TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ እርምጃ እንወሰወዳለን " - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች #ሒጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ዛሬ ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል። በዚሁ መግለጫ " የፌደራል…
#Update
" ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃዎችን እንስወዳለን " - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ የተከለከሉ 160 የያዝነው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ካለፈው ጥቅምት 2017 ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች እንዳደረገ ምክር ቤቱ ጠቅሷል።
ትምህርት ቤቱ በያዝነው ሳምንት የትግራይ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህግ እና ደንብ ባልወጣበት ሁኔታ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸው እንዳይማሩ መደረጉ ልክ እንዳልሆነ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ባለመቀበል ተማሪዎቹ በማስፈራራት እና በማሰር ከእውቀት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉ ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።
ምክር ቤት ባወጣው የ11 ነጥብ የአቋም መግለጫ፦
1. የሂጃብ ክልከላው በህገ-መንግስት የተቀመጡ የጋራ እና የግል መብቶች የሚፃረር ፣ በትምህርት ሚንስቴር እና በክልሉ መከበር ያለባቸው ደንቦች የጣሰ ነው።
2. የትምህርት ቤቶች ህግ በህገ-መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች የሚፃረር መሆን የለበትም። በትምህርት ሚንስቴር ደንብ ቁጥር -6 ንኡስ ቁጥር -3 ሂጃብ መልበስ እንደሚፈቅድ በግልፅ ተደንግጓል ስለሆነም ጥያቄያችን በዚሁ ደንብ በአስቸኳይ እንዲመለስ እንጠይቃለን።
3. ትግራይ አሁን ባለችበት ፓለቲካዊ ቀውስ በሃይማኖት ምክንያት ሌላ ቀውስ መጨመር ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስልን።
4. በጦርነቱ ምክንያት ከእውቀት መአድ ርቀው የነበሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲበረታቱ የሚገባቸው ሙስሊም ሴቶች ማበረታታት ሲገባ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ መከልከል ፍፁም ኢ-ህጋዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን።
5. ጉዳዩ በማንኛውም መልኩ ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀምያ ማዋል ስለማይገባ ጉዳዩ እንዳይፈታ የሚያወሳስቡት ግለሰቦች ወይም አካላት መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው ጥሪ እናቀርባለን።
6. ኢ-ህገመንግስታዊ ተግባሩን የሌሎች እምነት ተከታዮች እና የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች እንዲያወግዙት ጥሪ እናቀርባለን።
7. ከትምህርት ገበታ የተስተጓጎሉት ተማሪዎች የትምህርት ሚንስቴር ያወጣው ሁሉም ትምህርት ቤቶች መፈፀም የሚገባቸው የአለባበስ ሁኔታ የሚመለከት ህግና ደንብ ያልጣሱ ስለሆነ ትምህርታቸው እንዲቀጥሉ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን።
8. ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ እየተደረገ ያለው ተግባር ሰብአዊ መብቶች ፣ ክልላዊ ፣ አገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ህጎች የሚፃረር በመሆኑ በጥብቅ እንኮንነዋለን።
9. ከትምህርት ሚንስቴር መመሪያ እና ደንብ ባፈነገጠ መልኩ በግል ፍላጎት ብቻ በመመራት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ህገ-ወጥ ተግባር የፈፀሙት ግለሰቦች እና አካላት በህግ እንዲጠየቁ ጥሪ እናቀርባለን።
10. የአክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ የተደረገው ህገ-ወጥ ተግባር እንዲወገዝ ድጋፍ የቸራችሁ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ምክር ቤቱ ምስጋና ያቀርባል።
11. ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች ለህዝባችን እናሳውቃለን።
... ብሏል።
መረጃውን የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል። ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ። @tikvahethiopia
#Update
ከጥቂት ከደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ነው።
ዛሬ በተለያየ ሰዓት አምስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የአሁኑ ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው (በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካው ) በመጠን ከፍተኛው ነው።
ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ በደንብ ተሰምቷል።

#Update 🚨 “ ግብረሰዶም ወደ ሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ ➡️ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኑሮን ለማሻል በሚል ወደ ታይላንድ የሄዱና በኃላም ወደ ማይናማር የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን በጋንግስተሮች እጅ ወድቀው ከውላቸው ውጪ ህገወጥ የዶላር ማጭበርበር…
#Update
“ ከ29 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ኮሚቴ
በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲያስወጣቸው በተደጋጋሚ እየተማጸኑ እንደሚገኙ ይታወቃል።
የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ፣ “ ግብረሰዶም ወደማፈጸምበትና ኩካሊት እያወጡ የሚሸጡ ሰዎች ወዳሉበት ካምቦዲያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ስጋቱን ገልጾልን ነበር።
ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅነው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ልጆቹ ያሉበት ቦታ አዳጋች እንደሆነ፣ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት አለመኖሩ ሁኔታውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም።
ከቶኪዮ ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም ገልጾ የነበረው ሚኒስቴሩ ከዚያ በኋላ ላቀረብለት ጥያቄ፣ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” ቢልም እስካሁን ያለው ነገር የለም።
አሁንስ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
የወላጆች ከሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ከ29 በላይ የማሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ አገር ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” ብሏል።
በመሆኑም ልጆቹ ካሉበት ስቃይ እንዲወጡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ቢሯዎቻቸውን እያንኳኳ በደብዳቤ ጭምር እየተማጸነ መሆኑን ገልጾ፣ መንግስት አሁንም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።
ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?
“ ምንም መፍትሄ የለም። እንዲያውም የተወሰኑ ልጆችን ወደሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋልና ያን የሰሙ ልጆች በጣም ተረብሸዋል።
ወደ ካምቦዲያ እየሸጧቸው ነው ስለተባለ ተጨናንቀዋል። በየቀኑ ‘ምን አዲስ ነገር አለ?’ ነው የሚሉን። እኛም ውጪ ጉዳይን አሳስበን መፍትሄ በመጥፋቱ አሁን የሃይማኖት ተቋማትን እየተማጸንን እንገኛለን።
ልጆቹን በማይናማር ከነበሩበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ እየሸጧቸው ነው። ይሄ ነው ችግር የሆነው። በየጊዜው አዲስ ነገር ነው የሚሰማው በጣም ይጨንቃል።
ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምንም አዲስ ነገር የለም። አሁንም ተሰባስበን ልንሄድ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እየተማጸንን ነው።
ዱኣ አድርጉ፤ ጾም ጸሎት ይታወጅ ብለን እየጠየቅን ነው።
ሀገራቱንም፣ ህዝብንም፣ ቤተሰብንም መጥቀም የሚችሉ የተማሩ ልጆቻችን ስቃዬ ላይ እያሉ ውጪ ጉዳይ ሰምቶ ዝም ከማለት ያስቸገረው ነገር ካለም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትም ሄደን ነበር ለቅሬታ ሰሚ ክፍል ጥያቄያችንን በኢሜይል እንድናስገባ ነው የነገሩን። ግን በኢሜይል ብቻ አስገብተን አንቀመጥም ደብዳቤም እንወስዳለን ” ብሏል።
(ጉዳዩን እስከ መጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA

በነገው ዕለት ፓርላማው በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ፥ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሏል።
ከንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦
" #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል። "
የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ለመደንገግ ከተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ፦
" የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 50 ሺህ እስከ ብር 100 ሺህ የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል።
መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል እስከ 3 ዓመት እስርና እስከ 300 ሺህ ብር ቅጣት ያስጥላል። "
🔴 ስለ ንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም ያጋራናችሁን ዝርዝር መረጃና ሰነድ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/88315
🔵 ስለ ነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት ስለሚደነግገው ረቂቅ አዋጅ ያጋራናችሁ ዝርዝር መረጃ ደግሞ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/92370?single

Photo
#Update
በትግራይ ክልል ፤ አክሱም ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ መከልከል ጋር ተያይዞ የተከሰተው ውዝግብ አሁንም መቋጫ አላገኘም።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጉዳዩ በማስመልከት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማ በሰጠው መግለጫ " የመብት ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተመለሰ ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ እንወሰዳለን " ብሎ ነበር።
በመግለጫው " የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን " ማለቱም ይታወሳል ።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አክሱም ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጠው ፤ ከምክር ቤቱ መግለጫ በኋላ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ወደ አክሱም በማምራት ከትምህርት ቤቱ አመራሮች ፣ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች ተወያይተዋል።
የመረጃ ምንጫችን " ውይይቱ መሬት ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አላመጣም " ብሏል።
" የቢሮ ሃላፊው የትምህርት ሚንስቴር ህግ ፣ መመሪያ እና ደንብ መሰረት ያደረገ ትእዛዝ መስጠት ሲገባቸው ፤ ጉዳዩን ለማሸማገል ያደረጉት ጥረት ተጎጂ ተማሪዎቹ መታደግ አልቻለም " ሲል አክሏል።
ስለሆነም ችግሩ በቀጣዩ ቀናት መፈታት ካልተቻለ 160 የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች እጣ ፈንታ አደጋ ላይ ይወድቃል ሲል የመረጃ ምንጩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተናግሯል።
የመቐለ ቲክቫህ አባል ለትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘው መረጃ ደግሞ ከውዝግቡ ጋር በተያያዘ ይሁን ለሌላ ስራ ጉዳይ ነገ የፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ የሃይማኖት አመራሮች መቐለ ትግራይ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በተጨማሪ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅንም አጽድቋል፡፡ አዋጁ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

የጉምቱው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሃብት (የኢኮኖሚ) ሊቅ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል።
ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ የአስክሬን ሽኝት ይደረጋል።
ከሽኝቱ በኋላ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል።
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መስራቾች አንዱ እንደነበሩ የሚታወቅ ሲሆን ፓርቲው መላው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ከቤታቸው ለገጣፎ አንስቶ በሚደረገው ሽኝት እና በስርዓተ ቀብራቸው ላይ እንዲገኝ ጥሪ አቅርቧል።
ኦፌኮ አቶ ብልቻ ደመቅሳን " የሀገር ዋርካ " ሲል ገልጿቸው በህልፈታቸው ሀዘን ላይ መሆኑን ገልጿል።

#USA 🔥 በአሜሪካ ፤ በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ ነው በተባለ የሰደድ እሳት እስካሁን በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል። እሳቱ በሎስ አንጀለስ ከተማ በብዙ ስፍራ እየተዛመተ ነው ተብሏል። የሰደድ እሳቱ የሆሊውድ ምልክት በሚገኝበት የሆሊውድ ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ እየተያያዘ መሆኑ ተነግሯል። በሎስ አንጀለስ እና በአጎራባች ግዛቶች ቢያንስ 5 ሰደድ እሳቶች የተያያዙ ሲሆን ሶስቱን…
#Update
እስካሁን ድረስ መቆጣጠር ባልተቻለው የአሜሪካ፣ ሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ምክንያት ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ከ137 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
የበርካታ ሰዎች ቤት ወደ አመድነት ተቀይሯል።
ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት 135 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ከዚህም ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።
እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢቀጥልም ዝነኛ ወደሆነውና የአሜሪካ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወደሚሰሩበት " ሆሊዉድ " እየተቃረበ ነው ተብሏል።
በቀጣይ ቀናት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኛነት መተንበይ ባይቻልም ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ወይም ለመውጣት እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዛሬ ጥር 5/2017 ዓ.ም ተፈናቃዮች " ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን ! " በሚል የጀመሩትን ሰላማዊ ሰልፍ የሚደግፍ መግለጫ አውጥተዋል።
" ይበቃል ወደ ቄያችን መልሱን በሚል መሪ ቃል በተፈናቃዮች የተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቀናና የሚደገፍ " ብሎታል ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው።
" የተፈናቃዮች መከራ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም " ያለው መግለጫው " የፌደራል መንግስት የገባው ውል እና ቃል በመተግበር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለበት " ሲል በአፅንኦት ገልጿል።
" አሁንም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ከአገር መከላከያ ውጪ ያሉ ታጣቂዎች ይውጡ " ሲልም አክሏል።
" በህገ-መንግስቱ ማእቀፍ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ አለባቸው "ም ብሏል።
" የአፍሪካ ህብረት ፣ የአሜሪካ መንግስት ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የህዝቡ ድምፅ በማዳመጥ የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ጫናቸው እንዲያሳድሩ " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
" ፅላል ስቪክ ማሕበር ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ " የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ያስተባበረውና " ይበቃል ! " በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቐለ ሮማናት አደባባይ መንገድ በመዝጋት የተጀመረው የተፈናቀዮች ሰላማዊ ሰልፍ እስከ ጥር 7/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል ታውቋል።
ዛሬ በርካታ የመቐለ ጎዳናዎች ተዘግተው በርካታ የፖሊስ አባላትም ተሰማርተው ነው የዋሉት።

#Update #Axum
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።
" ያልተመዘገበ አይፈተንም " ማለቱ ይታወሳል።
ከሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ጋር ተያይዞ በአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ውዝግብ ባለመግባባት ተቋጭቷል።
159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።
ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተለው የቆየው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ከሰዓት በኋላ ወደ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ደውሎ አግኝቷቸዋል።
ርእሰ መምህር ስዩም ካሕሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" - በትምህርት ቤታችን ከተለመደው የአለባበስ ስርዓት የተለየ የተሰጠ የአለባበስ ትእዛዝ የለም።
- ሴት ሙስሊም ተማሪዎቻችን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከትምህርት ቤቱ አመራር በአካል በመምጣት እንዲወያዩ ማስታወቅያ በመለጠፍና ስልክ በመደወል ጥረት ተደርጓል ለመምጣት ፍቃደኛ ኣይደሉም።
- የአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ጉዳዩ እንዲረግብ ከትምህርት ቤታችን ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ከአገር ሽማግሌ እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ሰላማዊ ልመና ቢቅርብላቸውም ጉዳዩ ለማርገብ ፍቃደኛ አልሆኑም።
- በአጠቃላይ የፈተና ፎርም ያለ መሙላትና ያለ መፈተን ፍላጎቱ ከተማሪዎቻች ፍላጎት ውጪ የውጭ ተፅእኖ እና ግፊት አለበት።
- ልጆቻችን በቀላሉ በመግባባት ሊፈታ በሚችል ጉዳይ ከፈተና ውጪ መሆናቸው እንደ ርእሰ መምህርና ወላጅ እጅግ እሞኛል አበሳጭቶኛል " ... ብለዋል።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ታህሳስ 22 ቀን 2017 ከህገ-መግስት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ክልከላ ውጪ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች " ሂጃብ " እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፥ " ፍትሃዊ ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልላችን የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የምንወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎችን ለህዝባችን እናሳውቃለን " ማለቱ ይታወሳል።
ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት ጥያቄዎቹ በሚመለከተው አካል ጀሮ ዳባ ልበስ መባላቸውን በማረጋገጡ በታህሳስ 30 ቀን 2017 ባወጣው አጭር መግለጫ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ክስ መመስረቱ ግልጽ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አመራሮች ስለ ጉዳዩ አሁናዊ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጡ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
ከ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጭ የሆኑት 159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ወዴት ያመራ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።