TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለኩ⬆️

በለኩ ከተማ በ"እኔም ለወገኔ ወጣቶች" አስተባባሪነት ትላንት በጁኒየር ትምህርት ቤት የተጀመረው የደም ልገሳ በዛሬው ዕለት በለኩ #ሆስፒታል መቀጠሉን ሰምተናል። "ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ውዱ ስጦታ #የደም ስጦታ ነው" በሚል መሪ ቃል ነው የድም ልገሳው እየተደረገ የሚገኘው።

#ደም_በመገስ_ተደምረናል!

©Devila
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመጀመሪያውን የ3 ወር ስራ ለማስጀመር!!

በሺዎች የሚቆጠሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የቀረበውን ሀሳብ ወደውታል ያላችውን ስጋትን እና ጥርጣሬን ገልፀዋል። በተለይ ተረጂዎችን በመለይት ውስጥ ጥልቅ ጥናት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል። በዚህ ምንም አያሳስበንም በቂ #ማስረጃ ይዘን ነው ሰው የምንደግፈው። ከመንግስት አካላት ጋር እና ከማዕበረሰቡ ጋር በቅንጅት ይሰራል። እገዛ የተደረገላቸው ሰዎችም ስልክ እና አድራሻቸው ይገለፃል። በአካል ሄዶ መጠየቅ ይቻላል። ተማሪዎች ምልመላም በከፍተኛ ጥንቃቄ ይሰራል። ለተለያዩ የበጎ አድርጎት ድርጅቶችም እገዛ ሲደረግ በግልፅ በይፋ ይገለፃል።

ማሳሰቢያ፦ TIKVAH-ETH የኢትዮጵያዊያን መሰብሰቢያ ቤት ነው። #እንደድርጅት የተቋቋመ አይደለም። በግለሰብ ተነሳሽነት የሚንቀሳቀስ ነው።

በአካውንቱ ዙሪያ የቀረቡት ሀሳቦች፦

የመጀመሪያው እንደ ማህበር እንዲቋቋም እና አካውንት እንዲዘጋጅ ለዚህም ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል። አሁን ቤተሰባችን ይህን የሚያደርግበት ደረጃ ላይ አይደለም። በቀጣይ 2 አመት እቅድ ውስጥ የተካተተ ነው ይሄ!! አካውንት እንደ ማዕበር ለማዘጋጀት ብዙ የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዳሉ ተጠቁሟል።

ሌላኛው፦ በ5 አባላት ስም እንዲከፈት ስለሰዎቹ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጥ እነማን እንደሆኑ አካውንቱ ውስጥ ያለው ገንዘብ በሶስት ሰው ፍቃድ እንዲወጣ ማድረግ!! ለዚህም ሰዎችን መምረጥ የሚል ነው።

የመጨረሻው፦ TSEGAB WOLDE ባዶ አካውንት ተከፍቶ ስራው እንዲጀመርም እንደሀሳብ ቀርቧል። ይህም ለስራ እና ለግል ከምጠቀምበት ውጭ የሆነ እንዲሆን የሚል ሀሳብ ነው። ማንኛው አይነት የገንዘብ እንቅስቃሴን የTIKVAH-ETH ባንክ ቤት ሰራተኞች እንዲከታተሉ እና #ሌብነትም ላይ ስጋት እንዳይኖር እንቅስቃሴውን ሁሉ እየተከታተሉ ለህዝብ እንዲገልፁ የቻናሉ admin እንዲሆኑ እንዲደረግ የሚል ሀሳብም ቀርቧል። አካውንቱ በ15 ቀን ወይም በወር ባዶ እንደሆነ ለህዝብ እንዲታይ! በአካውንቱ ውስጥ በምንም ምክንያት ብር እንዳይኖር...ይህንንም ለህዝብ ማሳየት።

ለዚህም፦ 10 የባንክ ሰራተኞች admin እንዲሆኑ ሃሳብ ቀርቧል።

ሌላው ምንም አይነት ጥርጣሬ እና ስጋት ካለ እገዛው ያለአግባብ ተሰጥቷል፣ ገንዘብ ባክኗል የሚል ሰው በማስረጃ አስደግፎ ይሄን ቁጥር ይዞ 0919 74 36 30 ለፖሊስ እንዲያመለክት እንደሀሳብ ቀርቧል።

በድጋሚ ማሳሰብ የምወደው ነገር፦ #ተቀማጭ የሚባል ገንዘብ የለም። በወር ሁሉም ገንዘብ ወጥቶ ለታለመለት አላማ ይውላል።

🔹የቀን ሪፖርት በተመለከተ፦ በየዕለቱ ያለውን እንቅስቃሴ በቻናሉ ላይ በግለፅ ይገለፃል። ከባንክ የሚላኩትን መረጃዎች ህዝቡ በፎቶው እንዲያየው ይደረጋል።

ይህ እቅድ መነሻ ነው! ሶሻል ሚዲያውን እንዴት ለትልቅ ለወጥ መጠቀም እንደምንችል የምናሳይበት ነው። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ደግሞ #ሆስፒታል እና #ትምህርት_ተቋማት በራሳችን ወጪ በመግንባት ለሀገራችን ሰርተን የምናልፍበትን መንገድ የምንጀምርበት ነው።

ሲጠቃለል...

ድምፅ እንድትሰጡ በትህትና እጠይቃለሁ፦

❤️TIKVAH-AID በእቅዱ መሰረት ከ2 ዐመት በኋላ እንደማህበር ከተቋቋመ በኃላ ወደ ስራ እንግባ!

💚5 ሰዎች ከቻናሉ ተመርጠው አካውንቱ ተከፍቶ የቀኑን ውሎ ከባንክ በምናገኘው መረጃ እየተከታተልን ሰዎችን እንርዳ!!

💜ባዶ አካውንት ተዘጋጅቶ ሁሉም በየቀኑ አካውንት ውስጥ የገባውን ገንዘብ እንዲያየው ይደረግ። በ15 ቀን የገባው ገንዘብ ወጥቶ እንዲረዳበት። ገንዘብ ሲወጣ እና ሲገባ በየሰዓቱ በፎቶ ይገለፅ!!

እኛ ጋር የተሻለ ሀሳብ አለ የምትሉ ደግሞ በ0919 74 36 30 ወይም @tsegabwolde አናግሩኝ!

እናተው ወስኑ እና ወደእንቅስቃሴ መግባት እንችላለን! ብዙሀኑ ጥርጣሬ ካደረበት ደግሞ ስራው አይሰራም ይቆማል። ሀሳቡ ተቀባይነት ካጣ አብረን መስራት የምንችል ሰዎች ብቻ ተነጋግረን መጠነኛ ድጋፍ የማድረግ ስራ ላይ እንሰማራለን።

〽️ እንደከዚህ ቀደሙ የታመሙ ሰዎችን የምንረዳበት ስራ ግን አይቋረጥም። ይቀጥላል!!

🔹ከምንም በላይ የባንክ ቤት ሰራተኞች ሌብነትን በማጋለጥ በዚህ ስራ ውስጥ ይሳተፋሉ ብዬ ጠብቃለሁ። በፌስቡክ እና በቴሌግራም 1 ብር እንኳን ከባከነ ለህዝብ ያሳውቃሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ኮተቤ ዩኒ ቨርሲቲ አካባቢ በግንባታ ላይ የነበረ #ድልድይ አርማታ #ተደርምሶ 12 ሰዎች #ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ #ሆስፒታል ተወስደዋል። በአደጋው #ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ #የታወቀ ነገር የለም።

Via EBC
ፎቶ፦m & jes(tikvahethiopia)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ👆

ሰሞኑን በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ያለመረጋጋት ጉዳት ደርሶበት በባሕር ዳር ጥበበ ጊዮን ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተለ ያለው የ3ኛ ዓመት ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ታደለ በዛ ጋር አብመድ ቆይታ አድርጓል፡፡

‹‹ራሴን ያገኘሁት #ሆስፒታል ውስጥ ተኝቼ ነው፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ ማስታወስ አልቻልኩም፡፡ አሁን ላይ ሆኜ የማስታውሰው ነገር ቢኖር ያለፈው እሑድ ለሳምንት ያህል በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የውኃ እጥረት መፈጠሩን ተከትሎ ሰልፍ ተደርጎ ነበር፤ ሰልፉን ለመበተን የገቡ የፌዴራል ፖሊሶች ደግሞ በየብሎኩ ሲያሯሩጡን ነበር፤ እስከምሮጥ ድረስ፤ አስታውሳለሁ ከዚያ በኋላ ግን ራሴን ያገኘሁት ሆስፒታል ውስጥ ነው፡፡ ያች ቅፅበት ቀኝ እግሬን አሳጥታኛለች፤ …ከበፊቱ ቢሻለኝም… ያመኛል›› ብሏል ተማሪ ታደለ በዛ፡፡ አብመድ ስለጉዳቱ መንስኤ ያነጋገረው ተማሪ ታደለ ‹‹ጉዳቱ በምን እንደደረሰብኝ አላውቅም›› ብሏል፡፡

የጥበበ ግዮን ሪፈራል ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ድሕረ ምረቃ ሐኪም ዶክተር አደራው ጌቴ ‹‹ተማሪ ታደለ ከ13 ሰዓታት በኋላ ወደ እኛ መጥቶ ሰኞ ምሽት ቀዶ ጥገና ተደርጎለታል፤ በራጅ እና ላብራቶሪ በተደረገለት ምርመራ ቀኝ እግሩ ታፋ ላይ ስብራት ደርሶበታል›› ብለዋል፡፡

ዶክተር አደራው ‹‹በታደለ ላይ የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ ወደ ፅኑ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ገብቷል፤ በሕመሙ ከፍ ብሎ ከታፋው ወደ ሳምባው ያለመተንፈስ ችግርም ገጥሞታል፤ ወደ ከፋ ችግር እንዳይደርስ ግን የምንሰጠው ሕክምና ያግዘዋል›› ብለዋል፡፡

‹‹ታካሚው በጥይት ነው የተመታው የሚባለው ነገር ትክክል አይደለም፤ ጉዳቱ ከገደላማ ቦታ ወድቆ ከመሰበር አደጋ ጋር የተያያዘ ነው›› ብለዋል፡፡

አብመድ ያነጋገራቸው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው ለአንድ ሳምንት ያክል የንጹሕ መጠጥ ውኃ ባለማግኘታቸዉና ዩኒቨርሲቲው አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ የሚመለከተውን አካል ለመጠየቅ ሰልፍ በወጡበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሰልፍ ወጣን፤ ጥይት መተኮስ ጀመረ›› ብለዋል፡፡

‹‹እኛ ሰልፍ እንደወጣን ውኃው ተለቀቀ፤ ይህ ማለት ችግሩ ከአቅም በላይ ሁኖ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ባለመስጠቱ የተፈጠረ ችግር ነበር ማለት ነው›› ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ ሞላ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሰው ሕይወት እንደጠፋ እና ሆን ተብሎ ተመትቷል የተባለው ትክከል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ያሳለፍነው እሑድ ተማሪዎች በውኃ እጥረቱ ምክንያት ሰልፍ እያደረጉ ነበር፤ እኛም እጥረቱን ለመፍታት መረጃው እንደደረሰን ስንጥር ነበር፤ እንደአጋጣሚ በዕለቱ ችግሩ ተፈታ፤ ተማሪዎቹ ግን ሰልፉን ከማቆም ይልቅ ንብረት ማውደም በመጀመራቸው የፀጥታ አካላት ገብተው እንዲያረጋጉ›› ተደርጓል ብለዋል፡፡

ዶክተር ደሳለኝ ‹‹ሠላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በተማሪዎች እርስ በርስ መገፋፋት ተፈጥሮ ተማሪ ታደለ በዛ ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሰው ሕይወት አልፏል እየተባለ የሚወራው ግን የተሳሳተ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ ቢቋረጥም አሁን ዋናው ችግር የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦቱ መፈታቱ ታውቋል፡፡ ሌሎች ችግሮችም ካሉ ቀስ በቀስ በሚቻለው ልክ ምላሽ እስከሚሰጥ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀው ይህንን በማያደርጉ ተማሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደዱ አሳስበዋል፡፡

Via AAMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia