ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሹመት ሰጥተዋል።
በቅርቡ ፕሬዜዳንት ሆነው በተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የፍትሕ ሚኒስትሩን ጌዴዮን ጢሞቲዮስን (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል።
የኢትያጵ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ሃና አርዓያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል።
በተጨማሪም ፥ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሆነዉ በማገልገል ላይ የነበሩት ሰላማዊ ካሳ የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነዉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል።
@tikvahethiopia

#ውቕሮ
° " እሁድ ተድራ ሓሙስ በጭካኔ ተግድላለች " - የውቕሮ ከተማ ነዋሪች
° " ገዳዩ ሙሽራ እጅ ሰጥቷል፤ የድርጊቱ መንስኤ እየተጣራ ነው " - የውቕሮ ከተማ ፓሊስ
ከመቐለ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ትንሽዋ እና ደማቅዋ የውቕሮ ከተማ ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም የሃዘን ማቅ ለብሳ ውላለች።
በሃያዎቹ ዕድሜ የምትገኘው ሊድያ በአዲስ አበባ ከተማ በኮንስትራክሽን ሰራዎች የተሰማራች ወጣት ምሁር ነበረች።
ድል ባለ ሰርግ ለማግባትም ወደ ውቕሮ ትግራይ ተጓዘች።
እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም በውቕሮ ከተማ በደማቅ የሰርግ ስነስርዓት " የወደፊት የትዳር አጋሬ " ያለቸውን ወጣት አገባች።
" የሙሽሪት ሊድያና ባለቤትዋ ሰርግ ደማቅ ነበር " ይላሉ የውቕሮ ከተማ ነዋሪዎች።
ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ እሮብ ሙሽሪትና ሙሽራ በውቕሮ ከተማ በሚገኘው ባለ ኮኮብ ሆቴል በጫጉላ ሽርሽር ነበሩ።
ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ለአራት ቀናት የቆየው ደስታ ወደ ሃዘን ተለወጠ።
ሙሽሪት ሊድያ በባልዋ ተገደለች ፣ መገደልዋ ለፓሊስ የጠቆመው ገዳይ ሙሽራ ነው።
ፓሊስ ግድያ ወደ ተፈፀመበት ቦታ ድረስ በመሄድ ፤ ተጠራጣሪ ሙሽራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ የቀጠለ ሲሆን ፤ ሙሽራው ሙሽሪትን አንቆ ነው የገደላት ብሏል።
ፓሊስ ጭካኔ የተሞላው የግድያ ተግባሩ መነሻው ምን እንደሆነ በተሟላ መልኩ አጣርቶ ጉዳዩ ለሚመለከተው የህግ አካል ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ማለቱ ተሰምቷል።
ግድያው ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የውቕሮ ነዋሪዎችን ሀዘን ላይ ጥሏል።
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች " ደስታና ሀዘን ተቀላቀለብን ፤ ሙሽሪት እሁድ ተድራ ሓሙስ በጭካኔ ተግድላለች " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፍርድ ቤት በ ' አሻም ' ስያሜ ጉዳይ ያሳለፈው ውሳኔ ምንድነው ?
🔵 አሻም ቴሌቪዥን ስያሜውን መጠቀም ይቀጥላል ፤ 5,000,000 ብር ለፍርድ ባለመብት ለመክፈልም ተስማምቷል።
የፍርድ ባለመብት ኢካሽ የማማከር፤ ስልጠናና ፕሮሞሽን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር (አሻም የሬድዮ ዝግጅት) እና የፍርድ ባለዕዳ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር (አሻም ቴሌቪዥን) " ጉዳያችንን በሥምምነት ጨርሰን ቀርበናል " በማለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
በዚህም የአፈፃፀም ክርክሩ እንዲቋረጥ እና አስቀድሞ ተሰጥቶ የነበረው የአፈፃፀም ትእዛዝ ቀሪ እንዲሆን በማለት ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም የእርቅ እና ድርድር ስምምነት በመጻፍ አቤቱታ ጠይቀዋል።
የእርቅና የድርድር ውላቸውም የፋይሉ አካል ሆኖ እንዲመዘገብ እና በሥምምነታቸው መሠረት እንዲፈፀም ነው የጠየቁት።
የእርቅ እና ድርድሩ ይዘት ምን ይላል ?
- የፍርድ ባለዕዳ " አሻም " በሚል ስያሜ የቴሌቪዥን ስርጭት ማስላተለፉን እንዲቀጥል፤
- የፍርድ ባለመብት የፍርድ ባለዕዳ " አሽም " የሚለውን ቃል በቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜነት እንዲጠቀምበት ፈቃድ የሰጠው መሆኑ፤
- የፍርድ ባለዕዳ ብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን ብር) ለፍርድ ባለመብት ለመክፈል የተስማማ እና እ.ኤ.አ ታህሳስ 12 ቀን 2024 (ታህሳስ 03 ቀን 2017 ዓ.ም) የሚመነዘር የዘመን ባንክ ቼክ ቁጥር B1026682 የሆነ በዕለቱ ለፍርድ ባለመብት የሰጠው መሆኑ፤
- የፍርድ ባለመብት በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 የሚተላለፈው " አሽም የሬዲዮ ፕሮግራም የማሰራጨት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በመስማማት በእርቅና በድርድር ሥምምነት ጉዳዩን መጨረሳቸውን ይገልጻል።
የፍርድ ባለመብት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደምመላሽ ታደሰ እና የፍርድ ባለዕዳ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ግዛው ዘርጋው ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳዩን በእርቅ መጨረሳቸውን ገልፀዋል፡፡
የፍርድ ባለመብት የፍርድ ባለዕዳ " አሻም " በሚል ስያሜ የቴሌቪዥን ስርጭት ማስተላለፉን እንዲቀጥል እና እንዲጠቀምበት ፈቃድ መስጠቱን የእርቅ ስምምነቱ አስረድቷል።
ግራ ቀኙ ፅፈውና ፈርመው ያቀረቡት የእርቅ ሥምምነት ህግንና ሞራልን የማይቃወም መሆኑን ፍርድ ቤቱ በመረዳት እርቁን ተቀብሎ አፅድቋል ፤ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝም ብሏል።
አስቀድሞ ሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝም (ማለትም አሻም ቴሌቪዥን ስያሜውን እንዳይጠቀም የሚለውን) ቀሪ አድርጓል።
ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎት ሰጥቶ የነበረው የአፈፃፀም ትዕዛዝ በተለዋጭ ትዕዛዝ ቀሪ አድርጓል። ይህንን የአፈፃፀም ትዕዛዝ ተከትሎ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስም ሆነ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የተሰሩ ሥራዎች ያሉ ከሆነ ቀሪ እንዲያደርግ ታዟል፡፡
" አሻም ቴሌቪዥን " ስያሜውን መጠቀም ይቀጥላል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" ሌሊት 10 ሰዓት ነው በትዳር አጋሯ የተገደለችው ፤ አንቆ ነው የገደላት " - የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ
በትግራይ፣ በውቕሮ ከተማ ድል ባለ ሰርግ ከተሞሸረች በኃላ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ ታንቃ ስለተገደለችው ሊዲያ ዓለም ጉዳይ የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ለቢቢሲ አማርኛው ቃላቸውን የሰጡት የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ሙሉ ብርሃን ካህሳይ ፥ " ሊዲያ ረቡዕ፣ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ነው የተገደለችው " ብለዋል።
" ባለቤቷ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ለፖሊስ እጁን ሰጥቷል ፤ አሁን በሕግ ቁጥጥር ስር ይገኛል " ሲሉ አክለዋል።
ለድምጺ ወያነ ቃላቸውን የሰጡት የውቕሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ገብረ መድኅን ገብረጊዮርጊስ ፥ " ተጠርጣሪው ብርሃነ ገብረጨርቆስ የተባለ ግለሰብ ነው " ብለዋል።
" የ4 ቀናት ባለቤቱን አንቆ ነው የገደላት " ሲሉ ተናግረዋል።
ግለሰቡ እጁን ለፖሊስ ከሰጠ በኋላ ራሱን ለማጥፋት የተለያዩ ሙከራዎች አድርጎ እንደበረ ገልጸዋል።
" ፖሊስ አስፈላጊውን ጥበቃ እና ክትትል እያደረገ ነው " ብለዋል።
ሙሽራው የውቕሮ ተወላጅ እና በአዲስ አበባ በንግድ ስራ ይተዳደር ነበር። ውቕሮ ባረፈበት ሆቴል ውስጥ ንብረቱ እንደተገኘ ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪው ሙሽራ እና የተገደለችው ሙሽሪት ሊዲያ ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3 ነው በደማቅ የሰርግ ሥነ ሥርዓት የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ፈጽመው የነበሩት።

ኢትዮ ቴሌኮም !
የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን እንዴት በቀላሉ በቴሌብር ሱፐርአፕ መግዛት እንደሚችሉ ይመልከቱ፦ https://youtu.be/I44YC8mz5YE
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ተጨማሪ መረጃ ወደ 128 ይደውሉ!

YouTube
የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን እንዴት በቀላሉ በቴሌብር ሱፐርአፕ መግዛት እንደሚችሉ ይመልከቱ! #Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp
የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ተበስሯል፤ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮን ለገበያ ቀርቧል!
የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር፤ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 9,900 ብር (33 አክስዮኖች፤ ከፍተኛው 999,900 ብር (3,333 አክስዮኖች) ነው፡፡
የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል፤ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡
ለተጨማሪ…

#ብርሃን_ባንክ
ብርሃን ባንክ የ150 በመቶ ትርፍ እድገት አስመዘገበ !
ባንኩ 15ኛ መደበኛና 6ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤን ሐሙስ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሂዷል፡፡
(ሙሉ መረጃ ከላይ ተያይዟል)
More : https://t.iss.one/berhanbanksc

#ወላይታዞን
“ ከ1,000 በላይ መምህራንና የቢሮ ሠራተኞች የሐምሌ ደመዎዝ አልተከፈለንም ” - የወላይታ ዞን መምህራን
“ በአራት ወረዳዎች ሙሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው ” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ
በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው፣ በዚህም የትምህርት ሥራ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተጀመረ መምህራኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ክፍያ አለመፈጸሙን ተከትሎ አብዛኛዎቹ መምህራን ለማስተማር ፈቃደኞች ባለመሆናቸው የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደተስተጓጎለ ነው የገለጹት።
“ ከ1,000 በላይ መምህራንና የቢሮ ሠራተኞች የሐምሌ ደመወዝ አልተከፈለንም ” ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ እንኳን ደመወዝ ሳይከፈል ተከፍሏቸውም ኑሮውን መቋቋም እንዳልተቻሉ ባለስልጣናቱ በደንብ ሊረዱ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ያልተከፈለውን ጨምሮ ከዚህ ወዲያ ደመወዛቸው በወቅቱ እንዲፈጸምላቸውም በአንክሮ ጠይቀዋል።
ለምን ክፍያው አልተፈጸመም ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጉደና ሙሉ ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው አምነው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
“ አራት የወረዳዎች ላይ ሙሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው።
ከዚህ በፊትም ይታወቃል ከበጀት ካሽ ጋር ተያይዞ ወላይታ ዞን ላይ የደመወዝ ችግር ነበር። አሁን ግን እሱ ተቀርፎ ከዚህ በኋላ ሁሉም ሠራተኞች ሙሉ ደመወዝ ያገኛሉ።
በዞኑ ወረዳዎች የሚጠቀሟቸው በርካታ እዳዎች ስላሉ የሐምሌን ደመወዝ ሰብስበው እንዲጠቀሙ የሚል አቅጣጫ ተቀምጦ በዛው መልክ እየተሰራ ነው ያለው።
የመምህራን ብቻ ሳይሆን ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች ወረዳዎች ላይ ሙሉ ደመወዝ አላገኙም። ግን ክፍያቸው እስከ 70 ፐርሰንት የደረሰ፤ እየጨረሱ ያሉ ወረዳዎችም አሉ።
ከሞላ ጎደል ችግሮች እየተፈቱ ነው። የሐምሌ ደመወዝ ስላልተከፈለ በሚል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የትምህርት ሥራን ለማስተጓጎል የሚሞከሩ ሙከራዎች አሉና እሱ ተገቢ አይደለም።
አለመከፈሉ ስህተት ነው ግን በተከፈለው ደመወዝ ሥራ መስራት ይገባል። እየሰሩ ይጠይቁ ” ብለዋል።
በዞኑ የመምህራንን ጨምሮ የሌሎችም የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱ አለመፈጸም በተደጋጋሚ ማጋጠሙ የሚታወቅ ሲሆን ሠራተኞቹ የከፋ ችግር ለማሳለፍ እንደገደዱ እንደሆነ ከዚህ ቀደምም ሲያማርሩ ነበር።

" የቅልጥ ዓለቱ እንቅስቀሴ እስከቀጠለ ድረስ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ የመቀጠል እድል አለው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ሰዓት አከባቢ በ 'አዋሽ ፈንታሌ' የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ንዝረቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል፡፡ ትናንት ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት መሰማቱ ይታወሳል። አሁንም ዳግም የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ መከሰቱ ታውቋል። በአዲስ…
#አፋር
በአፋር ክልል ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።
በቦታው የባለሙያ ቲም አዋቅሮ የላከው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው እንደተከሰተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጦ ለአካባቢው ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ በአጽንኦት አሳስቧል።
ህዝቡ ላይ የከፋ ከደጋ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው አካላት ሊያደርጉት የሚገባው ርብርብ ምንድን ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ዩኒቨርሲቲው የጂኦሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና መምህር ኖራ ያኒሚኦ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
“ የአደጋው ምክንያት ምንነት አሁን ታውቋል። አደጋው የተፈጠረው የቀለጠ አለት በሚያደርገው እንስቃሴ ነው።
ስለዚህ የከሰም ግድብ የሚባል ስኳር ፋብሪካ አካበቢ አለ። አደጋው እዛ አካባቢ ላይ የሚከሰት ከሆነ የከፋ ጉዳት ሊያከተል ይችላል። ምክንያቱም የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ እየተፈጠረ ነው።
አደጋው ካልቆመና የግድቡ አካል የሚነካ ከሆነ ከግድቡ ቁልቁለት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
ስለዚህ በተለይ የአዋሽ ፈንታሌ የወረዳ ካቢኔዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች ህብረተሰቡን ከቁልቁለታማው ቦታ የውሃ ፍስት ወደማይደርስበት ወደ ሌላ ቦታ ያውርዱ።
ተራራ ስር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ታዝበናልና እነዛ ሰዎች ወደ ሜዳ የሚመጡበት መንገድ ቢፈጠር ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም አሊ በበኩላቸው፣ ወደ ቦታው ባለሙዎችን እንደላኩ ገልጸው፣ “ በአካባቢው የግድብ ስራዎች አሉ። አደጋው ከጨመረ ቀፈን ቀበና ያለው ግድብ ትልቅ ፋክተር ተደርጎ ተፈርቷል ” ብለዋል።
“ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ሊደረግለት ይገባል ግድቡ። አንዴ ጉዳት ከደረሰበት ህዝቡን ጠራርጎ ነው የሚወስደው። ከፍተኛ ቦታ ላይ ነው ያለው። በጣም ብዙ መሬትን ሊያካልል የሚችልም ነው ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አደጋው የሚጨምር ነው የሚቀንስ ? ምን እየተሰራ ነው ? አደጋው ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳትስ በምን ደረጃ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ተመራማሪና መምህር ኖራ በበኩላቸው ተከታዩ ማብራሪያ ችረዋል።
“ የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ነው። ከሦስት ሳምንታት ወዲህ የትላንት ስድስት ሰዓቱን ጨምሮ አደጋው ሦስት ጊዜ ተከስቷል።
መነሻው በክልሉ ሳቡሪ ቀበሌ ነው። ከዛ ተነስቶ ነው እስከ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አዋሽ አካባቢዎች ላይ ንዝረቱ የሚሰማው።
በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አማካኝነት አንድ ቲም ተዋቅሮ ለሁለት ሳምንታት በቦታው ተገኝተን ምልከታዎችን እያደረግን ነው። ሙያዊ ሥራዎችን እየሰራን ነው። ለህዝቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠንም ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሚከሰትበትን ቦታ መለየት ይቻላል። በዚህ ሰዓት ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመት ግን አይደለም። አሁን ባለን ቴክኖሎጂና እውቀት ቦታዎቹን መለየት ብቻ ነው የሚቻለው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ዋናው ምክንያቱ ከሥር የቀለጠው አለት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ማግማው ወደላይ ሰንጥቆ መውጣት እስከሚያቆም ድረስ አደጋው ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል።
እስካሁን ድረስ እየተመዘገበ ያለው ከ4.5 እስከ 4.9 ሬክተር ስኬል አካባቢ ነው፤ ይሄም ያን ያክል ጉዳት የሚያደርስ አይደለም መካከለኛ ስኬል ነው። 7 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው አደጋው ከፍተኛ ሊሆን የሚችለው ” ብለዋል።
በመጀመሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተበት ቦታ ፍል ውሃ መፍለቁ፤ ነዋሪውም ውሃውን ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ይታወሳል፤ የተገኘ የምርምር ውጤት አለ እንዴ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ አሰስመንት ላይ ነን። ካጠናቀቅን በኋላ ሙሉ መረጃ እናጋራለን ” የሚል ነው።

" በህክምና ሞያ ብቻ 10 ዓመት በላይ ተምረናል እድሜያችን ወደ ጎልማሳነት ተጠግቷል ቤተሰብ ማስተዳደር ፣ ለልጆቻችን ወተት እና ዳይፕር መግዣ እስከማጣት ድረስ ነው ያቃተን " - ሐኪም
በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክልል፣ ሃዲያ ዞን የሚገኘው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምሩ ሐኪሞች ፦
➡️ የ4 ወር ዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ)፣
➡️ የ14 ወር የኦቨር ሎድ ክፍያ (Over load)
➡️ የ2016 የአንዋላይዜሽን (Annualization) ክፍያ ስላልተከፈላቸው ማስተማራቸውን ለመቀጠል እንደሚቸገሩ ለዩኒቨርሲቲው በጻፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተውና ለዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች የተጻፈው ደብዳቤ በቁጥር 48 የሚሆኑ መምህራን ሐኪሞች ፊርማቸውን አስፍረውበታል።
ከማህጸንና ጽንስ፣ ከውስጥ ደዌ ፣ ከሰርጀሪ እና ከህጻናት ህክምና ክፍል የተወጣጡ ናቸው።
በጻፉት ደብዳቤ ሐኪሞቹ የማስተማር ሂደቱ ላይና የተጠራቀሙ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን በሚመለከት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና ሌሎች ከሚመለከታቸው አመራሮች ጋር የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በተገኙበት ተደጋጋሚ ውይይቶችን ቢያደርጉም መፍትሄ ባለማግኘታቸው እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ይገልጸል።
በመሆኑም ከ05/02/17 ጀምሮ የማስተማር ስራቸውን በጊዜያዊነት እንዳቆሙና ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ሃላፊነት እንደማይወስዱ ለዩኒቨርሲቲው አሳውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ለመምህራኑ ደብዳቤ ምላሹን በደብዳቤ የሰጠ ሲሆን የማስተማር ስራቸውን በመደበኛነት እንዲቀጥሉ እና ይህን የማያደርጉ መምህራን ሐኪሞች ላይ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅራቢ ሐኪሞችን በስልክ በማነጋገር ሃሳባቸውን ተቀብሏል።
በሆስፒታሉ የሚያስተምሩ የጤና ባለሞያዎች " የዲዩቲ ወይም የትርፍ ሰዓት ክፍያው ጨምሮ ሌሎችም ክፍያዎች እንዲከፈላቸው ተደጋጋሚ የሆነ ሙከራ ቢያደርጉም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ማስፈራሪያ እየደረሰን ይገኛል " ብለዋል።
የህክምና ሞያ በባህሪው ከመደበኛ የስራ ሰዓት በተጨማሪ የምሽት እና የአዳር ሰዓትን ጨምሮ ለተጨማሪ ሰዓታት እንዲሰሩ የሚያስገድድ ሲሆን በሆስፒታሉ የሚያስተምሩ ሲኒየር ሐኪሞች ባለፉት 4 ወራት የሰሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው ለከባድ የኢኮኖሚ ጫና መዳረጋቸውን ነግረውናል።
ካነጋገርናቸው መካከል አንደኛው ሐኪም ፦
" በህክምና ሞያ ብቻ 10 ዓመት በላይ ተምረናል እድሜያችን ወደ ጎልማሳነት ተጠግቷል ቤተሰብ ማስተዳደር ፣ለልጆቻችን ወተት እና ዳይፕር መግዣ እስከ ማጣት ድረስ ነው ያቃተን።
እኛ ትርፍ ነገር አልጠየቅንም ኑሮ ውድነቱ የሚታወቅ ነው በደሞዝ ብቻ መኖር አልቻልንም ለልጆቻችን የምንቋጥረው ምግብ ከአቅም በላይ ሆኖብናል።
መሰረታዊ ፍላጎታችንን እናሟላ የሰራንበተን ክፈሉን ነው ያልነው " ብለዋል።
እንደ ሐኪሙ ገለጸ የኑሮ ውድነቱ በተለይም አነስ ያለ ደሞዝ በሚከፈላቸው ነርሶች ላይ ከፍቷል።
ምግብ ሳይበላ መጥቶ በስራ ላይ ሳለ ራሱን ስቶ የወደቀና የቤት ኪራይ የሚከፍለው አጥቶ ቴሌቪዥኑን ያስያዘ ነርስ በሆስፒታል አለ ነው ያሉት።
በሚሰሩበት እና በሚያስተምሩበት በዋቻሞ ዪኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው የንግሥት እሊኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕረንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲውን ሃላፊዎችን ቢያናግሩም መፍትሄ እንዳጡ ነግረውናል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ ሐኪሞች " መኖር አልቻልንም " ሲሉ ክብደቱን አስረድተዋል።
ከተጠራቀመው የትርፍ ሰዓት ክፍያ ውስጥ የአንድ ወር ክፍያ ባለፈው ወር እንደተከፈላቸው ገልጸው ነገር ግን ዘግይቶ ስለተከፈለ " ከብድራችን አላለፈም ሁላችንም በብድር ነው የምንኖረው " ብለዋል።
" የብድር አዙሪት ውስጥ ገብተናል ደሞዝ እንቀበላለን ያልቃል ከዛ እንበደራለን፣ ብድር እንከፍላለን እንደዚህ ነው እየኖርን ያለነው " ሲሉ አስረድተዋል።
በተጨማሪ ሐኪሞቹ ፦
- የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ችግራቸውን ከመፍታት ይልቅ ሰዎችን ለይቶ ማስፈራራት ላይ እንደተጠመዱ ፤ የዲፓርትመንት ሃላፊዎችን ለይቶ በማስፈራራት " እናንተ ናችሁ እያሳመጻቹ ያላቹት የሙያ ፈቃዳቹ ይነጠቃል " እስከማለት እንደደረሱ፤
- ለሆስፒታሉ፣ ለተማሪው ፣ለማህበረሰቡ እና ለሰራተኞች የሚያስብ ሃላፊ እንዳጡ ፤
- ተወካዮች ከዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃየሶ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ፕሬዝዳንቱ " ችግሩ ያለው ግቢያቹ ውስጥ ነው የሆስፒታሉ የውስጥ ገቢ የት እንደሚሄድ አላውቅም የውስጥ ገቢው የተጠየቀውን ክፍያ መክፈል መቻል አለበት " ማለታቸውን፤
- ለቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐብታሙ አበበ ቅሬታቸውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ችግራቸው ሳይፈታ ፕሬዝዳንቱ በሙስና እና ሐብት ምዝበራ ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 15/2016 ዓም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፤
- ከትምህርት ሚኒስቴር ሊያማክሩ የመጡ በትምህርት ሚኒስትር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የተወከሉ ሰዎች ባሉበት ስብሰባ ላይ አዲስ ፕሬዝዳንት ስለሆነ ጊዜ እንዲሰጠው ፣ ነገሮችን አስተካክሎ እና አይቶ የእነሱን ክፍያ በቅድሚያ እንዲከፈል እንደሚያደርጉ እንደነገሯቸው እና እስካሁን መታገሳቸውን ጠቁመዋል።
ነገር ግን እስካሁን ከመፍትሄ ይልቅ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጻዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አያኖ ሻንቆ ምን ምላሽ ሰጡ ?
ስራ አስኪያጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃን ፥ መምህራኑ የጠየቁት ክፍያ ያልተከፈላቸው መሆኑን አምነዋል።
" አልከፍልም ያለ ሰው የለም ለምንድነው ስራ የሚያቆሙት ? የዲዩቲ እና ኦቨርሎድ ክፍያ ከደሞዝ ጋር አይገናኝም ለደሞዛቸው መስራት አለባቸው የትርፍ ሰዓት ክፍያ ግን ሲሰሩ ብቻ ነው መክፈል የሚቻለው አሁን ላለመግባት ከወሰኑ በቀጣይ ያልሰሩበት ይቆረጥባቸዋል " ብለዋል።
" በአንድ ጊዜ ያልተከፈለውን ክፍያ ሁሉ ለመክፈል የሆስፒታሉ በጀት የማይበቃ በመሆኑና ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ስለሌለ የሚመጣውን ገንዘብ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ሰጥተን ነው የምንከፍለው በጀቱን እየጠየቅን ነው ሲፈቀድ እንከፍላለን አንከፍልም ያለ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም " ይህን መሰል ችግር እኛ ጋር ብቻ አይደለም ያለው እናንተ ጋር ስለደረሰ ነው እንጂ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ችግር አለ " ያሉ ሲሆን " በእኛ በኩል በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ችግሩ ይፈታል ብለን እናስባለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ንጉስማልት
ቀዝቃዛ ንጉስዎን ይዘው ፤ ጣት የሚያስቆረጥመውን ማዕድዎን ያጣጥሙ።
ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/Negus_Malt
#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት

" መዋጋት ርስት አይደለም። ለ42 ዓመታት በውግያ ቆይቻለሁ። እኔ እጣ ፈንታዬ መዋጋት ነው ብዬ አላምን ፤ አቋሜ ውግያ አያስፈልግም ይቁም የሚል ነበር ፤ አሁንም አቋሜ ያው ነው የተለወጠ የለም !! " - ጄነራል ሳሞራ የኑስ
ከሰሞኑን የቀድሞው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሳሞራ የኑስ አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር።
ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደ ሚዲያ ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት ብራኸ (ከፍታ) ለተሰኘ በዩትዩብ ላይ ለሚተላለፍ ፕሮግራም ነው።
ምን አሉ ?
የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከመተካታቸው በፊት በእሳቸው (ጄነራል ሳሞራ) እና በአገር ድህንነት ሃላፊ በነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል አለመጣጣም እንደነበር በዚህም ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር እያሉ እንዲያስሯቸው ሲጠይቋቸው " አላስርም ! " ማለታቸውን አንሰተዋል።
ጄነራል ሳሞራ የኑስ ፥
" ያኔ ዐብይን እሰረው ተብዬ አይሆንም ካልኩኝ ዛሬም ልክ ነኝ። ምክንያቱ እኔ የሰራዊት መሪ እንጂ የሲቪል ፓለቲከኛ አሳሪና መሃሪ አይደለሁም።
መከላከያ ሲቪል ፓለቲከኛ የማሰር ስልጣንና ልኡክ የለውም።
ዐብይ ያኔ የአንድ ታላቅ ክልልና ህዝብ አመራር ነበር። ታላቁ ህዝብ ማለት ኦሮሞ ነው። ያኔ የኦሮሞ ህዝብ መሪ የፓለቲካ ድርጅት የነበረው ኦህዴድ ነው። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አብይ ነበር። በተጨማሪም የፓርላማ የህዝብ ተመራጭ አባል ነበር።
ዐብይ ያኔ መታሰር ከነበረበት ጥንካሬና ድክመቱ ወደ ሳራሞራ ሳይሆን ወደ ፓርለማ ነው የሚወሰደው።
ከፓርላማ ካለፈ ወደ ያኔው የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይቀርባል።
የኢህአዴግ ሊቀመንበሩና ጠ/ ሚንስትሩ የዐብይ ድክመት ልክ ነው ብሎ ካመነበት ከፓርላማ ሃላፊነቱ ማንሳት አለበት።
እንዲህ ሆኖ ራሱ ሃይለማርያም ደሳለኝ ዐብይን የማሰር ስልጣን ስለሌለው ወደ ኦህዴድ መላክ አለበት።
ኦህዴድ ካመነበት ደግሞ ይታሰር ብሎ ከወሰነ የሚመለከተው የህግ አካል እንጂ ሳሞራ ዐብይን የማሰር ስልጣን የለውም " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ፦
- በትግራዩ ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ እልቂት መፈጸሙን እንደሚያምኑ፤
- የትግራዩ ጦርነት መንስኤ የፓለቲካ ብልሽት ፤ የአመራሮች መበስበስና ከህዝብ አገልጋላይነት መውጣት ውጤት እነደሆነ፤ የአማራ ኤሊቶች የትግራዩ ጦርነት አንዲጋጋል ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ በርካታ እላፊ ነገሮች እንደተናገሩ፤
- የትግራዩ ጦርነት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ ወታደሮች የተሳተፉበት ቢሆንም የሁሉም ክልሎች ህዝብ ደግፎታል ተሳትፎበታል ማለት እንዳልሆነ፤
- በትግራይ ጦርነት የሻዕብያ ሃይል አጋጣሚው በመጠቀም የትግራይን ህዝብ ያለ ስሙ ስም በመስጠት አንገቱ ለማስደፋትና ለማጥፋት እንደዘመተ፤
- ከጦርነቱ በፊት ከምርጫው ጋር ተያይዞ የነበሩት የእልህ አገላለጾችና አካሄድ እንዲቆሙ በሁለቱም በኩል ሲገስጹ እንደነበር፤
- ጦርነቱ እንዳይነሳ ፤ ከዛም እንዲቆም ብዙ ጥረት እንዳደረጉ፤
- " ጄነራል ሳሞራ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ወግነው በድብቅ ጦርነት መርተዋል / ተሳትፈዋል " የሚለው ወሬ ጦርነቱ የከበዳቸው የትግራይ ፓለቲከኞች ለድክመታቸው መሸፈኛ የፈጠሩት እንደሆነ ፤ ጦርነቱ ሲጀመርም ሆነ ሲፋፋም ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ እንደነበሩ፤
- መዋጋት ርስት እንዳልሆነ ፤ ለ42 ዓመታት በውግያ እንደቆዩ ፤ እጣ ፈንታቸው ውግያ ነው ብለው እንደማያምኑ ፤ አቋማቸው ውግያ አያስፈልግም የሚል እንደሆነ ፤ አሁንም ድረስ አቋማቸው ያው እንደሆነ፤
- ያልተዘጋጁበትን፣ ያላመኑበትን ወግያ እንደማይሳተፉ፣ እንደማይዋጉ፤
- እምነታቸው የትግራይ ህዝብ መዋጋት የለበትም የሚል እንደሆነ ፤ እንደ አመራር ህዝቡ ወደ ውግያ መግፋት የለበትም የሚል እንደሆነ ፤
- ውግያ ሲጀመር አከባቢ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ እና አቶ ግርማ ብሩን አግኝተው ውግያ እንዳይጀመር እንደጠየቁ ፤ እነሱም እንደ አመራር የሰጧቸው መልስ እንዳለ፤
- ጦርነቱ በተጀመረ ማግስት መንግስትንና ጀነራሎቹን ጦርነቱ እንዲቆም እንደጠየቁ ፤ እስከ መጨረሻ ድረስም ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ጥረት እንዳደረጉ፤
- የትግራይ ህዝብ ሃያ ዓመት እየቆጠረ መዋጋት እንደሌለበት ፤ ጦርነትም እንደሰለቸው፤ የሰላም አርአያ መሆን እንደሚፈልግ ፤ ፓለቲከኞችም የህዝበ ሰላም መጠበቅ እንዳለባቸው፤
.... የሚሉና ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተዋል።
የጄነራሉ አቋም የአሁን ወይስ የነበረ ?
የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ጄነራል ሳሞራ የኑስን ከ5 ዓመታት በፊት በ2012 ዓ.ም ህዳር እና ታህሳስ ወር ላይ እንዲሁም ጦርነቱ ተጀምሮ የፌደራል መንግስት መቐለ በተቆጣጠረበት ወቅት የካቲት 2013 ዓ.ም በአካልና በስልክ አግኝቶዋቸው ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።
ጀነራል ሳሞራ ሀገራዊ ኒሻን ተሸልመው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አግኝቶ ባናገራቸው ወቅት ፥ በዚህም በዚያም በወጣቶች የሚታይ የነበረው የጦረኝነት ስሜት ፓለቲከኞቹ በማርገብ ሃላፊነታቸው እንዲወጡ ወታደራዊ ምክር ሰጥተው ነበር።
ጥር 2012 ዓ/ም ደጀና ላይ 45ኛው የህወሓት የምስረታ በዓል ለማክበር ለተሰባሰቡት ወጣቶች ባሰሙት ንግግር ፥ ወጣቶች ከዚህም ከዚያም ያሉ ፓለቲከኞች በሚለኩሱት ጦርነት ገብተው እንዳይቃጠሉ የሚያስገነዝብ አባታዊና ወታደራዊ ምክር አስተላልፈው ነበር።
ጦርነቱ ከተጀመረ እና ከተባባሰ በኃላ በሰጡትም አስተያየት ጦርነትን ከበፊቱ የባሰ እንደተጠየፉት ገልፀውለት ነበር።
ያንብቡ👇
https://teletype.in/@tikvahethiopia/lTm24ja5TwM