛል። ትላንት 97 ዶላር ደርሶም ነበር። ይህም እኤአ ከህዳር 2022 ወዲህ ከፍተኛው ጭማሪ ሆኖ ተመዝግቧል።

የዚህ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ #ምክንያት የፍላጎት መጨመር እና የድፍድፍ ዘይት አቅርቦቶች በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ነው ተብሏል።

ለአቅርቦት መቀነሱና ለዋጋ ንረቱ ደግሞ የ " OPEC+ " አባላት የሆኑት ሳዑዲ አረቢያና ሩስያ ከዚህ ቀደም ያሳለፏቸው ውሳኔዎች ትልቁን ድርሻ ይይዛል ተብሏል።

በርካታ በዘርፉ ላይ ያሉ ተንታኞች ዋጋው በቅርብ ጊዜ ከ100 ዶላር በላይ ሊደርስ እንደሚችል እየገለፁ ናቸው።

@tikvahethiopia