TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አማራ 🕊 ቅማንት!

‹‹ድርጅት እና መሪዎች ያልፋሉ ህዝብና #ታሪክ ግን ይቀጥላል፤ የምናልፍ መሪዎች #የማያልፍ ጠባሳ ጥለን እንዳናልፍ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡››

‹‹ማንነትን ማክበር እና ማስከበር ስንል አጥር ማጠር እና የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት አይደለም ፡፡ህዝብን ማድመጥ እና ታሪካዊ ወሰኑን ማስከበር እንጅ ተመልሶ ያደረ ጥያቄ ነው እያሉ ማለፍ ታሪኩ ያለፈበት ሂደት ነው፡፡››

‹‹ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በመጀመሪያ በህግ የበላይነት ልንገዛ ይገባል፡፡›› ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ግጭት ለታላቅ ሃገር እና ተስፋ ለሰነቀ ህዝብ የሚመጥን አይደለም፤ እንዲህ አይነት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ስራ ዛሬ ሳይሆን በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት አማራን የትኩረት ማዕከል አድርጎ ሲሰራበት ነበር ዳሩ የህዝቡን አንድንነት #ማፍረስ አልተቻላቸውም እንጅ ብለዋል፡፡

አማራን ከአገው፣ ቤተ እስራኤላዊያንን ከአማራ እንዲሁም ቅማንትን ከአማራ ለማጋጨት ጥረት ተደርጎ ነበር፤ ነገር ግን አባቶቻችን በብልጠት ሴራውን አክሽፈው እልፍ ዘመን የዘለቀ አብሮነትን አውርሰውናል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ማንነትን ማክበር እና ማስከበር ስንል አጥር ማጠር እና የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት አይደለም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብን ማድመጥ እና ታሪካዊ ወሰኑን ማስከበር እንጅ ተመልሶ ያደረ ጥያቄ ነው እያሉ ማለፍ ታሪኩ ያለፈበት ሂደት ነው ብለዋል፡፡

ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በመጀመሪያ በህግ የበላይነት #ልንገዛ ይገባል፡፡ ሃገራችን ያከበረችንን ያክል አላከበርናትም ያሉት አቶ ደመቀ ሃገር ግንባታ ጊዜ ይወስዳልና በትዕግስት ሃገር ልንገነባ ይገባል ብለዋል፡፡

እኛ እና እናንተ አሉ አቶ ደመቀ ‹‹እኛ እና እናንተ ከግለሰብ እልፍ ያለ ኃላፊነት ስላለብን ስሜት ሳይገዛን እና ከንፈራችን እየመጠጥን እንዳናዳማ ትክክለኛ መሪ እና መፍትሄ ፈላጊዎች ልንሆን ይገባል ብለዋል፡፡››

ይህ ህዝብ አብሮ ኖሯል ፤ ተዋልዷል ፤ #ደም አስተሳስሮታል እና! ይህ ቀን አልፎ ነገ አብሮ መኖሩ ስለማይቀር ‹‹መሪና ድርጅት ያልፋሉ ህዝብና ታሪክ ግን በዘመናት መካከል ይቀጥላሉና በሚያልፍ የመሪነት ዘመናችን የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ እንዳንተው ልንጠነቀቅ ይገባል››
ብለዋል፡፡

🔹በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ያለው የሰላም መድረክ እንደቀጠለ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት እነ አቶ አብዲ ኢሌ ተቃውሞ አሰሙ። ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ-ሽብር እና የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡት የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ 17 ተከሳሾች ተቃውሞ አሰምተዋል። እነ አቶ አብዲ ኢሌ ከኛ ጋር ታስረው የነበሩት እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም ሲሉ ነው ተቃውሞ ያሰሙት። …
#ችሎት

የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነአቶ አብዲ መሀመድ ኡመር አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል።

አቶ አብዲ ጨምሮ 17 ተከሳሾች " ከኛ ጋር ተከሰው የነበሩ እስረኞች ክስ ተቋርጦ እኛ ብቻ የምንታሰርበት ምንም ምክንያት የለም። በህገ መንግስቱ የተሰጠንን በእኩል የመታየት መብታችን የተነፈገ በመሆኑ ፍርድ ቤት አንቀርብም " ሲሉ ተከሳሾቹ ማክሰኞ አቤቱታ ማሰማታቸው ይታወሳል።

በአቤቱታው ላይ ፍ/ቤቱ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በተያዘው ቀጠሮ ችሎቱ ተሰይሟል።

ሆኖም ዛሬ አቶ አብዲ መሀመድን ጨምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 14 ተከሳሾች ችሎት አንቀርብም በማለት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

በዛሬው ችሎት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 3 ተከሳሾች በችሎት ቀርበው በአስገዳኝ ሁኔታ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ፍ/ቤት እንዳመጣቸው አቤቱታ አቅርበዋል። ከሌሎች ታራሚዎች ጋር ቃሊቲ እንዲዛወሩ እና አንድ ላይ ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ካለ በጽሁፍ እንዲያቀርቡ ብሏል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ አብዲ ኢሌን ጨምሮን አጠቃላይ ተከሳሾች ሌሎች እስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ መርምሮ አቤቱታውን ማቅረብ ያለባቸው ክስ ላቋረጠው መንግስታዊ አካል እንጂ ለዚህ ችሎት አደለም፤ ጥያቄው የህግ መሰረት የሌለው ነው ሲል አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጓል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ በያዘው ቀጠሮ የምስክር አሰማም ሂደት ይቀጥላል ሲል የዓቃቢ ህግ ቀሪ ምስክርን ለመስማት ለየካቲት 14 /2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዛሬ ያልቀረቡ 14 ተከሳሾችን በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ አዟል።

#ታሪክ_አዱኛ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የሬሜዲያል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከነሐሴ 23 – 26 ቀን 2015 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚወስዱ አሳውቋል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ (50%) ሳያመጡ የቀሩ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው የማካካሻ ትምህርት ፈተናን ከሰኔ 26-30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ከተፈታኝ ተማሪዎች እና የማካካሽ ትምህርቱን ከሚሰጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር አንፃር እንዲሁም በወቅቱ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሁለት የመንግስት እና በ143 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የሪሜዲያል ፈተናውን ለመስጠት ባለመቻሉ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ፈተናውን እንዲወስዱ ተወስኖ ነበር፡፡

ሚኒስቴሩ በቅርቡ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቦርድ አባላት ጋር ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረገው ውይይት እና በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፈተናው ከነሐሴ 23 – 26 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ተወስኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፦

- ፈተናው #በበይነ_መረብ እንዲሰጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ አብዛኞቹ ተማሪዎች ግን የኮምፒዩተር ክህሎት ስለሚያንሳቸው እያንዳንዱ ተቋም ከወዲሁ ተማሪዎቹን በማሰልጠን የማብቃት ስራ እንዲሰራ፣

- ተፈታኞች የ #ፊዚክስ እና የ #ታሪክ ኮርሶች በሪሜዲያል ፈተና ውስጥ እንደማይካተቱ አውቀው በሌሎች ትምህርት ዓይነቶች ላይ አተኩረው ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲደረግ፤

- ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ፈተናውን የሚወስዱበት ተቋም ወይም ቦታ በመለየት ከተፈታኝ ተማሪ ቁጥር ጋር በቶሎ እንዲያሳውቁና ተማሪዎቹ ከዋናው ፈተና በፊት ልምምድና ከፈተና ሶፍትዌር ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉ ሞዴል ፈተናዎችን እንዲፈትኑ ፤ ፈተናው የሚሰጥባቸው ከየመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችም ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ኮምፒዩተሮችን ለዚህ ስራ ዝግጁ በማድረግ ጠንካራ ክትትል እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

(በዶ/ር ኤባ ሚጄና - የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ ለሐረር መምህራን ኮሌጅ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

More : @tikvahuniversity

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው አርብ ሀዋሳ ከተማ ላይ ተፈፅሟል ስለተባለ አንድ የወንጀል ድርጊት ጥቆማ ደርሶት ተመልክቷል። ጉዳዩን በተመለከተ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን እንዲሁም ድርጊቱ ተፈፅሞበታል የተባለውን ክ/ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። 👉 ተጎጂ የራስሰው ገዛኸኝ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፦ " ሀዋሳ ላይ ቀን ነው በሚባልበት 12:30 የምናሽከረክረውን ' ላንድሮቨር…
#Hawassa

የራስሰው ገዛኸኝ የተባሉ ግለሰብ ሀዋሳ ላይ የተደራጀ ዝርፊያ እና ሳንጃ በማውጣት የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈው አሰራጭተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ መልዕክት በውስጥ ደርሶት ተመልክቷል። የሀዋሳ ፖሊስንም ስለጉዳዩ ደውሎ ጠይቋል።

" በሀዋሳ ከተማ ላይ የተደራጀ የዝርፊያ እና የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብናል " ያሉት የራሰው ገዛኸኝ ፅፈው ባሰራጩት ፅሁፍ መሰረት ፦

- ድርጊቱ የተፈፀመው ሀዋሳ፣ በተለምዶ ከአቶቴ ወደ ፉራ በሚወስደው መንገድ " ቦሌ መንደር " አካባቢ በሚገኘው የትራፊክ መብራት ጋር ነው።

- ቀኑ 12/04/2016 ዕለተ #አርብ ከምሽቱ 12:30 ላይ ነው።

- ሲያሽከረክሩት የነበረው ላንድ ሮቨር መኪና ሲሆን ውስጥ እንግዶቻቸው ከሆኑ 3 የመንግስት አካላት ጋር ሆነው ሲጓዙ ነበር።

- በተለምዶ " ቦሌ መንገደር  " የትራፊክ መብራቱ ጋር ሲደርሱ የሚያሽከረክሩት መኪና ከጎን በኩል በከፍተኛ ምት ይመታባቸዋል። አደጋ ያደረሱ ስለመሰላቸው መኪናውን ዳር በማስያዝ ያቆማሉ።

- በመኪናው ውስጥ ከነበሩት አንዱ ከመኪና ፈጥነው በመውረድ የተመታውን መኪና ዙሪያውን ቢመለከቱም የደረሰ አደጋ የለም። ግን ሰዎች ተሰብስበዋል።

- የወረደው ሰው ከመኪናው ኃላ የተሰበሰቡ ወጣቶች የደረሰውን ግጭት ምንነት እየጠየቃቸው በነበረበት ወቅት የራስሰው ገዛኸኝም ከመኪናቸው ወርደው ወደ ወጣቶቹ በመሄድ ምን ተፈጠረ ? ማለት ጥያቄ ይጀምራሉ።

- በዚህ ሁኔታ አስፓልቱ ዳር ከሚገኝ 2 ፑል ቤት አንድ ግሮሰሪ ተጨማሪ ወጣቶች ወጥተው ከበባ ያደርጋሉ፤ ወዲያው አንድ ወጣት በተለምዶ በአከባቢው አጠራር " ባንጋ " የተባለ የሚጠራውን ሳንጃ ይዞ ማሳደድ ይጀምራል።

- በተፈጠረው ሁኔታው #ተደናገጠው ቢያፈገፍጉም ወጣቱ ሊተዋቸው ባለመቻሉ ወደ መኪናው ለመግባት ሲሞክሩ እዛው ጋር የነበሩት ሌሎች ወጣቶች በሩን እንዳይገቡ ይይዙታል።

- ሁኔታው በተደራጀ መልኩ #ዘረፋ መሆኑ ስለገባቸው በሳንጃው ላለመወጋት ይሸሻሉ።

- በዚህ መካከል ከመኪና ውስጥ ያልወረዱት ሰዎች መኪናውን ሎክ ለማድረግ ቢሞክሩም ሌሎች ወጣቶች ከኃላ በር በመክፈት፦
* ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣ
* ከአንድ ፕሮግራም ቀረፃ እየተመለሱ በመሆኑ ብላክ ማጂክ ካሜራ ፣
* መቅረፀ ድምፅ የያዘ ቦርሳ ይዘው ተሰውረዋል።

- አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ዘራፊዎቹ ከአከባቢው መሰወራቸውን ተመልክተው " ስፍራውን ቶሎ ለቃችሁ ካልሄዳችሁ አሁን ከመጡ #ይገሏችኋል " በማለት አከባቢውን ለቀው እንዲሸሹ ያስፈራሯቸዋል።

- በተጠና ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ኦፕሬሽን በመሆኑ ከአከባቢው ለመሄድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው የፓሊስ አካል እስኪመጣ ጠበቁ።

- በዚህ መካከል አንድ የፓሊስ አባል ይመጣል። ቀርቦ ምንድነው ? ሲል ይጠይቃል። እነሱም የደረሰባቸውን የዘረፋ ወንጀልና የግድያ ሙከራ አስረድተው የህግ ከለላ ቢጠይቁም። ፓሊሱ " በቃ አሁን ከዚህ ሂዱ ልጆቹ ከላልታወቁ ምን ማድረግ ይቻላል ? " በማለት መልሷል።

- የፖሊስ አባሉ ቢያንስ እንኳን #ፓትሮል ደውሎ ኃይል እንዲያስጨምርላቸው ቢነግሩትም ፤ " እኔ የናንተ ጠባቂም ተላላኪም አይደለሁም " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል።

- ወደ አንድ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ዘንድ ደውለውም እንዲደርሱላቸው ፤  የደረሰባቸውን በደል ቢያስረዱም ከባለስልጣኑ ዘንድ ምንም አይነት እርዳታ አላገኙም።

- ወደ ተለያዩ የህግ አካላት በመደወል #ከ40_ደቂቃ በኃላ አንድ የፓሊስ ፓትሮል ሊመጣ ችሏል።

- የመጡት የፖሊስ አባላት ችግሩን ለመስማት የሞከሩ ሲሆን " የዘራፊዎችን ማንነት እና ስም " ከተፈራፊዎች ይጠይቃሉ። እነሱም መንገደኛ በመሆናቸው ገልጸው የዘራፊዎቹን ማንነት በስምና በአድራሻ ለይቶ ለፓሊስ መናገር የሚችሉበት መንገድ ስላልገባቸው ቢያንስ የተወሱ ወጣቶች የወጡበትን ግሮሰሪ እና ፑል ቤት አሳዩ።

- ከፍተኛ #ክርክር እና አለመግባባት ከተፈጠረ በኃላ የፖሊስ አባላቱ የተፈፀመውን ነገር የዕለት መዝገብ ላይ እንዲያስመዘግቡ በማለት ወደ ታቦር ክፍለ ከተማ ፓሊስ ማዘዣ ጣቢያ እንዲሄዱ አድርገዋል።

- ፖሊስ " የፑል ቤቱ ባለቤቶች  " አንዳንድ ነገር ሲናገሩ በመስማታቸው አስረዋቸዋል። ነገር ግን ዋናዎቹ የተደራጁትን የዘራፊ ቡድኖች የያዘም ሆነ በወቅቱ ለመከታተል የሞከረ አካል የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መልዕክት ከተመለከተ በኃላ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ፤ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ አሁን ላይ በከተማዋ ዉስጥ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች በጅጉ የተሻለ ሰላም ያላት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ጠቅሰዋል።

ተፈፅሟል የተባለውን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ ሲያዩት #ማዘናቸዉን ገልጸዋል።

ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ፤ ችግር ተፈጥሮ ከሆነ በተዋረድ ለሚመለከተዉ አካል ማቅረብ እንደሚቻልና በተለይ እንዲህ ያለዉን ጉዳይ እንኳን ፖሊስ የትኛዉም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ከማስቆም ወደኋላ እንደማይል ገለጸዋል።

አሁንም " ችግሩ ተፈጽሞብን ፍትህ አጣን " የሚሉ አካላት በየትኛዉም ጊዜ ማመልከት ቢፈልጉ ቢሯቸዉም ሆነ ስልካቸዉ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ብዙዎች ሰላሟን የሚመሰክሩላትን ሀዋሳ ከተማን በትንሹ መገመት አግባብ አይደለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተጎጅዎች እንዲያመለክቱና ቃላቸውን እንዲሰጡ የተደረጉበትን የታቦር ክ/ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ወንድዬ ከበደን አነጋግሯል።

እሳቸው በሰጡት ምላሽ በወቅቱ መኪናችን ተመታብን ያሉት አካላት ወደፖሊስ ጣቢያዉ በመምጣት ባስመዘገቡት መሰረት በአካባቢዉ ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ተይዘዉ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢ/ር ወንድዬ ፤ የተጠቀሱት ንብረቶች መሰረቃቸዉን በወቅቱ አለመስማታቸውን እና አለመመዝገባቸዉን አስታውሰዉ አሁንም ቢሆን ጉዳዩን በአግባቡ ወደሚመለከተዉ የህግ አካል በማቅረብ በተያዘዉ ምርመራ እንዲካተት ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ተጎጅዎች " በተደራጀ ዝርፊያ ጥቃት ተፈጽሞብናል " የሚሉት የተሳሳተ መሆኑን የሚያነሱት ኢንስፔክተሩ በወቅቱ ' ግጭት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ' ውስጥ በመግባታቸዉ ለስርቆት ተዳርገዉ ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጅ በከተማዉ የተባለዉ አይነት ዝርፊያ በፖሊስና በማህበረሰቡ ትብብር #ታሪክ_የሆነ ጉዳይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃለማርያም ሀገር ጥለው ከወጡ ዛሬ ድፍን 33 ዓመት ሆኗቸዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ/ም ነው ከሀገር የወጡት። የድርግ ውድቀትን እና የ #ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ መቃረብን ተከትሎ ከሀገር እንደወጡ የሚነገርላቸው ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃለማርያም በአንድ ወቅት ፤ " እኔ ኮብልዬ አልወጣሁም " ሲሉ ነበር ቃላቸውን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ #ታሪክ

የቀድሞው ፕሬዜዳንት ሀገር ጥለው ከወጡ በኃላ ለ7 ቀናት ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ናቸው።

የ7 ቀኑ መንግሥት በወቅቱ ' የተስፋዬዎች መንግስት ' የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር። ይህ ስያሜ የተሰጠው ፦

- ተስፋዬ ገ/ ኪዳን ➡️ ተጠባባቂ ፕሬዜዳንት
- ተስፋዬ ዲንቃ ➡️ ጠቅላይ ሚኒስትር
- ተስፋዬ ወልደስላሴ ➡️ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር
- ተስፋዬ ታደሰ ➡️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው ነው።

ሌ/ጄነራል ተስፋዬ በተለይም ፦

" #የኢትዮጵያ_ህዝብ_ሰላም_ጠምቶታል። የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሰላም መታጣት በመሆኑ ቀዳሚው ጉጉቱና ናፍቆቱ ሰላም ነው።

በሰሜንም ሆነ በደቡብ፣ በምስራቅም ሆነ በምዕራብ በመሃልም ሆነ በደንበር ኢትዮጵያዊ እናት፣ ኢትዮጵያዊ አባት፣ የወደፊት ባለተስፋ የሆነው ወጣት ሁሉ ከምን ጊዜ በላይ ምኞቱ ሰላም ነው። " በሚለው ንግግራቸው ይታወሳሉ።

ከ7 ቀናት የ ' ተስፋዬዎች መንግሥት ' በኃላ ኢህአዴግ ሀገሪቷን ተቆጣጠረ ፤ 17 ዓመታትን በስልጣን ላይ የቆየው ደርግም እስከወዲያኛው ላይመለስ አከተመ።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia