TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትኩረት‼️

የፌደራሉ መንግሥት #አጣዬ አካባቢ የተፈጣረው ችግር ሳይባባሥ #አስቸካይ መፍትሄ እንዲፈልግ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሠብ አባላት ጠይቀዋል።

ከአጣዬ••••

ለሰላም ሚኒስቴር
50 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...

#በከሚሴ እና #አጣዬ አካባቢዎች ከወራት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት በወንጀል የተጠረጠሩ 50 ሰዎች ከሕገ-ወጥ መሳሪዎች ጋር መያዛቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ከኮሚሽኑ እና ከሕግ አካላት የተውጣጣ የመርማሪ ቡድን ተዋቅሮ ጉዳዩን ከቦታው ሲያጣራ መቆየቱንም የኮሚሽኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር #ሰይድ_አህመድ ተናግረዋል፡፡

የምርመራ ቡድኑ በአጣራው መሠረትም በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች የተደራጀ ወንጀል ሲፈፅሙ ቆይተዋል ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

የምርመራ ቡድኑ በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ጨምሮ ሌሎችንም በቁጥጥር ስር አውሎ ለሕግ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በተጠቀሱት አካባቢዎች ከወራት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት ከ4 ዓመት ህጻን እስከ 94 ዓመት አዛውንት ህይዎት ማለፉንም ረዳት ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል፡፡

በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ወንጀል የፈፀሙ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አጣዬ

አጣዬ ዳግም ሰላም ርቋታል፤ የአጣዬ ቲክቫህ አባላት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ዳግም በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ሰዎች ሞተዋል ፣ ንብረት ተቃጥሏል፣ ሰዎች ሰላምን ፍለጋ ከገዛ ቤታቸውን ተፈናቅለው ሸሽተዋል።

ረቡዕ በአጣዬ ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ ከአምስት ሰዓት ጀምሮ የተኩስ እሩምታ የነበረ ሲሆን በሰዓት መከላከያ እና ፌዴራል ሁኔታውን መቆጣጠር ችለው ነበር።

አንድ የቲክቫህ አባል በአጣዬ ባለው ሁኔታ ሁለት በቅርብ የሚያውቃቸው ሰዎች መሞታቸውን ቢያረጋግጥም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር በትክክል እንኳን እንደማይታውቀ ተናግሯል።

ሌላ የቲክቫህ አባል ፥ በቅድሚያ ወደዳር አካባቢ የነበረው የተኩስ እሩምታ ወደ መሃል ክፍልም ይሰማ እንደነበረ ተናግሮ በአካባቢው የሚኖሩ ቤተሰቦቹ ሰላምን ፍለጋ ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል።

የፀጥታ ኃይሎች ያሉ ቢሆንም፥ በቂ አይደለም በታጠቁ ኃይሎች የሚፈፀመው ጥቃት / የሚሰማው ተኩስ በርካቶችን በደህንነት ስጋት ውስጥ ከቷቸውን ቤታቸው ለቀው እየሸሹ ናቸው።

በተጨማሪ በአንጻኪያ ወረዳ ውስጥ ባሉቱ የተለያዩ ቀበሌዎች ዳግም ግጭት ተቀስቅሶ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል።

በእነዚህ አካባቢዎች በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ዋናው ዳግም መንገድ ተዘግቷል፤ወደ እና ከ አ/አ መሄድ አይቻልም መኪናዎችም ሸዋሮቢት ላይ ቆመዋል።

የሸዋሮቢት ቲክቫህ አባላት እንዴት ናችሁ ብለን ጠይቀናቸው ነበር?

ዛሬ በሸዋሮቢት ሁሉም መደበኛ እንቅስቃሴ መቀጠሉን አረጋግጠውልን፤ አጣዬ ላይ የተፈፀምጠረውን ሁኔታ ግን እንደሰሙት ገልፀዋል።

የአካባቢው አስተዳደር የጸጥታ ኃይል ችግር ቢፈጠር እንኳን ለመጠበቅና ለመከላከል ቦታ መያዙን፤ ምንም የሚያሳስብ ነገር እንደሌለ መግለፁን ነገርውናል።

ከሀሰተኛ መረጃና ውዥንብር ማህበረሰቡ እንዲቆጠብ ጥሪ መቅሩብን ነግረውናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አጣዬ

“ የሰው ሕይወት በእነርሱም በእኛም ጠፍቷል። የሟቾች ቁጥር እንደ አጣዬ ከተማ ወደ 10 ደርሷል። በጣም በርካታ ቁስለኞች አሉ ” - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን በታጣቂዎች መካከል ተከፈተ የተባለው የተኩስ ልውውጥ ከሰሞኑ ይልቅ ዛሬ (ሰኞ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም) አንፃራዊ #ሰላም እንዳሳዬ፣ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ግን በሁለቱም ወገኖች የንጹሐን ሕይወት እንዳለፈ የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰላሙ ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፣ የተኩሱ ሂደት ምን ይመስል እንደነበር፣ የጉዳት መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለከንቲባው ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ ተመስገን ተስፋ፦

“ ተኩሱ ሁለት ቀናት በዙሪያው ሲካሄድ ቆይቷል። ወደ ከተማው ከገባ በኋላ ደግሞ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ውጊያው ተካሂዷል።

መከላከያ ገብቶ ከቆመ በኋላም ተራራ ላይ በመሆን በመተኮሱ የተገደሉ ንጹሐን አሉ። የሰው ሕይወት በእነርሱም በእኛም ጠፍቷል። በጠቅል የሟቾች ቁጥር እንደ አጣዬ ከተማ ወደ 10 አካባቢ ደርሷል። ቁጥራቸው ባይታወቅም እጅግ በጣም በርካታ ቁስለኞች ናቸው ያሉት።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን በኩል “ ፋኖ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱብን ” በአማራ ክልል በኩል ደግሞ “ የሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱብን ” የሚሉ ሀሳቦችን ነዋሪዎቹ በየፊናቸው እየገለጹ ይገኛሉ። እንደተባለው “ የፋኖ ታጣቂዎች ” ም ሆኑ የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ጥቃት አድራሿቹ ? እውነታው ምንድን ነው? ሲል ጠይቋል።

አቶ ተመስገን ተስፋ፦

“ በከተማችን ላይ የፋኖ ታጣቂ የለም። ከእነርሱም ጋር ግጭት አልፈጠረም። ምናልባት የፋኖ ታጣቂ የሚባለው ችግሩ ከመንግሥት ጋር ነው። መንግሥትን ካልሆነ በስተቀር የኦሮሚያን ብሔር በዚህ ቦታ ሂዶ ተጋጨ የሚል እንደ ከተማችን የለም። ችግሩ የተፈጠረው በእኛ በከተማው ታጣቂዎችና በእነርሱ መካከል ነው።

ዞሮ ዞሮ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች በአንድ ገበያ የሚገበያዩ፣ ተስማምተው የሚኖሩ፣ በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ ስለሆኑ፣ አማርኛ ተናጋሪው ኦሮሞው ላይ፣ ኦሮምኛ ተናጋሪውም እንደ ህዝብ ጥቃት ያደርሳል፣ ፈልጎ ይዋጋል ብለን አናስብም።

ልዩ የሆነ ቡድን፣ ፀቡ እንዲነሳ የሚፈልግ (ምናልባት ደግሞ ከዚያ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችል) ቡድን አለ። እሱም ደግሞ ኦረምኛ ተናጋሪ ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው ‘ሸኔ’ ነው።

ስለዚህ የእኛ ፍረጃ አሁን የኦሮሞ ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ወጋው ሳይሆን፣ የኦሮሞ ‘ሸኔ’ አማርኛ ተናጋሪውን በከተማው ላይ መጥቶ ወግቷል የሚል ግምገማ ነው ያለን።

Q. ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንዲቻል መንስኤውን ማወቅ ያስፈልጋልና የሰሞኑ ተኩስ መነሻው ምን ነበር ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ ተመስገን ተስፋ፦

“ እንደ አጠዬ ከተማ ነዋሪ፣ እንደ ከተማ አመራር መነሻው ይሄ ነው የሚል ነገር የለም። ግጭቶቹ የተካሄዱት በወሰን ብቻ ሳይሆን በከተማው መሀል ላይ ነው። ድንገት ገቡ ተወረረ ከተማው።

ከንጹሐን ሞት በተጨማሪ ሆቴሎች፣ ሱቆች ተዘርፈዋል። አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ህፃናት ከከተማ ወጥተው ወደ ገጠራማው ክፍል ተፈናቅውለዋል። አጣዬ ከተማ ያሉት ወንዶችና የጸጥታ አካላት ብቻ ናቸው።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አካባቢውን መከላከያ ተቆጣጥሯል። አንጻራዊ የሆነ ሰላም አለ። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በኩል ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም። ፈቃደኛ ሆነው የሚሰጡት ማብራሪያ ካለ በቀጣይ ይቀርባል።

@tikvahethiopia