TIKVAH-ETHIOPIA
ደሴ አድባሯን አጣች ! ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የከተማ አስተዳደሩ ፥ " ደሴ አድባሯን አጣች፤ ብዝኅ ሕይዎት ጠባቂያቸውን እና ተንከባካቢያቸውን ተነጠቁ፤ ሊቀ ትጉሀን ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ " ብሏል። " የሁሉ አባት፣ የሁሉ አለቃ፣ የሁሉ መካሪ፣ የሁሉ ዘካሪ፣ የሀገር ምሰሶ፣ የቤተ ክርስትያን ድምቀት እና የአውደ ምህረት ጌጥ ነበሩ "…
ፎቶ ፦ የሁሉ አባት የሆኑት የአባ መፍቀሬ ሰብእ ክቡር አስከሬን ሌሊቱን በርዕሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ሰዓታት ፣ ማኅሌት ሲደረስ አድሮ ፣ በክብር አሸኛኘት ወደ ደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በመድረስ በአሁኑ ሰዓት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐት እየተደረገ እንደሚገኝ ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የተገኘው መረጃ ያሳያል።
የደሴ አድባር ፣ የሁሉ አባት፣ የሁሉ አለቃ፣ የሁሉ መካሪ፣ የሁሉ ዘካሪ፣ የሀገር ምሰሶ፣ የቤተ ክርስትያን ድምቀት እና የአውደ ምህረት ጌጥ እንደነበሩ የተገለጸላቸው ሊቀ ትጉሀን ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ በ96 አመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወሳል።
Photo Credit - ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል/ TMC
@tikvahethiopia

" በተፈጸመባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታለች፤ የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " - የቤተሰብ አባል
በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ' የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም ' በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ ክፉኛ የተደበደበችና የተገረፈች የ3 ልጆች እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ።
በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው ኩሹ ቦናያ የተባለችው እናት በደረሰባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታ " የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " በማለት የቤተሰብ አባሏ ገልጸዋል።
የአካባቢው አቃቤ ሕግ በበኩላቸው ግርፋቱን መፈጸማቸው የተጠረጠሩ ባለቤቷን ጨምሮ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ መካሄዱን ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፈዋል የተባሉት ሽማግሌዎች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ጃርሶ ቡሌ (ዘመዷ) ምን አሉ ?
" ኩሹ ቦናያ የ3 ልጆች እናት ናት።
ገበያ ላይ አስሮ የመግረፉ ድርጊት የተፈጸመው ባለፈው ወር መስከረም 9/ 2017 ዓ.ም. ነው።
ግርፋቱ የተፈጸመባት ባለቤቷ ገልገሎ ዋሪዮ ይባላል።
ኩሹ እና ባለቤቷ ገልገሎ በትዳር 12 ዓመት ቆይተዋል
በኑሯቸው ችግር ውስጥ ሲወድቁ ባለቤቷ ወደ ውትድርና ይገባል። በውትድርና 4 ዓመት ያህል ቆይቷል።
እሷ ልጆቿን ለማሳደግ ብቻዋን ስትጥር ነው የቆየችው።
ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ግን ባለቤቱን መደብደብ ይጀምራል።
በተደጋጋሚ ወደ ቤተሰቦቿ እየሸሸችም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ወደ ቤቷ ትመለስ ነበር።
ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ከባለቤቱ ጋር መስማማት አለመቻሉም ፤ ዘወትር ባለቤቱን እና ልጆቹን ይደበድብ ነበር።
በአገር ባህል መሰረት ሽማግሌዎች በባለትዳሮቹ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በተደጋጋሚ ለሽምግልና ተቀምጠዋል።
ችግሮች ሳይፈቱ ሲቀሩ ወደ አባቷ ቤተሰብ ሸሸች። ሽማግሌዎች ተነጋግረው ባለቤቷ ጠባዩን እንዲያሻሽል እርሷም ወደ ቤቷ እንድትመለስ መከሯት።
እርሷ ግን ነገሩን በደንብ እንዲያጤኑት ወደ ቤቷ ብትመለስ አንደሚገላት’ ተናገረች።
የሽማግሌዎቹን ቃል አላከበረችም በሚል ሽማግሌዎቹ ታስራ እንድትገረፍ ወስነውባታል።
የሽማግሌዎቹ ውሳኔ የቦረናን ባሕል አይወክልም ፤ ይህ የጥቂት ሰዎች ውሳኔ ነው።
በሚኖሩበት አካባቢ ባለ ዛፍ ላይ አሰሯት። ይህንን ያደረጉት ልጇ እያለቀሰ፣ ሌሎች ቆመው እያዩ ነው።
በስፍራው ተገኝተው የነበሩ በሙሉ ፎቶ እንዳያነሱ፣ ቪድዮ እንዳይቀርጹ ተከልክለው ነበር።
ስትገረፍ ከዋጪሌ ዱብሉቅ አንድ መኪና በድንገት መጣ።
አንድ ልጅ ከመኪናው ወርዶ ቪድዮ መቅረጽ ጀመረ ፤ በዚህም የተፈጸመውን ወንጀል ሌሎች ሊያዩት ይችለዋል።
የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ኩሹ በዛፍ ላይ ታስራ በባለቤቷ ግርፋት ከደረሰባት በኋላ ክፉኛ ተጎድታለች።
የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል።
የቤተሰብ አባላቶቿ የደረሰባትን ወድያውኑ አልሰሙም ነበር። ለሳምንት ያህል ሕክምና ሳታገኝ ቆይታለች።
ወንጀሉ አንደተፈጸመ ወድያውኑ ቪድዮው አልተለቀቀም ነበር። ከሳምንት በኋላ ነው ሰው ያየው። ወላጆቿም የሆነውን ያዩት ከቪድዮው ላይ ነው።
መጀመርያ በአሬሮ ሆስፒታል በኋላም ወደ ያቤሎ ሆስፒታል ሄዳ ሕክምና የተከታተለች ቢሆንም የተሻለ ሕክምና በማስፈለጉ ወደ ሐዋሳ ሆስፒታል ተልካለች። "
የዋጪሌ ወረዳ አቃቤ ሕግ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጉዮ አሬሮ ጥቃቱ በቃቃሎ መንደር መፈጸሙን እና ከተፈጸመ ከሳምንት በኋላ ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል።
" መረጃው እንደደረሰን የምርመራ ቡድን በማዋቀር መረጃ መሰብሰብ ጀምረናል " ብለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ሽማግሌዎቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ጨምረው ተናግረዋል።
" ክስ ለመመስረት የሕክምና ማስረጃ እንፈልጋለን። አሁንም የሕክምና ክትትል እያደረገች በመሆኑ መረጃው ገና ተጠናክሮ አልቀረበልንም። ሕጋዊው ጉዳይ ግን ሂደቱን ጠብቆ ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።
ቪድዮ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

#Infinix_TV
ፍሬም አልባ ስማርት ቲቪ፣ ኩልል ያለ ድምፅ፣ የአንድሮይድ 11 ሲስተም የተገጠመለት፣ ዩቱዩብ ቢሉ ኔት ፍሊክስ አማዞን ቢሉ ኢንተርኔት ያለምንም እክል በፍጥነት ከሶፋዎት ምቾት ላይ ሆነው በስማርት ሪሞት መጠቀም የሚያስችል፤ ካፈለጉም በድምጾት የሚያዙት አዲሱን የኢኒፊኒክስ ስማርት ቲቪ X5 እናስተዋውቆት በ32 በ43 እና55 ኢንች ይጠብቁት፡፡
@Infinix_Et | @Infinixet
#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #PerfectFit #tvx5

#MPESASafaricom
የመብራት ክፍያችንን በM-PESA ከፍለን ፤ 10% ተመላሻችንን ከኪሳችን እንክተት ፤ የ M-PESA ቅናሽ አሁንም ቀጥሏል ፤ መብራት ተከፍሏል ተመላሽም ገብቷል!
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether

#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ
በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ማቋረጥን የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ በጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ተካቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደቀረበ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
መሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ማቋረጥ የሚቻለው የታማሚዎችን የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ፣ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ በአንቀጽ 14 ተደንግጓል፡፡
ዝርዝር አፈጻጸም የጤና ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያ እንደሚወሰን ተመላክቷል፡፡
በማይድን በሽታ የሚሠቃዩና የሕይወታቸውን ፍፃሜ የሚጠባበቁ ሰዎችን ሥቃይ ለመቀነስ የሚሰጥ የጤና አገልግሎት በረቂቅ አዋጁ የተካተተ ሲሆን፣ በጤና ባለሙያ ወይም ሥልጠና ባገኘ ማንኛውም ግለሰብ (አካላት) ሊሰጥ እንደሚችል በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 13 ተደንግጓል፡፡
" ሆስፒስ " እየተባለ የሚጠራው አገልግሎቱ የሚሰጠው ተገልጋይ የቅርብ ዘመዶቹ ስለታካሚው የበሽታ ክብደት፣ ደረጃና ስለሚያስከትው ውጤት ሊያውቁ እንደሚገባ በረቂቅ አዋጁ ተዘርዝሯል፡፡
በማንኛውም ሁኔታ የተገልጋይን ሕይወት የሚያሳጥር ሕክምና ተግባር መፈጸምን ይከለክላል ይላል፡፡
በረቂቅ አዋጁ የተቀመጠው በክፍል ሦስት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሥር ከተዘረዘሩት ውስጥ፣ ስለሆስፒስ ወይም በማይድን በሽታ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሚጠባበቁ ሰዎች የሚሰጥ አገልግሎትና በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ በተመለከተ ይገኝበታል፡፡
የጤና አገልግሎቶች አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ በ12 ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን፣ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ስለአጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ ስለመብትና ግዴታ፣ ስለጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ስለልዩ የጤና አገልግሎቶችና ሌሎች 60 አንቀጾች ተካተውበታል፡፡
የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 5/2017 ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና ማኅበራት ልማትና ባህል ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
ሆስፒስ ማለት ምን ማለት ነው ?
በሕይወት መትረፍ የማይችሉ ሰዎች የሚሰጣቸው የሕክምና አገልግሎት ነው።
ታካሚው ስለሕመሙ እንዲያውቅ የሚደረግበትና ቤተሰብ (አስታማሚ) እንደሚቀበሉት የሥነ ልቦና ድጋፍና ምክር የሚገኙበትን አገልግሎት ያካተተ ነው።
የጤና ባለሙያዎች ምን አስተያየት ሰጡ ?
- ከዚህ ቀደም በመሣሪያ የታገዙ ታማሚዎች ሕይወታቸው እንደማይተርፍ እየታወቀ፣ መሣሪያውን ለመንቀል ከሥነ ምግባር አኳያ ለመወሰን ይከብድ ነበር።
- በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበት ሁኔታ የሕግ ማዕቀፍ የለውም የተወሰነ የአንጎል ክፍል እየሠራ ነገር ግን መሣሪያው እየተነፈሰላቸው እስከ 2 እና 3 ዓመታት በሕክምና የሚቆዩ ታማሚዎች ይኖራሉ።
- በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚቋረጥበትን ሁኔታ ውሳኔ ለመስጠት ማረጋገጫ በሚሰጡ ሆስፒታሎች የሥነ ምግባር ኮሚቴ መኖር አለበት።
- ጉዳዩ በባለሙያ ብቻ መወሰን የሌለበት በመሆኑ በየጤና ተቋማቱ ራሱን የቻለ የሥነ ምግባር ኮሚቴ መቋቋም ይገባዋል።
(#ሪፖርተር_ጋዜጣ)

“ የሞቷ ምክንያት ምን እንደሆነ ፓሊስ እያጣራ ነው ” - ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጂ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ሩት ማርሻ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየች ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከቀናት በፊት አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ተማሪዋን፣ “ በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ” ከማለት ውጪ ስለአሟሟቷ የጠቀሰው ግልጽ ማብራሪያ የለም።
ይህ በእንዲህ እያለ “ ተማሪዋ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በመጣላቷ ከፎቆ ተወርውራ ነው የተገደለችው ” የሚሉ ወሬዎች እየተዘዋወሩ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ያሰራጫችሁት ፅሑፍ ተማሪዋ በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፈች ከመግለጽ ውጪ ስለአሟሟቷ አያብራራም፤ በሌላ ወገን ደግሞ ተማሪዋ የሞተችው “ ከፎቅ ተወርውራ ” እንደሆነ እየተገገረ ነው፣ እውነታው ምንድን ነው ? ሲል ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል።
ከዩኒቨርሲቲው የሕዝብና ዓለም ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ምላሽ የሰጡን አቶ ማቲዎስ ጪናሾ፣ “ በፃፍነው ላይ ድንገት ሕይወቷ አለፈ ነው የሚለው። አሁን ደግሞ የሞቷ ምክንያት ምን እንደሆነ ፓሊስ እያጣራ ነው ያለው ” ብለዋል።
“ እርሷ ጋር የነበረ ልጅም አለና ከእርሱ ኢንቬስቲጌት እያደረጉ ስለሆነ መረጃውን ፓሊስ ይፋ ሲያደርግ እኛም ይፋ እናደርጋለን ብለን ነው እየጠበቅን ያለነው ” ነው ያሉት።
እስካሁን የተገኘ ፍንጭ አለ ? ከፎቅ ተወርውራ ስለመገደሏ አመላካች ጉዳዮች፤ የአሟሟቷ ሂደት እንዴት ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ ፣ “ የአሟሟት ሂደቱን እኛ አሁን ይሄ ነው ብለን መናገር አንችልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ምክንያቱም ጉዳዩን የያዘው ፓሊስ ነው። የሞቷ ምክንያት ይሄ ነው ብሎ ይፋ ሲያደርግ ነው ይፋ ማድረግ የምንችለውና አሁን እኛም የተረዳነው ነገር የለም ” ሲሉም አክለዋል።
“ ዝም ብለው ወሬዎቹ አሉ። ወሬዎቹ የተለያዩ ናቸው” ያሉት አቶ ማቲዎስ፣ “ ‘ከ4ኛና 5ኛ ፎቅ ወድቃም’ ይባላል፤ ‘ሰው አንቋትም’ ይባላል፤ የተለያዬ ወሬ ነው ያለውና ያንን አሁን እንደ ምክንያት አንቀበልም። መቀበል የምንችለው የተጣራ መረጃ ሲገኝ ነው ” ብለዋል።
አደጋው የደረሰው ከቀናት በፊት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ እንደሆነ፣ አስከሬኑ አዲስ አበባ ወደሚመለከተው ሆስፒታል ሌሊት ተወስዶ፣ በማግስቱ ሀዋሳ ከቤተሰብ እንደደረሰ፣ ቤተሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደፈጸመ፣ ዩኒቨርሲቲውም ትላንት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት እንዳካሄደ አቶ ማቲዎስ ተናግረዋል።
በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቀው የወላይታ ሶዶ ዞን ፓሊስ ለጊዜው ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ደግሞ ጉዳዩን እንደሚያጣራ ገልጿልናል።
(ጉዳዩን እስከመጨረሻው በመከታተል ተጨማሪ መረጃ እናደርሳችኋለን)
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ፎቶ ፦ የሁሉ አባት የሆኑት የአባ መፍቀሬ ሰብእ ክቡር አስከሬን ሌሊቱን በርዕሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ሰዓታት ፣ ማኅሌት ሲደረስ አድሮ ፣ በክብር አሸኛኘት ወደ ደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በመድረስ በአሁኑ ሰዓት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐት እየተደረገ እንደሚገኝ ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የተገኘው…
ተፈጸመ !
የሊቀ ትጉኃን ባሕታዊ አባ መፍቀሬ ሰብእ ኪዳነወልድ የቀብር ስነ-ስርዓት በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ እና አቡነ ኢየሱስ ሞዓ አንድነት ገዳም ተፈጽሟል።
የቀብር ስነ-ስርዓታቸው የደሴና አካባቢው የተለያዩ እምነት ተከታዮች በተገኙበት ነው የተፈጸመው።
የፎቶ ባለቤት ፦ የደቡብ ወሎ ኮሚኒኬሽን

#እድታውቁት #አዲስአበባ
አጠቃላይ በ571 የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች " የተለያዩ ሥራዎች (ጥገናና የመልሶ ግንባታ ስራ) ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።
በተለዩት አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚቋረጠው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሲሆን የሚቋረጥበትን ሰዓት እንዲሁም ቀናት በዝርዝር ይፋ አድርጓል።