TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረማያ አስቸኳይ! Urgent!

ለሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ወደ ግቢ እየተመለሱ ላሉ ተማሪዎች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ስላዘጋጀ ቅዳሜና እሁድ ማለትም 30-03-2010ና 01-4-2010 ጠዋት በአዳማ አዲሱ መናሀርያና በአዲስ አበባ ነባሩ አውቶብስ ተራ በመገኘት
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ይጋብዛል፡፡

0255530035 / 0910253360
#Urgent

Barattoota Yuunivarsiitii Haramayaa Hundaaf Ministeerri barnootaa Yuunivarsiitii Haramayaa waliin ta'uun barattoota gara yuunivarsiitiitti deebi'a jiraniif tajaajila
geejjiba tolaa waan qopheesseef sanbataa fi dilbata ganama 1. Finfinnee buufata konkolaataa biyyaalessaatti.
2. Adaamaa buufata konkolaataa haaraatti argamuun akka
fayyadamtan isin affeera.

ምንጭ፦ ቢኒ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Urgent

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን ለማከናወን ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ዝግጅቶች መካከል ስድስት ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎችን አሰልጥኖ በትላንትናው እለት ስምሪት የጀመረ ሲሆን የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ ስርጭትም በዛሬው እለት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን የተወሰኑ ርቀት ያላቸው የምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁስ አለመድረሱን ቦርዱ ስለተረዳ የመራጮች ምዝገባ መጀመሪያ ቀን በሁሉም ቦታዎች እኩል እንዲጀመር በማሰብ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ ወስኗል፡፡ በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት እና ህብረተሰቡ የመራጮች ምዝገባ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀመር አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ያሳውቃል፡፡

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Urgent

ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች።

ገና የመመረቋን ደስታ ሳታጣጥም እንደቀልድ ለ " ቶንሲል ህመም " በሚል ምርመራ ስትደረግ ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረድታለች።

ዶክተሯ የደም ካንሰር በአይነቱ ደግሞ " acute lymphoblaatic leukemia " የሚባል እንዳለባት በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት።

የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድም አፋጣኝ የሆነ የመቅኒ ንቅለ ተከላ እንዲደረግላት መወሰኑን ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል።

የደም ካንሰር ምንም እንኳን እጅግ አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመዳን እድል ያለው በሽታ ነው።

መላው ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን እና ወደፊት ህዝቧን በሞያዋ የምታገለግል ሀኪም ህይወት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።

ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ ምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት።

እንደአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰብ አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም። ስለሆነም አቅም ያላችሁ ሁሉ ድጋፋችሁ ታደርጉ ዘንድ ቤተሰቦቿ ተማፅነዋል።

በስልክ ደውሎ ለማነጋገር በ0913922441 ላይ መደወል ይቻለል።

Dr Bethel Germamo Ganebo
➡️ የባንክ አካውንት CBE 1000105102384

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯 " በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት ርብርብ ውስጥ የነበረው ማህበረሰብ በአደጋው አልቋል ! " - የጎፋ ዞን ፖሊስ በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ አሁን ላይ የሟቾች ቁጥር እጅግ በጣም እየጨመረ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉን አግኝቷቸዋል። " ሁኔታዉ እጅግ አሳዛኝ ነው " ብለዋል። በመጀመሪያው ናዳ የተጎዱትን ለማዉጣት…
#Urgent🚨

የጎፋ ዞን ፖሊስ የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ የደረሰ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" የሰው ኃይል በጣም ተዳክሟልም " ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በጎ ፈቃደኞች በጉልበትም ፣ በምግብ እና በአልባሳት አቅርቦት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በተለይ ወደቦታዉ ማቅናት የሚችሉ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ቢኖሩ ብዙ ሊያግዙ ይችላሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆነ የመሬት ናዳ አደጋ በተመለከተ ከስፍራው የሚያገኛቸውን መረጀዎች እና መልዕክቶች ያደርሳችኋል።

@tikvahethiopia
#Urgent🚨

ኢትዮጵያዊው ተማሪ ጣሊያን ሀገር ለትምህርት በሄደበት ህይወቱ አልፎ ተገኘ።

የ22 ዓመቱ አቤኔዘር ተሰማ አበበ በትምህርት ጉዳይ በስኮላርሺፕ ነው ወደ ጣሊያን ሀገር፣ ሲሲሊ ግዛት ያቀናው።

በመሲና ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበር።

ከትላንትና በስቲያ ማታ እንደተኛ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የህልፈቱን ምክንያት ፖሊስ እየመረመረ እንደሚገኝ ጉዳዩን ከሚያውቁ የቅርብ ቤተሰቦቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

የተማሪ አቤነዘር አስክሬንን ወደ ሀገር ቤት ለመምጣት ወጪው ከፍተኛ እንደሆነ ከቤተሰቦቹ ለመረዳት ተችሏል።

ቤተሰብ በታላቅ የልብ ስብራት ውስጥ ስለሚገኝ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያን እንድትረባረቡ ጥሪ ቀርቧል።

ጎፈንድሚ https://gofund.me/01490b2f

አቶ ተሰማ አበበ 1000020084913 (ንግድ ባንክ)

አቶ ተሰማን በስልክ ማግኘት የምትፈልጉ በ 0911817718 ላይ መደወል ይችላል።

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Urgent🚨

በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጠለምት ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል።

በርካቶችም ችግር ላይ ወድቀዋል፤ ተፈናቅለዋል።

ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል።

ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወረዳው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል።

የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ቃል ፦

“ አካባቢው ከዚህ ቀደም በድርቅ የተጠቃ ነው፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች ደግሞ ከ14, 400 በላይ እህል ያስፈልገናል።

የእርዳታ ምግብ ድጋፍ ፤ 480 ድንኳን / ሸራ ፣ እንደ ብረት ድስት፣ ሳፋ አይነት የቤት ቁሳቁሶች በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ ናቸው። ”

#TikvahEthiopiaFamyAA

@tikvahethiopia
#Urgent🚨

በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀርቧል።

በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በተለይ በደቡብ እና ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርቧል።

ጽ/ቤቱ በደቡብ እና ምሥራቅ ሊባኖስ ያለው የፀጥታ ችግር እየተባባሰ እንደመጣ አመልክቷል።

ይህን ተከትሎ በአካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጠቁሟል።

በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ከታች በተቀመጠው መሠረት ፦

➡️ ስማቸውን ፓስፖርት ላይ እንደተፃፈው፣

➡️የፓስፖርት ቁጥር

➡️ ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

° በደቡብ ሊባኖስ (ታየር ፣ ሱር ፣ ቢንት ጅቤል ፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89

° በምሥራቅ ሊባኖስ (አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት አሳስቧል፡፡

#Share #ሼር

@tikvahethiopia