TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalBankofEthiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት የባንክ ስራን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 5 መመሪያዎችን እንዳሻሻለ አሳውቋል። እነዚህ መመሪያዎች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የተመደቡ ናቸው። በመጀመሪያው ምድብ የሚካተቱት ፦ - “ የብድር ተጋላጭነት ጣሪያ ስለመወሰን”፤ - “ከባንኩ ጋር ዝምድና/ግንኙነት ባላቸው ወገኖች አማካኝነት ስለሚኖር የብድር ተጋላጭነት” - “ስለንብረት…
#NBE #Ethiopia

የብሔራዊ ባንክ የሕግ ማሻሻያ ፦

ከባንክ ጋር #ተዛማጅነት_ላላቸው_አካላት የሚሰጥ የብድር ተጋላጭነት ገደብ መመሪያ ላይ የሕግ ማሻሻያ ተደርጓል።

የዚህ መመሪያ ዓላማ አንድ ባንክ ተዛማጅነት ካላቸው አካላት ጋር በሚያደርገው ግንኑነት ብድር አግባብነት በሌለው መንገድ እንዳይሰጥ ለማድረግ ፣ የጥቅም ግጭት ለመቀነስ እንዲሁም ደግሞ ተዛማጅነት ካላቸው አካላት ጋር ባንኮች የሚያደርጉትን ማንኛውም ግብይት በተመለከተ በቂ የሆነ ክትትል ለማድረግ እና ያለ አድልዎ በተገቢው መንገድ የተሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።

ይህ መመሪያ በዋነኛነት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን #ገደቦች_ጥሏል

ሀ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከባንክ ጋር ተዛማጅነት ላላቸው አካላት በማንኛውም ጊዜ የሚኖረው አጠቃላይ የብድር ተጋላጭነት ከባንኩ ጠቅላላ ከፒታል ከ15% እንዳይበልጥ፤

ለ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከባንክ ጋር ተዛማጅነት ላላቸው አካላት በሙሉ በማንኛውም ጊዜ የሚኖር አጠቃላይ የብድር ተጋላጭነት ከባንክ ጠቅላላ ካፒታል ከ35% እንዳይበልጥ፤

ሐ) አንድ ባንክ ተዛማጅ ከሆኑ ወገኖች ጋር ግብይት ሲፈጽም ከማናቸውም ተዛማጅ ካልሆኑ ወገኖች ጋር ግብይት ሲፈጽም ተግባራዊ በሚደረግ ሁኔታዎች ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልክ እንዲሆን እና ከዚህ በተለየ ሁኔታ እንዳይፈጸም ይደነግጋል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/88218?single

#የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ባንክ

@tikvahethiopia
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE

@tikavhethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) #NBE @tikavhethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦

" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility) ይስጣል፡፡

እነዚህ የአንድ ቀን የብድር ወይም የተቀማጭ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ምክንያት ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ፍሰት አቋማቸውን ለማስተካከል እንዲረዳቸው ነው፡፡

እነዚህ ቋሚ አገልግሎቶች የሚሰጡት ከብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን 3 በመቶ በማስበለጥ ወይም በማሳነስ ይሆናል፡፡ "

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል። (ሙሉ መግላጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ

ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል።

ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም ባንክ (WB) እና ከአበዳሪዎች የሚገኘውን እንደሚጨምር አመልክቷል።

ነገር ግን፣ በሁለትዮሽ የማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ (central bank deposits) እና በከረንሲ ልውውጥ (currency swap) መልክ የሚመጣውን 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና ከሌሎች ባለብዙ ወገኖች (multilaterals) ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀውንና በሃደት ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ የሚደረገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አያካትትም ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ " በዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የሚለገሰው ልዩ የገንዘብ እርዳታ የመንግሥትን የሪፎርም ሥራዎችን ጥንካሬ ያገናዘበና በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ከሚባሉት የገንዘብ እርዳታዎች አንዱ ነው " ብሎታል።

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
FXD012024-FOREIGN-EXCHANGE-1-1.pdf
22.8 MB
NATIONAL BANK OF ETHIOPIA FOREIGN EXCHANGE DIRECTIVE NO. FXD/01/2024

በዚህ መመሪያ መሰረት የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚችሉት እነማን ናቸው ?

➡️ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።

➡️ ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

➡️ ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።

በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።

➡️ ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።

➡️ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።

➡️ ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።

ተጨማሪ ከላይ ተያያዘውን ፋይል ከፍተው ያንብቡ !

#NBE #BBC #Ethiopia

@tikvahethiopia
#NBE

ብሔራዊ ባንክ ወርቅን ከአምራቾች እና አቅራቢዎች በብቸኝነት ይገዛል።

ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ በዉጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ላይ ለዉጥ በማድረግ በገበያ የሚመራ የፖሊሲ ማእቀፍን ስለሚከተል ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የእለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኮች ይፋ ከሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ ዋጋ ውጭ የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን እና ሌላ ክፍያ እንዲያቆሙ ወስኗል።

እንዲህ ያሉ ክፍያዎችን ካስከፈሉ እንኳን ከመግዣና መሸጫ ዋጋው ጋር አካተው አንድ ላይ ለደንበኞቻቸው ይፋ እንዲያደርጉት ተብሏል።

ይህም የውጭ ምንዛሬ ግዥና ሽያጭ ላይ ግልፅነትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ግን ይህ አሰራር ደንበኞች ከውጭ ሀገር ግዢ ለመፈፀም LC ለመክፈት ሲጠይቁ የሚኖረውን ግብይት አይመለከትም ተብሏል፡፡

ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ በስራ ላይ መዋል መጀመሩንም ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

#ShegerFMRADIO #NBE

@tikvahethiopia
#NBE

ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ እንደሆነ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

ይኸው ልዩ ጨረታ የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች ነው።

ጨረታው ነገ ነው የሚካሄደው።

ፍላጎትት ያላቸው ባንኮች እንዲያመለክቱ ጥሪ ቀርቧል።

እንደ ገበያው ሁኔታ ደግሞ በመጪዎቹ ሳምንታት ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊወጣ እንደሚችል አሳውቋል።

(ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የውጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን የብሔራዊ ባንክ አሳውቋል። ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የውጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አውጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል። የውጪ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን…
#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጠ።

የስራ ፍቃድ የተሰጣቸው ፦

1. Dugda Fidelity Investment PLC
2. Ethio Independent Foreign Exchange Bureau
3. Global Independent Foreign Exchange Bureau
4. Robust Independent Foreign Exchange Bureau
5. Yoga Forex Bureau ናቸው።

" እነዚህ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው " ናቸው ያለው ብሔራዊ ባንክ " የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ለማስፋፋትና ለማዳበር የሚረዳ ሚና ይኖራቸዋል " ብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎቹ በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዥ ወዲያውኑ የሚፈጸም (spot transaction) ብቻ ይሆናል ተብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለ ጉምሩክ ዴክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡

እንዲሁም ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይችላሉ፡፡

@tikvahethiopia
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።

ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

አሁንም ቢሆን ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ መንገድ መተመናቸውን እና ይህንኑ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁሟል።

ባንኩ እስካሁን በነበረው አሰራር ንግድ ባንኮች ከውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቁትን ኮሚሽን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር ጠቅሶ፤ ወደፊት ግን ኮሚሽኑን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁ አስታውቋል።

#NBE

@tikvahethiopia
#NBE : ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ግብይት ይፋ አድርጓል።

ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ ማለትም ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት መቆየት የሚችል ገንዘብ መበደርና ማበደር የሚችሉ መሆናቸውንም አብስሯል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት መጀመሩ ፦

➡️ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ ግብይቱ የአጭር ጊዜ ማለትም የአንድ ቀን ወይንም የሰባት ቀናት የመክፈያ ጊዜ ያላቸው ብድሮችን ያካትታል ፤ ይህ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ እጥረት ስጋትን በመቀነስና በተረጋጋ የወለድ ተመን ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲል ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንዲሆ ብሔራዊ ባንክ ፈቅዷል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE

@tikvahethiopia
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ እንዳነሳ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።

የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል ተብሏል።

መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።

የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ፥ የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ መሆኑ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia